መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / ኑ በጋራ እንደግ – ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር
goh-saving

ኑ በጋራ እንደግ – ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር

ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በኅዳር 6 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ማኅበራት ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/2009 ዓ.ም. አንቀጽ 10 መሠረት ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በግ ታውቆ በመዝገብ ቁጥር አራ/1/1/750/2014 ዓ.ም ተመዝግቦ የተቋቋመ ነው።

ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ዓላማ፣ ራዕይ፣ ተግባር እና ግብ

ራዕይ

በአባላት መካከል የቁጠባ ባሕል እንዲዳብርና እንዲስፋፋ በማድረግ፣ አባላትን በተናጠል ሊወጧቸው የማይችሏቸውን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮችን በተባበረ ጥረት ከመወጣት በተጨማሪ ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በዐጭር ጊዜ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ማድረግ

ዓላማ

  • አባላት በተናጠል በመሥራት ሊወጧቸው የማይችሏቸውን የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ችግሮች በተባበረ ጥረት መወጣት፣ መቋቋምና መፍታት
  • አባላት ያላቸውን ዕውቀት፣ ሀብትና ጉልበት በማቀናጀት የተሻለ ውጤት ማግኘት
  • በአባላት ዘንድ በራስ መተማመንን ማጎልበት
  • በአባላት መካከል የቁጠባና ብድር አገልግሎት እንዲዳብርና እንዲስፋፋ ማድረግ
  • በአባላቱ በግል ይዞታ ስር ተበታትኖ የሚገኘውን ገንዘብ በቁጠባ መልክ በማሰባሰብ የአገሪቱ ማዕከላዊ የገንዘብ ክምችት እንዲዳብር ማድረግ
  • አባላት ስለ ገንዘብ ቁጠባና ብድር የኀብረት ሥራ ማኀበር ጠቀሜታና አገልግሎት ትምህርትና ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ
  • አባላትን በማቀራረብ እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ልምድ እንዲያዳብሩ ማድረግ
  • ለአባላትና ለአካባቢው ኅብረተ ሰብ የሥራ እድል መፍጠር

ግብ

የአባላቱን ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጋራ በመቅረፍ በኅብረተ ሰቡ ዘንድ እና በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ የላቀ ሚና የሚኖረው የቁጠባ ማኅበር መገንባት

ተግባር

  • ከአባላት የዕጣ መዋጮ እና ወርሃዊ ቁጠባ በመሰብሰብ በማኀበሩ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ውስጥ ገቢ ማድረግ ወይንም አባላቱ ገቢ እንዲያደርጉ መሥራት
  • በአክብሮትና በታማኝነት አገልግሎት መስጠት
  • ለአባላት ገንዘብ ማበደርና ከነወለዱ መሰብሰብ
  • ለአባላት ከማኅበሩ የተበደሩትን ገንዘብ አዋጭ በሆነ የሥራ ዘርፍ ላይ እንዲያውሉት የምክርና የሥልጠና አገልግሎት መስጠት
  • ለአባላት ቁጠባና ወለድን በየጊዜው ማሳወቅ
  • የማኀበሩን ሂሳብ በየዓመቱ መዝጋትና ማስመርመር
  • ዓመታዊ የትርፍ ድርሻን ለአባላት ማሳወቅና በጉባኤው ውሳኔ መሠረት ማከፋፈል

ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

የአዋቂ ቁጠባ

    አገልግሎቱን ለመጠቀም
    • መመዝገቢያ - 350 ብር
    • ወርሃዊ ቁጠባ - 250 ብር
    • ዝቅተኛ እጣ (ሼር) - 1000 ብር

የልጆች/ሕፃናት ቁጠባ

አገልግሎቱን ለመጠቀም
    • መመዝገቢያ - 200 ብር
    • ወርሃዊ ቁጠባ - 150 ብር
    • ዝቅተኛ እጣ (ሼር) - 1000 ብር
    • እድሜያቸው ከ18 (ዐሥራ ስምንት) ዓመት በላይ ሲሆን የሚንቀሳቀስ ይሆናል
    • ቁጠባ የተቆጠበለት ልጅ (ህጻን) ታሞ፣ ለትምህርት ወይም ወደ ውጪ ሀገር ክሄደ እና አሳማኝ ምክንያቶች ከቀረቡ የልጅ (ህጻን) ቁጠባን ማንቀሳቀስ ይችላል

የቤት ቁጠባ

አገልግሎቱን ለመጠቀም
    • መመዝገቢያ - 500 ብር
    • ወርሃዊ ቁጠባ - 350 ብር
    • ዝቅተኛ እጣ (ሼር) - 3000 ብር
    • የትኛውም የቤት ቆጣቢ ለመበደር 1 (አንድ) ዓመት ሳያቋርጥ መቆጠብ አለበት
የትኛውም አባል ለመበደር 8 (ስምንት) ወር ለተከታታይ ሳያቋርጥ መቆጠብ አለበት
  • ሊበደር ያሰበውን ገንዘብ መጠን በቁጠባ ደብተር ½(አንድ ሁለተኛ) መቆጠብ አለበት
  • የብድር ወለድ 13% (አስራ ሦስት በመቶ)
  • የመመለሻ ጊዜ እንደሚበደሩት ብር የተለያየ ሰሌዳ አለው
  • ለቤት ብድር ሊበደር ያሰበውን ገንዘብ በቁጠባ ደብተሩ 1/3 (አንድ ሦስተኛ) መቆጠብ አለበት
  • ለቤት ብድር ወለድ 13.5% (አስራ ሶስት ነጥብ አምስት በመቶ) ነው
  • የብድር መመለሻ ጊዜ እንደተበደሩት ገንዘብ መጠን የተለያየ ሰሌዳ አለው

ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር አድራሻ እና ስልክ

ዋና መ/ቤት

አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09፣ አራት ኪሎ ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ቁጥር 1 ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302

ስልክ ቁጥር

  • +251 964 424964
  • +251 919 005922

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …