ጊዜ የገንዘብ ቁጠባና ብድር

ጊዜ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በሕግ ታውቆ በምዝገባ ቁጥር ቦሌ/1/1234/2013 የተመዘገበ ለመሆኑ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ወረቀት በኅዳር 15 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. ተሰጥቶት ሥራ ጀምሯል።

ጊዜ የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ ራእይ፣ ተልዕኮ እና ዕሴቶች

ራእይ

በምስራቅ አፍሪካ ላይ የሚገኝ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኅብረት ሥራ ማኅበር መመስረት

ተልዕኮ

አባላት የገንዘብ አቅማቸውን የሚቆጣጠሩበትና የሚያሳድጉበትን መንገድ መፍጠር፤ ይህም ለዜጎች እና ለመንግሥት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ይኖሩታል።

ዕሴቶች

  • ሀቀኝነት
  • የሠለጠነ ባለሙያ
  • ተጠያቂነት
  • የኅብረት ሥራ

ጊዜ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • መደበኛ ቁጠባ
  • የፍላጎት ቁጠባ
  • የቤት ቁጠባ
  • የመኪና ቁጠባ
  • እና ሌሎች የቁጠባ አገልግሎቶች በተመጣጣኝ ወለድ አገልግሎት ይሰጣል
ተ.ቁ የብድር ዓይነት የብድር መጠን በብርቅድመ ቁጠባበተከታታይ መቆጠብ ያለበት ጊዜየወለድ ተመንየብድር ዓመት
1መደበኛ ብድር፣ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለማኅበራዊ ጉዳይ እና ለአነስተኛ ንግድ16 ሺሕ - 600 ሺሕ25%6 ወር እና ከዚያ በላይ12.5% (በ1 ዓመት ከተመለሰ)
13.25% (በ3 ዓመት ከተመለሰ)
1 ዓመት
3 ዓመት
2መኪና ብድር600 ሺሕ - 800 ሺሕ40%6 ወር እና ከዚያ በላይ14.5%3 ዓመት
3መኪና ብድር800 ሺሕ -1.5 ሚሊዮን40%1 ዓመት እና ከዚያ በላይ14.5% (በ3 ዓመት ከተመለሰ)
15.5% (በ5 ዓመት ከተመለሰ)
3 ዓመት
5 ዓመት
4ለቤት መሥሪያ / ማደሻ600 ሺሕ - 800 ሺሕ30%6 ወር እና ከዚያ በላይ14.5%3 ዓመት
5ለቤት መሥሪያ / ማደሻ800 ሺሕ - 2 ሚሊዮን30%1 ዓመት እና ከዚያ በላይ15.5%5 ዓመት
  • አንድ አዲስ አባል የብድር አገልግሎት ለማግኘት ቢያንስ ለተከታታይ 6 ወር መቆጠብ አለበት
  • ለቤትና ለመኪና ለተከታታይ 6 ወር መቆጠብ ይኖርበታል
  • የገቢ መግለጫ፣ ተመጣጣኝ ዋስትና፣ የጋብቻን ሁኔታን የሚገልጽ ሰርተፍኬት (የራሱንም፣ የዋሱንም) ባል ወይም ሚስት ማቅረብ ይኖርበታል።
  • የደመወዝ ዋስ እስከ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺሕ ብር) ለሚበደር ቢያንስ ብር 10,000.00 (ዐሥር ሺሕ ብር) የወር ደመወዝ ያለው ዋስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  • ከብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺሕ ብር) በላይ ለሚኖር ማንኛውም ብድር ደግሞ የመኪና ሊብሬ፣ የቤት ካርታ እንዲሁም የአክሲዮን መጠን መቅረብ ይኖርበታል።
  • የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ
  • እድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ
  • በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ደንብና መመሪያ ተገዢ ለመሆን ፈቃደኛ የሚሆን
  • በህግ መብቱ ያልተገፈፈ
  • የመመዝገቢያ ክፍያ ለአንድ ጊዜ ብቻ ብር 500 (ዐምስት መቶ ብር) መክፈል የሚችል
  • የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1000.00 (አንድ ሺሕ ብር) ሲሆን አንድ አባል መግዛት ያለበት ዝቅተኛ የዕጣ መጠን አንድ ነው
  • የማኅበሩ መነሻ መደበኛ ቁጠባ መጠን ብር 500 (ዐምስት መቶ ብር) በየወሩ መቆጠብ የሚችል

ጊዜ የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

ዋና መሥሪያ ቤት፦ ፓልም ሕንጻ (ሲኤምሲ)፣ 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 104

ስልክ

  • +251 929 234622
  • +251 979 700070

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ  የተዘጋጀው ጊዜ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ሥራ ማኀበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …