መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / ፓልም የምግብ ዘይት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በሃገር ውስጥ በከፊል ሊመረት ነው

ፓልም የምግብ ዘይት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በሃገር ውስጥ በከፊል ሊመረት ነው

መንግስት በዜጎች ላይ የኑሮ ውድነት እንዳይፈጠር መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦችን በድጎማ ከውጪ ከሚያሥገባቸው ሸቀጦች ውስጥ አንዱ የሆነውን ፓልም የምግብ ዘይት ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በሃገር ውስጥ ለማምረት እንቅስቃሴ መጀመሩን በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ትራንስፎርሜሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ አድማሱ ይፍሩ ተናገሩ፡፡

ፌቬላ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ደብሊው ኤ የዘይት ማምረቻና ማከፋፈያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ሸሙ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እና አል ኢምፔክስ ዘይት ማምረቻ የተባሉት አራት ፋብሪካዎች ዘይቱን ለማምረት ፍቃድ የተሰጣቸው መሆኑን አቶ አድማሱ ገልጸዋል፡፡palm-oil

እነዚህ ኩባንያዎች የምርት ሂደታቸውን በቅርቡ እንደሚጀምሩ የገለጹት ዳይሬክተሩ ለግብዓትነት የሚጠቀሙበትን የዘይት ድፍድፍ ከውጪ ለማስመጣት ይቻል ዘንድ ከብሄራዊ ባንክ የውጪ ምንዛሬ ጥያቄ አቅርበው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ ተናግረዋል፡፡

ሃማሬሳ የምግብ ዘይት ማምረቻ አክሲዮን ማኅበርም ዘይቱን ለማምረት ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ሂደቱ ታይቶ ፈቃድ መስጠት ሲጀመር ሚኒስቴር መ/ቤቱ ለድርጅቱ ምላሽ እንደሚሰጠው ይጠበቃል፡፡

የዜና ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …