ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ሄኖክ ስብሃት እና ዘጠኝ መሥራች አባላት 2013 ዓ.ም. ነው። አጠቃላይ የእንጨት ውጤቶችን የሚያመርት ድርጅት ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ተያያዥ የሆኑ የብረት ሥራዎችን ይሠራል።
ከሚያመርታቸው ምርቶች መካከል
- የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች
- ሶፋ
- አልጋ
- ኪችን ካቢኔት
ድርጅቱ ምርቶቹን በሚከተለው ዋጋ ለገበያ እያቀረበ ይገኛል
- በር:- ከ ብር 15,000 (ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ብር) ጀምሮ እስከ ብር 20,000 (ሃያ ሺሕ ብር) ድረስ
- አልጋ:- ከ ብር 15,000 (ዐሥራ ዐምስት ሺሕ ብር) ጀምሮ እስከ ብር 30,000 (ሰላሣ ሺሕ ብር) ድረስ
- ኪችን ካቢኔት:- በሜትር ካሬ ሲሆን የሚሠራው በሜትር ካሬ ከብር 8,000 (ስምንት ሺሕ ብር) ጀምሮ እያመረተ ይገኛል።
ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት
አቶ ሄኖክ ወደ እዚህ የሥራ ዘርፍ የተቀላቀሉት ከዐሥራ ሁለት ዓመት በፊት ነበር። ሙያውን ሲጀምሩ ምንም ገንዘብም ሆነ የሙያው ዕውቀት ስላልነበራቸው በረዳትነት በመቀጠር ነበር ዘርፉን የተቀላቀሉት። በሂደት ቀስ በቀስ ሥራውን እየለመዱ ሲመጡ እያደጉ በመምጣታቸው ለእሳቸው ደግሞ ሌላ ረዳት ተቀጥሮላቸው መሥራት ይጀምራሉ። በዚህ ሁኔታ ትንሽ እንደሠሩ “እኔ ዕውቀቱ አለኝ በራሴ ለምን አልሠራም የሚል ሀሳብ በውስጣቸው መመላስ ይጀምራል”። በሂደት ሁኔታዎች ይመቻቹና መንግሥት በጥቃቅን እና አነስተኛ ማደራጀት ሲጀመር እሳቸውም ለመሞከር ሲመዘገቡ ዕድል ቀንቷቸው ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን ይህን ድርጅት መሠረቱ።
ድርጅቱ ሲመሠረት የነበረው መነሻ ካፒታል ብር 10,000 (አስር ሺሕ ብር) የነበረ ሲሆን አሁን ብር 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ካፒታል ደርሷል። በተጨማሪ ደግሞ አሥራ ሰባት ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በዋናነት ሰው በሰው ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሶሻል ሚዲያን (ቴሌግራም እና ፌስቡክ የመሳሰሉትን) በመጠቀም ይሠራል። እንዲሁም ደግሞ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ላይ በመሳተፍ ባዛር ለመጎብኘት ለሚመጡ ደንበኞች ቢዝነስ ካርድ በመስጠት ሥራዎችን ይሠራል። አሁን ደግሞ በቅርቡ አቶ ሄኖክ ከጓደኛቸው ባገኙት ጥቆማ 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት በመጠቀም ጨረታዎች ላይ በመሳተፍ አቅማቸውን ለማሣደግ አገልግሎቱን አየተጠቀሙ ይገኛሉ። ድርጅቱ አሁን ያለው የገበያ አለመረጋጋት ችግር እንዳለ ሆኖ አሁን ባለው የማምረቻ ቦታ እና አቅም በአንድ ወር ውስጥ ከሃያ በላይ በሮች እና ከዐሥር በላይ ቁምሳጥኖች የማምረት አቅም አለው።
የኮቪድ ተፅዕኖ
በኮቪድ ጊዜ ድርጅቱ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነበር። ምክንያቱም ሰዎች እንዲፈሩ ስላደረጋቸው ቅድሚያ ይሰጡ የነበሩት ለሌሎች ነገሮች ነበር። በዚህም ምክንያት ምንም ገበያ አልነበረም፤ በተጨማሪ ደግሞ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግር በጣም ነበር። በነዚህ ምክንያቶች ድርጅቱ ተዘግቶ ሥራ ሙሉ በሙሉ አቁሞ ነው የኮቪድን ጊዜን ያሳለፈው።
ምክር እና ዕቅድ
የድርጅቱ መሥራች አዲስ ወደ ዘርፉ ለሚቀላቀሉ ሰዎች ችግር ሲገጥማቸው በተቻለ መጠን ተስፋ ሳይቆርጡ መትጋት እንዳለባቸው፣ በተጨማሪ ደግሞ ለሥራው አስፈላጊ የሚባሉ መሠረታዊ ልምዶችን ማዳበር አለባቸው ብለዋል። ሌላው የውስጥ ፍላጎት አስፈላጊ ሆኖ ሥራው የሙያ ሥራ እንደመሆኑ የታወቀ ሕግ ወይም ሥርዓት የለውም ተብሎ እንደልብ መሆን አያስፈልግም። በዲስፒሊን (በሥነ ስርዓት) መሥራት ይገባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ድርጅቱ ወደ ፊት የማሳያ ሱቅ የመክፈት እቅድ አለው።
የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ።