ታዳጊ ወይም መስፋት

ወደ ታዳጊ ደረጃ ለማደግ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማራ ጥቃቅን/አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ

  1. በሥራ ዕድል ፈጠራ
    • የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል፡-
      • ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ በቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ እስከ 3 ሰዎች የቀጠረ (በደመወዝ ክፍያ ሰነድ የሚከፍል)
      • ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ እስከ 6 ሰዎች የቀጠረ
    • የፈጠረው ጊዜያዊ የሥራ ዕድል፡-
      • ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል በዓመት ውስጥ እስከ 2 ሰዎች የቀጠረ
      • ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል በዓመት ውስጥ እስከ 5 ሰዎች የቀጠረ
  2. በሃብት መጠን
    • ጠቅላላ ሃብት ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከ50,001 እስከ 75,000 ብር (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
    • ጠቅላላ ሃብት ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከ100,001 እስከ 500,000 ብር (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
    • በብድርም ሆነ በራሱ ገንዘብ ሥራ ለጀመረ፣ ካገኘው ሃብት ቢያንስ 50% ለቋሚ ንብረት ያዋለ
    • ቋሚ ንብረት ኖሮት ለግብዓት የሚበደር፣ ብድሩን ሙሉ በሙሉ ለሥራ ያዋለ
    • የሃብት እና የእዳ መግለጫ (ኦዲት ሪፖርት) ህጋዊ እውቅና ባለው ኦዲተር ያረጋገጠ
  3. በትርፋማነት
    • በ1 ዓመት ካደረገው ሽያጭ ቢያንስ 10% ትርፍ ያስመዘገበ
    • ከትርፉ ላይ ለሥራ ማስፋፊያ ያዋለው ወይም የቆጠበው፣ ከተጣራ ሃብቱ ቢያንስ 20% የሆነ
  4. በገበያ መጠን
    • የ1 ዓመት ሽያጩ፡-
      • ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ከ75,000 እስከ 100,000 ብር የሆነ
      • ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከ150,000 እስከ 750,000 ብር የሆነ
    • እንደየ ንዑስ ዘርፉ፣ ተከታዩ መጠን ሽያጭ ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ የሆነ
      • ኮንስትራክሽን – ቢያንስ 30%
      • ብረታ ብረትና እንጨት – ቢያንስ 70%
      • ሌሎች ንዑስ ዘርፎች – ቢያንስ 75%
    • ቢያንስ ሦስት ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን የተጠቀመ
    • ለደረጃው በተዘጋጀ ኤግዚቢሽንና ባዛር ቢያንስ በዓመት ሁለቴ የተሳተፈ
  5. በምርታማነት
    • ካለው ሙሉ የማምረት አገልግሎት የመስጠት አቅም ቢያንስ 50% የተጠቀመ
    • ከኢንተርፕራይዙ አባላት ወይም ቋሚ ሠራተኞች ውስጥ ቢያንስ 70% ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያላቸው
  6. በተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት
    • ዘመናዊ የሥራ አመራር ዘይቤ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረ
    • የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ሥራ ላይ ያዋለ፣ የሂሳብ መግለጫ ያዘጋጀ ወይም ኦዲት የተደረገ
    • የማምረቻ ማዕከሉ አደረጃጀት የምርት ሂደትን የተከተለና ንጽሕናውን የጠበቀ
    • የሠራተኞችን የሥራ ደህንነት ለመጠበቅ የሥራ ልብስ እና እንደ ንዑስ ዘርፉ ዓይነት የደህንነት መሣሪያዎች የተሟሉለት
    • ሥራውን ሊያስፋፋ የሚያስችል በጽሑፍ የተዘጋጀ የንግድ ዕቅድ ያለው
    • ከሌሎች ኢንተርፕራይዞች ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥም ሆነ በጋራ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል የንግድ ግንኙነት የፈጠረ
  7. በመንግስታዊ ድጋፎች አጠቃቀም
    • የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተግባር ላይ ያዋለ
    • ያልተመለሰ ውዝፍ ብድር የሌለበት (ብድር ተጠቃሚ ከሆነ)
    • የውል ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ (የማምረቻ ማዕከል ተጠቃሚ ከሆነ)
    • በመንግስት የሚሰጠውን የገበያ ትስስር በገባው ውል መሠረት በአግባቡ እየሠራ ያለ ወይም ሠርቶ ያስረከበ
  8. በቴክኖሎጂ አጠቃቀም
    • ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማሻሻል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሰራጩ ተፈላጊና አዋጪ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ ለመሆን ቅድመ ዝግጅት ለማድረጉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
    • ከሚጠቀምባቸው የማምረቻ ወይም የአግልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ውስጥ ቢያንስ 50% የአካባቢ ብክለት የማያስከትሉና ኃይል ቆጣቢ የሆኑ
  9. ግዴታን ስለመወጣት
    • የሚጠበቅበትን ዓመታዊ ግብር የከፈለ
    • ዓመታዊ የንግድ ፈቃድ እድሳት ያካሄደ
    • የተሠጠውን የዕድገት ደረጃ ሰርቲፊኬት የመለሰ

በአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማራ ጥቃቅን/አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ

  1. በሥራ ዕድል ፈጠራ
    • የፈጠረው ቋሚ የሥራ ዕድል፡-
      • ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ በቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ እስከ 2 ሰዎች የቀጠረ (በደመወዝ ክፍያ ሰነድ የሚከፍል)
      • ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በቋሚ የሥራ ዕድል የኢንተርፕራይዝ አባላቱን ጨምሮ እስከ 6 ሰዎች የቀጠረ
    • የፈጠረው ጊዜያዊ የሥራ ዕድል፡-
      • ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል በዓመት ውስጥ 1 ሰው የቀጠረ
      • ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በጊዜያዊ የሥራ ዕድል በዓመት ውስጥ እስከ 4 ሰዎች የቀጠረ
  2. በሃብት መጠን
    • ጠቅላላ ሃብት ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ እስከ 40,000 ብር (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
    • ጠቅላላ ሃብት ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከ50,001 እስከ 200,000 ብር (የተጣራ ሃብት እና እዳን ጨምሮ)
    • በብድርም ሆነ በራሱ ገንዘብ ሥራ ለጀመረ፣ ካገኘው ሃብት ቢያንስ 20% ለቋሚ ንብረት ያዋለ
    • ቋሚ ንብረት ኖሮት ለግብዓት የሚበደር፣ ብድሩን ሙሉ በሙሉ ለሥራ ያዋለ
  3. በትርፋማነት
    • በ1 ዓመት ካደረገው ሽያጭ ቢያንስ 10% ትርፍ ያስመዘገበ
    • ከትርፉ ላይ ለሥራ ማስፋፊያ ያዋለው ወይም የቆጠበው፣ ከተጣራ ሃብቱ ቢያንስ 15% የሆነ
  4. በገበያ መጠን
    • የ1 ዓመት ሽያጩ፡-
      • ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ እስከ 75,000 ብር የሆነ
      • ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከ75,001 እስከ 200,000 ብር የሆነ
    • ከሽያጩ ቢያንስ 70% ከመንግስት የገበያ ትስስር ውጪ የተገኘ
    • ቢያንስ ሦስት ዓይነት ውጤታማ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን የተጠቀመ
  5. በምርታማነት
    • ካለው ሙሉ የማምረት አገልግሎት የመስጠት አቅም ቢያንስ 50% የተጠቀመ
    • ከኢንተርፕራይዙ አባላት ወይም ቋሚ ሠራተኞች ውስጥ ቢያንስ 70% ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ያላቸው
  6. በተቋማዊ አመራርና አደረጃጀት
    • ዘመናዊ የሥራ አመራር ዘይቤ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረ
    • የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ሥራ ላይ ያዋለ፣ የሂሳብ መግለጫ ያዘጋጀ ወይም ኦዲት የተደረገ
    • የማምረቻ ማዕከሉ አደረጃጀት የምርት ሂደትን የተከተለና ንጽሕናውን የጠበቀ
    • የሠራተኞችን የሥራ ደህንነት ለመጠበቅ የሥራ ልብስ እና እንደ ንዑስ ዘርፉ ዓይነት የደህንነት መሣሪያዎች የተሟሉለት
    • ሥራውን ሊያስፋፋ የሚያስችል በጽሑፍ የተዘጋጀ የንግድ ዕቅድ ያለው
    • ከሌሎች ኢንተርፕራይዞች ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥም ሆነ በጋራ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል የንግድ ግንኙነት የፈጠረ
  7. በመንግስታዊ ድጋፎች አጠቃቀም
    • የሚሰጠውን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ተግባር ላይ ያዋለ
    • ያልተመለሰ ውዝፍ ብድር የሌለበት (ብድር ተጠቃሚ ከሆነ)
    • የውል ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ (የማምረቻ ማዕከል ተጠቃሚ ከሆነ)
    • በመንግስት የሚሰጠውን የገበያ ትስስር በገባው ውል መሠረት በአግባቡ እየሠራ ያለ ወይም ሠርቶ ያስረከበ
  8. በቴክኖሎጂ አጠቃቀም
    • ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማሻሻል በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሰራጩ ተፈላጊና አዋጪ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ ለመሆን ቅድመ ዝግጅት ለማድረጉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
    • ከሚጠቀምባቸው የማምረቻ ወይም የአግልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ውስጥ ቢያንስ 50% የአካባቢ ብክለት የማያስከትሉና ኃይል ቆጣቢ የሆኑ
  9. ግዴታን ስለመወጣት
    • የሚጠበቅበትን ዓመታዊ ግብር የከፈለ
    • ዓመታዊ የንግድ ፈቃድ እድሳት ያካሄደ
    • የተሠጠውን የዕድገት ደረጃ ሰርቲፊኬት የመለሰ

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ቀድሞ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አሁን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽሕፈት ቤት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

industry

ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ዕድገት ደረጃ

ወደ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ ዕድገት ደረጃ የሚሸጋገሩ ኢንተርፕራይዞች ሊያሟላቸው የሚገቡ መስፈርቶች በሥራ ዕድል ፈጠራ ሀ) በኢንዲስትሪ …