ታደለ ሱልጣን እና ጓደኞቻቸው የእንጨት ሥራ ሽርክና ማኅበር የተመሠረተው በ2011 ዓ.ም ግንቦት ወር መጨረሻ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሁለት ዓመት ሆኖታል። አላማው ሠርቶ ለመለወጥ እና የሥራ እድል በመፍጠር ለሌሎችም የሥራ እድል ማመቻቸት መሆኑን ከመስራች አባላት መካከል አንዱ የሆነው አቶ ታደለ የሺ በላይ ገልጸዋል። አቶ ታደለ ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ከቤተሰባቸው ጋር መሥራታቸው እንዲሁም ሰባት አመታትን በእንጨት ሥራ ያዳበሩት ልምድ ቢዝነሱን ሲጀምሩ ትልቅ እገዛ አድርጎላቸዋል። አቶ ታደለ ወደ እንጨት ሥራ እንዴት እንደገባ ሲናገር ትምህርቱን እንደጨረሰ ከቤተሰቡ ጋር የእንጨት ሥራ አየሠራ የተወሰነ ልምድ ካገኘ በኋላ ሰባት አመት ተቀጥሮ ከዚያም የብቃት ማረጋገጭ ፈተና (COC) ተፈትኖ በማለፉ ይህንን ኢንተርፕራይዝ ከአራት አባላት ጋር መሠረተ። የድርጅቱ መሥራች አባላት (አቶ ታደለን ጨምሮ) አምስት ሲሆኑ ሦስት ግዜያዊ ሠራተኞች አሉ። በአሁኑ ወቅት ሌሎች ቋሚ ሠራተኞች የሉም።
ታደለ ሱልጣን እና ጓደኞቻቸው የእንጨት ሥራ ሽርክና ማኅበር የሚያመርታቸው ዋና ዋና ምርቶች
- አልጋ
- ሶፋ
- ቁም ሳጥን
- የተለያዩ ኪችችን ካብኔቶቸ፣
- የቤት በር
- ሌሎችም የእንጨት ሥራዎች ይሰራል።እነዚህን ምርቶች ለእንድ ጅምላ ተረካቢ ያስረክባሉ። እንዲሁም እንደደንበኛው ፍላጎት በዛትም በነጠላም ያመርታሉ።
ምሥረታ እና እድገት
ሥራ ሲጀምሩ የተከተሉት የሠራር መንገድ ለአካባቢው ነዋሪ የተለያዩ የእንጨት ውጤቶችን በመሸጥ ቀጥሎም የተለያዩ ሱቆችን እየሄዱ በማናገር ለነሱ በማስረከብ ነበር። ቀጥሎም የተለያዩ የጅምላ ተረካቢዎችን በማናገር ሥሩ እና ሥራችሁን እናይላችሁዋለን በማለት የምርቱን ውጤት በማየት እየተደሰቱ ይወስዳሉ። በአሁኑ ወቅት እቃ ከመቼውም ጊዜ በላይ በጣም በመወደዱ ሥራውን በጣም እስቸጋሪ አድርጎታል። ለዚህም መፍትሔ ሥራ ሲወስዱ ባላቸው ጥሬ እቃ መሰረት የዋጋ ተመን በማውጣት መፍትሔ ሊያገኙ ችለዋል።
ድርጅቱ ካጋጠሙት ችግሮች መካከል የሥራ ቦታ ጥበት ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታት የምርት ማሳያ ሱቅ ያስፈልጋል ወደሚል መፍትሔ መጥተዋል። ነገር ግን ቅድሚያ የሚሰጠው አስፈላጊ ማሽኖችን ሟሟላት ስለሆነ በአሁኑ ግዜ ትኩረታቸው እዛ ላይ ነው። ”ነገር ግን የቦታ ጥበትም አሳሳቢ ነው ምክያቱም ስራው ተሰርቶ ለደንበኞች ስለማይደርስ ይህ ደግሞ እቃው በጊዜ ባለመሽጡ እንዲበላሽ እና ለአቧራ ስለሚጋለጥ መፈታት ይኖርበታል” ይላሉ የድርጅቱ ኃላፊ። ይህንን ችግር ለመፍታትት ከሚመለከተው አካል ጋር እየተነጋገሩ ይገኛሉ። በራሳቸው ተከራይተው ለመሥራት ቢያስቡም ማሽኖችን ማሟላት እስፈላጊ እና ቅድሚያ እንደሚሰጠው ስላመኑበት በአሁን ግዜ ማሽኖች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የኮቪድ ተፅዕኖ
የኮሮና ወረርሽኝ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደ ነበረው ከዚሀም የተነሳ ሥራው በጣም እንዳቀዘቀባቸው ገልዋል። ይህም ሥራውን እንደጀመሩ መከሰቱ ይበልጥ ፈታኝ አድርጎት ነበር። ነገር ግን ተስፋ ባለመቁረጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ሳይዘናጉ መቀጠላቸው እንደጀማሪ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል። ሥራ ሲጀመር ከእግዚአብሔር ጋር በራስ መተማመን እና ጠንካራ ስነ-ልቦና ጠቃሚ ነው። “የራስ ሥራ መሥራት በሰዓት ሳትገደብ ረዥም ሰዓት ትሠራለህ። በማለዳ ሥራ ትጀምራለህ፤ ማታ አምሽተህም ትወጣለህ። ይህም ለሥራው መሳካት ትልቅ አስተዋፅዖ አለው” ሲሉ አቶ ታደለ ገልፀዋል።
ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት፣ ምክር
ምርት የማምረት አቅማቸውን በተመለከተ ለተረካቢ ከዐሥራ አምስት እስከ ሃያ አልጋ እስከ ሦስት ሳምንት በሚፈጅ ጊዜ ውስጥ የማምረት አቅም አላቸው። በድርጅቱ የሥራ ዘመን ከመቶ ሀምሳ በላይ ሥራዎችን አጠናቀዋል። አሁንም ሥራ አለ፣ ነገር ግን የማቴሪያል ዋጋ መወደድ በጣም አስቸግሮናል ይላሉ አቶ ታደለ። ይህንን ለመፍታት የተወሰነ ሥራ ሠርተው የማሳያ ሱቅ ለመክፈት ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በአምስት ሺህ ብር የተጀመረ ሥራ አሁን መቶ ሺህ ብር የሚደርስ ሀብት አፍርቷል።
እቅዳቸው ከአምስት እመት በኋላ ድርጀቱን አሁን ካለበት ጥቂት ደንበኞ በማሳደግ ብዙ ደንበኞችን ማፍራት እና ወደ ተሻለ ደረጃ ማደግ እንዲሁም ለሌሎች ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር ነው።
አሁን ባለው የገበያ ሁኔታ በ’ከፍታ’ በኩል የሚሰጠውን የ2merkato የመረጃ አገልግሎት በቴሌግራም እየተጠቀሙ ነው፤ በቅርቡ የቦታውን ችግር ሲፈታ እና ማሽኖች ሲሟሉ የ2merkato ጨረታ አገልግሎት ለመጠቀም እቅድ አላቸው ።
የራሱ ቢዝነስ ያለው ሰው ሥራውን ማክበር አለበት፣ ከሰው ጋር በመግባባት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በትእግስት በመፍታት ሥራውን መሥራት መቻል አለበት። በማኅበር ሥራ ሲሠራ መቻቻል በጣም ያስፈልጋል፤ በሥራ ላይ ግጭት ሊኖር ይችላል ስለዚህ መደማመጥና ትእግስት ያስፈልጋል ብለው ይመክራሉ አቶ ታደለ።