መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ሰኢድ ሃሰን ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

ሰኢድ ሃሰን ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሰኢድ ሃሰን በ2012 ዓ.ም. የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን የሚሠራ ድርጅት ሲሆን በይበልጥ ደግሞ በፊኒሺንግ ሥራዎችን ላይ በሰፊው ይሳተፋል።

ድርጅቱ የሚሥራቸው ሥራዎች

  • ጠቅላላ የሕንጻ ግንባታ ሥራዎች
  • ጠቅላላ የመንገድ እና ተጓዳኝ ሥራዎች እና
  • የፊኒሺንግ (የሕንጻ ማጠናቀቅ) ሥራዎችን ይሠራል

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ሰኢድ ወደ ኮንስትራክሽን የሥራ ዘርፍ ሊገቡ የቻሉት ትምህርታቸው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ስለነበር እና ትምሕርት እንደጨረሱ ቀጥታ የኮንስትራሽን ሥራ ላይ ነው በመሠማራታቸው። በዘርፉም ተቀጥረው ከዐሥር አመት በላይ ሠርተዋል። በዚህ ጊዜም ስለኮንስትራክሽን ሥራ አጠቃላይ አሠራር ከቀለም ትምህርታቸው በተጨማሪ ሌሎች በልምድ የሚዳብሩ ዕውቀቶችን መያዝ እንዲችሉ አድርጓቸዋል።

ይህን የግንባታ ሥራ ልምድ ካደበሩ በኋላ ሰዎችን ሥራው እንዴት እንደሚሠራ ጠንቅቄ አውቃለሁ፣ ስለዚህ በራሴ ብሠራ ውጤታማ መሆን እችላለሁ በማለት ነው ድርጅቱን የመሠረቱት። ድርጅቱ ከጅምሩ የነበረውን አቅሙን ስላሳደገ አሁን አንድ ሙሉ 4 ፎቅ ሕንጻ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ሥራውን አጠናቆ ማስረከብ ይችላል።

የድርጅቱ መሥራች ጠንክረው በመሥራታቸው ድርጅቱ ሲመሠረት ከነበረው ሃምሳ ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ወደ አምስት መቶ ሺህ ብር ያሳደገ ሲሆን እንዲሁም ወደ ሠላሳ ለሚጠጉ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር የቻለ ድርጅት ነው። በተጨማሪም ድርጅቱ ወደ ስድስት የሚጠጉ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል።

ድርጅቱ ሥራዎችን ከሠራባቸው ቦታዎች መካከል

  • ኮዬ ፈቼ ኮንዶሚኒየም
  • ሰሚት ኮንዶሚየም እና
  • ሌሎች አርባ ስልሳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ የፊኒሺንግ ሥራዎችን እና የሕንጻ ግንባታ ሥራዎችን ሠርቷል።

ድርጅቱ ሥራዎችን እየሠራ የነበረው እና የሚገኘው በሰው በሰው ሲሆን አሁን ደግሞ ትተውት የነበረውን የጨረታ አገልግሎት 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ባዘጋጀው የከፍታ ፓኬጅ ፓኬጅ መጠቀም ጀምረዋል። አቶ ሰኢድ የከፍታ አገልግሎትን መጠቀም የጀመሩት ከወረዳ የደረጃ እድገት ባለሙያዎች ባገኙት ጥቆማ አማካኝነት እንደሆነ ተናግረዋል።

ድርጅቱ እስከ አሁን ድረስ የሚቀበለውን የዲዛይን ሥራ በአግባቡ ስለሠራ ምንም ይህ ነው የሚባል የጎላ ችግር አልገጠመው። ይሁን እና አንዳንድ ቀለል ያሉ ችግሮች ሲፈጠሩ ግን እራሳቸው አቶ ሰኢድ መፍትሔ በመፈለግ ነው እየሠሩ የሚገኙት።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ድርጅቱ በኮቪድ ወቅት ከባድ ጊዜን አሳልፏል፤ ይህም በነበረው ፍርሃት እና ለኮንስትራክሽን ሥራዎች ቅድሚያ አለመስጠት ማለትም ለምግብ እና ለመሳሰሉት ነገሮች ቅድሚያ እየተሰጠ ስለነበረ የኮንስትራክሽን ሥራ ጠፍቶ ነበር። ምንም ሥራ አልነበረም ቢሆንም አቶ ሰኢድ በግላቸው አጅ አልሠጡም አንዳንድ ሥራዎችን በመሥራት ነበር ያሳለፉት።

ምክር እና እቅድ

አቶ ሰኢድ የግል ሥራ ምን ጥቅም አለው ለሚለው ጥያቄ “በአንድ ሥራ ብቻ እንዳትወሰን ያደርጋል፤ መሥራት ያለብህን ሥራ ሠርተህ ሌላ ሥራ መሥራት ትችላለህ። የግል ሥራ እንኳን ባትሠራ የማኅበራዊ ተሳትፎዎች ላይ መሳተፍ ያስችላል። ይህ ቢቀር ደግሞ ያለህን ሥራ ለማዳበር እና ለማጠንከር ጥሩ እድል ይፈጥራል” በማለት መልስ ሰጥተዋል። ድርጅቱ ከአምስት ዓመት  እስከ ዐሥር ዓመት በሚጠጋ ጊዜ ውስጥ ወደ ደረጃ አንድ ተቋራጭነት ለማደግ እቅድ አለው።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …