harbu-mfi

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በ2005 ዓ.ም. በፋሲሊቴተር ፎር ቼንጅ (መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም) ድጋፍ አማካኝነት የተቋቋመ ተቋም ነው። ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የዕሴት ሰንሰለት ልማት እና የፋይናንስ አገልግሎቶችን ተደራሽነት በመደገፍ የግብርና ምርታማነትን እና የግብርና ግብይትን ለማሳደግ ያለመ ነው።

ሀርቡ፦ ራዕይ፣ ዕሴት፣ ተልዕኮ እና ምሥረታ

ራዕይ

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በኢትዮጵያ የባንክ አገልግሎት የማያገኙ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በቅርበት እንዲያገኙ ለማስቻል ከሚሠሩ ዋና ዋና የግል የፋይናንስ አካታች ተቋማት አንዱ ሆኖ መታየት ነው

ዕሴቶች

ታማኝነት፣ ቀልጣፋ አገልግሎት፣ ደንበኛን ማስቀደም፣ ለለውጥ መዘጋጀት፣ በጋራ መሥራት፣ በቴክኖሎጂ መታገዝ፣ መከባበር እና ሕግን ማክበር

ተልዕኮ

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የገጠር አርሶ አደሮች፣ ሴቶች፣ የተረሱ የቡድን አባላት እና ሥራ አጥ ወጣቶችን ማዕከል አድርጎ ወቅታዊ፣ አስተማማኝ፣ ጥራት ያለው፣ ተመጣጣኝ እና እንዲሁም ተስማሚ የገንዘብ አገልግሎቶችን በመስጠት ቤተሰቦታቸውን በቀጥታ በመለወጥ እና በዚህም አስተዋፅዖ የሃገር ኢኮኖሚ ልማት አንዲመጣ ማድረግ።

ሀርቡ ማይክሮፋይናንስ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  1. የግብርና እና የግብርና ኢንዱስትሪ
  2. የንግድ ሥራ (ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ)
  3. የማኑፋክቸሪንግ እና ኢንዱስትሪዎች ምርቶች
  4. አገልግሎት
  1. የግብርና ብድሮች (አጠቃላይ ግብርና፣ የሰብል ተኮር ብድሮች፣ የዕሴት ሰንሰለት ፋይናንስ)
  2. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች (MSE) ብድሮቸ
  3. የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SME)ብድሮች
  4. ለሴቶች ሥራ ፈጣሪዎች እና የንግድ ባለቤቶች (WEDP) የሚሰጥ ብድር
  5. በግለሰብ የንግድ ሥራ ለተሰማሩ የሚሰጥ ብድር
  6. በቡድን ለተደራጁ ወጣቶች እና ሴቶች ሥራ ፈጣሪዎች የሚሰጥ ብድር
  7. ተቀጥረው ለሚሰሩ ሠራተኞች ደመወዝን ዋስትና አድርጎ የሚሰጥ ብድር
  8. የትምህርት ብድር
  1. በግብርና እና ተዛማች ሥራዎች ላይ ለተሰማሩ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች
  2. በጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ለተሰማሩ ወጣቶች
  3. በግል እና በቡድን ተደራጅተው ለሚመጡ ወጣቶች
  4. በሥራ ላይ ላሉ ሴቶች ልዩ ብድር
  5. በግል ሥራ ለተሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎች ልዩ ብድር
  6. በግል እና በመንግሥት ሥራ የተሰማሩ ደንበኞች
  1. በፈቃደኝነት መቆጠብ
  2. በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የደብተር (መደበኛ) ቁጠባ
  3. የሳጥን (የሙዳይ) ቁጠባ
  4. ቅድመ-ብድር ቁጠባ
  5. የህጻናት ቁጠባ
  6. የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ገንዘብ ቁጠባ
  7. የገጠር ቁጠባ (RSF)
  1. የብድር ሕይወት መድህን
  1. በቤት ውስጥ እና በውጭ ባለሞያዎች የሚሰጡ ሥልጠናዎች
  2. የገንዘብ አያያዝ
  3. የንግድ እቅድ ዝግጅት
  4. የሥራ ፈጠራ ንግድ አመራር ክህሎት
  5. የሂሳብ አያያዝ
  6. የደንበኞች አገልግሎት
  7. የከተማ ግብርና
  1. በአረንጓዴ ኢነርጂ አቅርቦት ምርቶች ላይ የገጠርና ለከተማ ነዋሪ ቀልጣፋና ውጤታማ የፋይናንስ ድጋፍ ይሰጣል
  2. በካፒታል መጠን ላይ በመመርኮዝ በንግድ ምርጫ ላይ ነፃ ቀጣይነት ያለው ምክር ይሰጣል
ሀርቡ ማይክሮፋይናንስ መሥርያ ቤቱ የሚገኘው ቦሌ አትላስ ሆቴል ጀርባ ሲሆን በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ማግኘት ይቻላል።
  1. +251 11 6630294
  2. +251 11 6684382

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …