መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር
saving

ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር

ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር በ1993 ዓ.ም ተመሥርቶ በብድር እና ቁጠባ ዘርፍ እየሠራ ያለ ማኅበር ነው። ከ24,000 በላይ አባላት እና ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ሀብት አለው። በቦሌ ደምበል (ኦሎምፒያ) አካባቢ በ1083 ካሬ ሜትር ላይ ባለ 4 ፎቅ ሕንጻ እና ለቢሮ ምቹ የሆኑ ተጨማሪ ክፍሎች ያሉት ግቢ ባለቤትም ነው። በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ በ6 ቅርንጫፎች አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል።

ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር ኃ/የተ/ የኅብረት ሥራ ማኅበር ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዕሴቶች

ራዕይ

የማህበሩን አባላት በኑሮአቸው፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚ መስክ ተሻሽለው በክብርና በብልጽግና ህይወትን ሲኖሩ ማየት ነው።

ተልዕኮ

የማበሩን አባላት በተመጣጠነ ዋጋ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በማቅረብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን በማጎልበት የተሻለ አማራጭ አድል መፍጠር

ዕሴቶች

  • ጥራት እና ልቀት ያለው አገልግሎት
  • ፈጠራን የሚያበረታታ
  • ከአድልዖ የፀዳ
  • ተአማኒ የሆነ
  • ብቃት
  • አጋርነት
  • ተጠያቂነት
  • ግልጽነት
  • ሩህሩህነት

ጆሽዋ ቁጠባ እና ብድር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

በማኅበሩ የቁጠባ አገልግሎቶች ከተመጣጣኝ የቁጠባ ወለድ 7% እና በድርድር የሚወሰን የጊዜ ገደብ ቁጠባ ወለድ ክፍያ ጋር

የውዴታ ግዴታ ቁጠባ

  • ማንኛውም የማኅበሩ አባል በየወሩ በመደበኛነት የሚቆጠብ ቁጠባ

በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ቁጠባ

  • አባላት በማንኛውም ጊዜ ወጪ ሊያደርጉ የሚችሉ ቁጠባ/ የባንክ ዓይነት አገልግሎት

የፕሮቪደንት ፈንድ ቁጠባ

  • ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸው የፕሮቪደንት ፈንድ በተመጣጣኝ ወለድ ማስቀመጥ

ለህጻናት የሚቀመጥ የረጅም ጊዜ ቁጠባ

  • ማኅበሩ ለህጻናትና ወጣቶች ልዩ ትኩረት ይሰጣል

የቁጠባ ሣጥን ቁጠባ

  • ለአነስተኛ ቁጠባ በቤታቸው ቆጥበው ተጠራቅሞ ሂሳባቸው እንዲገባ የሚደረግ የቁጠባ ዓይነት ነው።

የኢንቨስትመንት ብድር

ለንግድ ዘርፍ ማቋቋሚያ ወይም ማስፋፊያ፣ ለቤት ግንባታ ሥራ ወይም እድሳት የሚውል፣ ለቋሚ ንብረት ግዢ (ለመኪና፣ ለቤት፣ ለመሬት ሊዝ ክፍያ) ለከፍተኛ ትምህርት ክፍያ፣ ሌሎች ከኢንቨስትመንት ጋር ተያያዥነት ላላቸው ሁኔታዎ፦ የብድሩ መጠን እሰከ 3 ሚሊዮን ብር ድረስ

የማኅበራዊ ጉዳይ ብድር

ለሰርግ፣ ለቀብር እና ለሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች፦ የብድሩ መጠን እስከ 100 ሺህ ብር ድረስ

ልዩ ብድር

ለሕክምና እና ለልጆች የትምህርት ቤት ክፍያ ብድር

በፕሮጀክት ላይ የተመሠረተ ብድር

የዚህ ይብድር ዓይነት፦ የብድር ጣሪያው እስከ ብር 3,000,000.00 ይደርሳል
  • በቁጠባና በዕጣ ዋስትና
  • በደመወዝ ዋስትና
  • በቋሚ ንብረት ዋስትና የሚሰጥ ብድር
  • የመኪና ዋስትና
  • የኮንስትራክሽንንና ሌሎች ማሽነሪዎች ዋስትና
  • በኅብረት ሥራ ማኅበሩ የሥራ ክልል ነዋሩ የሆነና የነዋሪነት ማረጋገጫ ያለው
  • ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
  • የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል በመሆን በኅብረት ሠርቶ በኅብረት ለማደግ ዓላማ ያለው
  • በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ደንብና መመርያ ተገዢ ለመሆን ፈቃደኛ የሆነ/ነች
  • በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
  • ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው
አንድ አመልካች አባል አንዲሆን ሲፈቀድለት
  • የመመዝገቢያ ብር 1000
  • የቁጠባ መክፈቻ ብር 500
  • ለሼር ብር 1000 በድምሩ 2500 ብር እና
  • ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍና የቀበሌ መታወቂያ / የታደሰ ፓስፖርትን መንጃ ፍቃድ
በመያዝ መመዝገብ ይችላል።
  • ለመመዝገቢያ የተከፈለ ገንዘብ በስንብት ወቅት ለአባላት ተመላሽ አይሆንም!
  • የአንድ ዕጣ ዋጋ 1000.00 ብር ሲሆን አንድ አባል መግዛት ያለበት ዝቅተኛ የዕጣ መጠን አንድ ነው።
  • አንድ አባል በጠቅላላ ጉባሌ ተወካይ አባላት አንዲሸጥ ከተወሰነው የዕጣ መጠን ከ10 በመቶ በላይ ድርሻ ሊኖረው አይችልም።
  • በኅብረት ሥራ ማኅበሩ የዕጣ እና ቁጠባ ምጥጥን መሠረት አንድ አባል በየጊዜው 1፡3.5 ዕጣ መግዛት ይጠበቅበታል።

ጆሽዋ ቁጠባና ብድር አድራሻ

ዋና መሥሪያ ቤት፦ ኦሎምፒያ ኤቢሲ ትሬዲንግ አጠገብ 40 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር፦
  • +251 115 58 44 14
  • +251 115 58 44 15
  • +251 115 58 44 16
  • +251 115 58 44 18
  • +251 115 58 29 70
ቅርንጫፍአድራሻስልክ ቁጥር
ፒያሳ ቅርንጫፍ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ፣ ሀሮን ታወር / ኤሊያና ሆቴል ፊት ለፊት+251 993 53 15 30
+251 930 05 06 87
ጎተራ ቅርንጫፍ ጎተራ ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት፣ ንግድ ባንክ ያለበት ሕንጻ ላይ አንደኛ ፎቅ+251 114 70 72 11
+251 144 70 21 99
ዋና መሥርያ ቤትኦሎምፒያ፣ ኤቢሲ ትሬዲንግ አጠገብ 40 ሜትር ገባ ብሎ+251 115 58 44 14
+251 115 58 44 15
+251 115 58 44 16
+251 115 58 44 18
+251 115 58 29 70
አየር ጤና ቅርንጫፍ አየር ጤና፣ ሳሚ ካፌ ጎን ህብረት ባንክ ሕንጻ+251 113 69 41 97
+251 113 69 39 78
መገናኛ ቅርንጫፍከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ላይ ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት፣ ታላቁ ተልዕኮ ሕንጻ ላይ+251 116 66 11 02
+251 116 66 09 87
ልደታ ቅርንጫፍ ልደታ ቤተክርስትያን ፊት ለፊት አዋሽ ባንክ ሕንጻ ላይ+251 115 57 38 91
+251 115 57 40 92

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ጆሽዋ ሁለገብ ኃ/የተ/የኅ/ሥ/ማ በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …