መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማኅበር
metemamen-logo

መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማኅበር

መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም ከብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት ሁሉንም የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በተለይም ሴቶችና ወጣቶች ለማገልገል የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ባሁኑ ወቅት በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ሕዝቦች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጠቅላላው 29 ቅርንጫፎችና 4 ንዑስ ቅርንጫፎች ያሉት ተቋም ነው። ተቋሙ የኅብረተ ሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ህይወት ለመለወጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡ ማኅበሩ ላለፉት ዐሥራ ስምንት ዓመታት ደንበኞቹን በማገልገል ላይ ይገኛል ወደፊትም አገልግሎቱን በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች ለማስፋፋት አቅዶ እየሠራ ይገኛል።

  • የእርሻ ብድር፦ ለእርሻ ሥራ የሚውል ደንበኞች በቡድን ወይም በግል የሚወስዱት የብድር አይነት ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ ብድሩ ይመለሳል።
  • ጥቃቅን የሴቶች ብድር፦ ሴቶች በቡድን ተደራጅተው ለጥቃቅን ንግድ ሥራዎች የሚወስዱት የብድር ዓይነት ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ ብድሩ ይመለሳል።
  • የሠራተኞች ብድር፦ ለመንግሥትና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች በደመወዝ ዋስትና የሚሰጥ ብድር ሲሆን ብድሩ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ የከፈላል።
  • የሴቶች ብድር፦ ለሴት ሥራ ፈጣሪዎች በንብረት ዋስትና በተመጣጣኝ ወለድ ከ1-3 ዓመት ድረስ የሚቆይ እስከ 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር ድረስ የሚሰጥ ብድር ዓይነት ነው።
  • ለግለሰብ የሚሰጥ ብድር፦ በንብረት ዋስትና ለንግድ ሥራ በግል ከ1-4 ዓመት ድረስ የሚቆይ እስከ 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር ድረስ የሚሰጥ ብድር ዓይነት ነው።
  • ዋሽ ብድር፦ የውሃ መስመር ለማስገባት፣ መጸዳጃ ቤት ለማሠራት፣ የውሃ ማጣሪያና ማጠራቀሚያ ለመግዛት የሚውል የብድር ዓይነት ነው።
  • ሶላር ብድር፦ በፀሓይ ኃይል የሚሠሩ የኃይል ምንጭ ምርቶችን ለመግዛት የሚሰጥ ብድር ዓይነት ነው።
በደሞዝ ብድር ለመውሰድ የሚያስችል መጠን
ቁጥርደሞዝየሚችለው ብርቁጠባ (10%)ያገልግሎት ክፍያ (4%)የደብተርድምር
15,000-5,50040,00040001600405,640
26,00050,00050002000407040
37,00055,00055002200407740
48,00065,00065002600409140
59,00075,000750030004010540
610,00080,000800032004011240
711,00090,000900036004012640
812,000100,0001000040004014040
913,000110,0001100044004015440
1014,000115,0001150046004016140
1115,000125,0001250050004017540
1216,000135,0001350054004018940
1317,000140,0001400056004019640
1418,000 Above150,0001500060004021040
  • የደብተር ቁጠባ፦ ተበዳሪ የሆኑና ያልሆኑ ደንበኞች በተሻለ ወለድ በማንኛውም ወቅት ገንዘባቸውን በማስቀመጥ በፈለጉት ጊዜ ወጪ የሚያደርጉት የቁጠባ ዓይነት ነው።
  • የሳጥን ቁጠባ፦ የድርጅቱን የቁጠባ ሳጥን በነጻ በመውሰድ የሚቆጥቡበትና ውድ ጊዜአቸውን ሳያባክኑ ባሉበት ቦታ የድርጅቱ ሠራተኞች በመገኘት በተቀመጠው መመርያ መሰረት በሕጋዊ ደረሰኝ ገንዘቡን የሚቀበሉበት የቁጠባ ዓይነት ነው።
  • የተቋማት ቁጠባ፦ ሕጋዊ እውቅና ያላቸው የግልና የሕዝብ ተቋማት፤ ማኅበራትና ድርጅቶች የሚቆጥቡት የቁጠባ ዓይነት ነው።
  • መተማመን (ልዩ) ቁጠባ፦ ይህ የቁጠባ ዓይነት በማንኛውም ጊዜ ወጪ አድርገው ሊጠቀሙበት የሚችሉት የገንዘብ መጠን የሚፈቅድ ከመሆኑም በላይ እንደሚቀመጥበት ጊዜ ብዛት በስምምነቱ መሠረት ከመደበኛው ቁጠባ የተሻለ ወለድ ያስገኛል።
  • የጊዜ ገደብ ቁጠባ፦ በጊዜ የተገደበ ቁጠባ ሆኖ እንደ ገንዘቡ መጠንና እንደሚቆይበት ጊዜ የወለዱ መጠን ለድርድር ክፍት የሆነና ንግድ ባንኮች ከሚሰጡት የቁጠባ ወለድ በላይ የሚገኝበት የቁጠባ ዓይነት ነው።
  • የህጻናት ቁጠባ፦ ልጆችና ወላጆች የቁጠባ ባህል እንዲያዳብሩና ወደፊት ለልጆች ከፍተኛ ትምህርት ወይም የራሳቸውን ሥራ መሥራት ሲፈልጉ የሚጠቀሙበት በወላጆች ፈቃድ የሚንቀሳቀስ የቁጠባ ዓይነት ሲሆን እንደ ቆይታ ጊዜው የወለድ መጠኑ ዳጎስ ያለና እየጨመረ የሚሄድ ይሆናል።
ተቋሙ ለከተማም ሆነ ለገጠር ደንበኞቹ ተስማሚና ዳጎስ ያለ ጥቅም የሚያስገኙ የቁጠባ አገልግሎቶችን አቅርቧል፤ እንዲሁም ሁሉንም የቁጠባ አገልግሎቶች ባሉበት ቦታ ተገኝቶ ይሰጣል።
  • እድሜዎ ከ 18 እስከ 60 አመት ከሆነ
  • በሚሠሩበት መሥሪያ ቤት ከስድስት ወር በላይ ከቆዩ
  • የታደሰ ስድስት ወር ያላለፈው ንግድ ፍቃድ ካለዎ
  • ለማስያዣ ቤት፣ ተንቀሳቃሽ መኪና፣ ዋስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለብዎት
  • በሚኖሩበት ቀበሌ ከአንድ ዓመት ባላይ መቆየትዎን የሚመሰክር የታደሰ መታወቂያ
ቅርንጫፍስልክ ቁጥር
ዋና መስሪያ ቤት ቦሌ ወሎ ሰፈር0113 69 87 12፣ 0113 69 82 52፣ 0114 70 68 67
ቦሌ ቅርንጫፍ0118 29 85 11
መካኒሳ ቅርንጫፍ0113 69 87 39
ጉለሌ ቅርንጫፍ0111 54 66 32
አዲስ ከተማ0112 73 53 66
የካ0116 68 73 80
ሞጆ ቅርንጫፍ0222 36 34 40
አርሲ ሮቤ ቅርንጫፍ0224 43 03 09
አርሲ ነጌሌ ቅርንጫፍ0461 16 20 08
አሰላ ቅርንጫፍ0223 31 57 91
ዝዋይ ቅርንጫፍ0464 41 22 60
ደንቢ ዶሎ ቅርንጫፍ0575 55 19 31
ሁሩታ ቅርንጫፍ0223 34 00 36
መቂ ቅርንጫፍ0228 18 05 34
አዳማ ቅርንጫፍ0221 12 98 72
ሻሸመኔ ቅርንጫፍ0462 11 50 07
ወልቂጤ ቅርንጫፍ0118 30 60 23
ወሊሶ ቅርንጫፍ0118 81 31 13
ኢቴያ ቅርንጫፍ0223 35 03 81
ኦጎልቾ ቅርንጫፍ0224 75 02 42
ወላይታ ቅርንጫፍ0461 80 40 88
እምድብር ቅርንጫፍ0113 31 08 11
አለም ጤና ቅርንጫፍ0221 150381
ሆሳዕና ቅርንጫፍ0468 55 91 86
ቦዲቲ ቅርንጫፍ0468 95 81 83
ስሬ ቅርንጫፍ0223 30 06 66
ሳጉሬ ቅርንጫፍ0223 381695
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 21304፣ ኮድ 1000 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው መተማመን ብድርና ቁጠባ ተቋም አክሲዮን ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።  

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …