መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ሆሞዶ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ
plaster ceiling in living room

ሆሞዶ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

ሆሞዶ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የተመሠረተው በአቶ ዘላለም ሙላቱ እና በጓደኛቸው በ2010 ዓ.ም. ነው።  ሆሞዶ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን ከውሃ ሥራ በስተቀር የሚሠራ ድርጅት ነው።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ዘላለም ወደ ኮንስትራክሽን ሥራ ሊገቡ የቻሉት ከጓደኞቻቸው ጋር የነበራቸው የሥራ ልምድ እና የተማሩትም ትምህርት በኮንስትራክሽን ዘርፍ በመሆኑ እንደሆነ ገልጸዋል። አቶ ዘላላም ሆሞዶ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ድርጅትን ከመመሥረታቸው በፊት በኮንስትራክሽን ሥራ ዘርፍ ተቀጥረው ለዐምስት ዓመት ሠርተዋል።

በዘርፉ በቂ ልምድ ካዳበሩ እና ሥራው እንዴት እንደሚሠራ አስፈላጊውን ዕውቀት ከያዙ በኋላ  በኮንስትራክሽን ዘርፍ የራሳችውን አስተዋፅዖ ለማበርከት በማሰብ እንዲሁም የፈለጉትን ሥራ እሳቸው በፈለጉት መልኩ ለመሥራት በማሰብ ከጓደኛቸው ጋር ተማክረው በብር 50,000 (ሃምሳ ሺሕ ብር) መነሻ ካፒታል ድርጅቱን መሥርተዋል። ድርጅቱ አሁን የካፒታል አቅሙን ወደ ብር 550,000 (ዐምስት መቶ ሃምሳ ሺሕ ብር) ማሳደግ ችሏል። ከዚህ በተጨማሪ እንደ ሥራው መጠን እና ሁኔታ በኮንስትራክሽን የሥር ዘርፍ ለአንድ መቶ ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ አሁን ባለው የኮንስትራክሽን ደረጃ እስከ አራት ፎቅ ሕንጻ የመሥራት ፈቃድ አለው። በተሰጠው የኮንስትራክሽን ደረጃ ስለተገደበ ነው እንጂ መሥራቾቹ ትላልቅ ሕንጻዎችን ለመሥራት የሚያስችል በቂ የሥራ ልምድ  አላቸው። እንደማሳያም ለሌሎች ደረጃ ሦስት እና አራት ላሉ ሠራተኞች በቂ የሆነ የማማከር አገልግሎትን ሰጥቷል፤ እየሰጠም ይገኛል። ድርጅቱ በፊኒሺንግ እና በኮንትራክት ሥራዎች በዋናነት ከስትራክቸር ሥራ ጀምሮ ሙሉ ሥራዎችን በመሥራት አራት ፕሮጀክቶችን አጠናቅቆ አስረክቧል። በመሃል ደግሞ የተለያዩ የፊኒሺንግ ሥራዎችን ሠርቷል።

ሆሞዶ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የከፍታን አገልግሎት መጠቀም የጀመረው በቴክስት በደረሰው መረጃ መሠረት በማድረግ የ2መርካቶን ድረ-ገጽ ይመለክቱ ነበር። እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮምን የጨረታ ዶክመንት በ2merkato.com በኩል መግዛት እንደሚችሉ መረጃውን ሲያውቁ በዚሁ አጋጣሚ 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት መጠቀም ቢጀምሩ በይበልጥ አትራፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ በማሰብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሊሆኑ ችለዋል።

ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው ዋናነት በጨረታዎች ላይ በመሳተፍ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ ከመንግሥት በሚፈጠሩ ሥራዎች እንዲሁም ሰው በሰው በሚመጡ ሥራዎች ነው። እነዚህን መንገዶችን በመጠቀም ሁለት ጨረታዎችን ከመሬት ሥራዎች ኮርፖሬሽን በማሸነፍ ጣራ ማልበስ እና የአጥር ሥራዎችን ጨረታ አሸንፎ በጥራት ሥራውን በማጠናቀቅ አስረክቧል። ሌሎች ሁለት ሥራዎችን ደግሞ ከከተማ መስተዳደሩ ጋር በተመቻቹ ሥራዎች በመሳተፍ ሁለት የኮንዶሚኒየም ፕሮጀክቶች ሠርቶ አስረክቧል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በየመሃሉ ቀለል ያሉ የፊኒሽኒንግ ሥራዎችን በሰው በሰው እና በራሱ በመፈለግ ሠርቷል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

በኮቪድ ወቅት ለድርጅቱ የነበረው ሁኔታ በጣም አስፈሪ እና አስቸጋሪ ነበር፤ ምክንያቱም ድርጅቱ ሥራዎችን ይሠራባቸው የነበሩ ተቋማት ሥራ በማቆማቸው እና የኮንስትራክሽን ሥራ ከነበረው ሁኔታ አንጻር ቅድሚያ የሚሰጠው ሥራ ባለመሆኑ እንቅስቃሴ በጣም ስለቀነሰ ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ሥራ ለማቆም ተገዶ ነበር።

ምክር

የግል ሥራ የሚጀምሩ ሰዎች የግል ሥራ ቀላል አይደለም፤ ብዙ ኅላፊነቶች ያለበት እንደሆነ አውቀው ቢገቡ ብለው ይመክራሉ። ለምሳሌ ቀላል የሚመስል ነገር እንደ ልብ ከቤተሰብ ጋር በቂ ጊዜ ማሳለፍ እያለባቸው ጊዜያቸውን በሙሉ ለሥራው ለማዋል ሊገደዱ ይችላሉ። ይህ ደግሞ በጣም ከባድ ነው፤ ምንም የማይመስል ሊሆን ይችላል እየቆየ ችግር ያመጣል። ስለዚህ ይህንን አስተካክለው ቢገቡ ጥሩ ነው። ሌላው ደግሞ ብዙ ችግሮች ቢፈጠሩ ለማለፍ ዝግጁ ሆነው ቢጀምሩ ጥሩ ነው ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የሚሠሩት ማንኛውንም ሥራ ልምድ ቢኖራቸው ጥሩ ነው፤ ይህ ካልሆነ ግን ሥራው ስለሚያዋጣ ብቻ በደንብ ሳያውቁት ከጀመሩ ኪሣራ ነው። በመቀጠል ደግሞ ሥራውን ከጀመሩ በኋላ ደግሞ ራሳቸውን ከአዳዲስ ነገሮች ጋር ማላመድ አለባቸው፤ ይህም ከጊዜው ጋር ለመራመድ በጣም ጠቃሚ እንደሆነ መክረዋል።

ዕቅድ

ድርጅቱ በቀጣይ ዐምስት ዓመታት የኮንስትራክሽን ደረጃውን ወደ ደረጃ ሦስት ወይም አራት ለማሳደግ ዐቅዶ እየሠራ ይገኛል።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …