መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / ግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር
global-logo

ግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር

ግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዋጅ 985/2009 እና ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በወጡ ደንቦች መሠረት የተቋቋመት የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።

ግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

ራዕይ

እስከ 2020 ዓ.ም. ቁጠባ በማሰባሰብ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት በአገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ አቻ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት መካከል ብቁና ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት

ተልዕኮ

ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተ ሰብ ክፍል በአባልነት በማሰባሰብ የቁጠባ ባሕሉን ማዳበርና አስተማማኝ የሆነ የባንኪንግ አገልግሎት በመስጠት የአባላትን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አቅም ማሻሻል

ዓላማ

  • ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የኅብረተ ሰብ ክፍል በአባልነት ማሰባሰብ
  • ለአባላት ጠቀም ያለ ዓመታዊ ትርፍ ማስገኘት (ማከፋፈል) እና ሌሎችም የተቋሙ ዓላማዎች ናቸው።

ግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር፦ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • የኅብረት ሥራ ማኅበሩን ሕገ ደንብ የተቀበለ
  • ዕጣ መግዛት የሚችል የአንድ ሼር (ዕጣ) ዋጋ ብር 1,000 ሆኖ አምስትና ከዚያ በላይ ዕጣ መግዛት የሚችል
  • በተቋሙ ሕገ ደንብ መሰረት በየወሩ መደበኛ ቁጠባ ብር 500 በተሻለ ወለድ ለመቆጠብ ፍቃደኛ የሆነ
  • አንድ ግለሰብ አባል እንዲሆን ሲፈቀድለት በምዝገባ ወቅት የመመዝገቢያ ብር 1000 ይከፍላል
  • የዕጣው ግዢ አከፋፈል ሁኔታ በምዝገባ ወቅት አባሉ ሊገዛ የፈለገውን የዕጣ ብዛት 50% ይከፍላል
  • ቀሪውን የመጀመሪያው ክፍያ በከፈለ እስከ ሥስት ወር ከፍሎ የሚያጠናቅቅ ይሆናል
  • ለተለያዩ ቢዝነሶች መነሻና ማስፋፊያ ብድር መስጠት
  • ለቤት መሥሪያ ብድር መስጠት
  • ለኮንዶሚኒየም ቤት ቅድመ ክፍያና ሙሉ ክፍያ ብድር መስጠት
  • ለህክምና ብድር መስጠት
  • አባሉ የብድር አገልግሎት የሚያገኘው አባል ከሆነ ከ6 ወር በኋላ ሆኖ የቆጠበውን ገንዘብ አራት ዕጥፍ የመበደር መብት አለው።
  • ለአባላት በተለያየ አርዕስት በተሻለ ወለድ ብድር መስጠት
  • ከተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች የአደራ ገንዘብ ተቀብሎ ማስተዳደር
  • ለአባላትና አዲስ አባል ለሚሆኑ ግለሰቦች የቢዝነስ ልማት (Business Development) ሥልጠና እና የማማከር አገልግሎት መስጠት
  • በተጠኑና አዋጭነት ባላቸው የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሳተፍ አባላትን ተጠቃሚ ማድረግ

ግሎባል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኅበር:- አድራሻ

አድራሻ
  • ሰሜን ሆቴል ሀበሻ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር
  • +251 118 12 66 16
  • +251 911 02 24 45
  • +251 901 08 42 74
ኢሜይል
  • Gscmcs@yahoo.com

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ግሎባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …