መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ቴዎድሮስ፣ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት

ቴዎድሮስ፣ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት

ቴዎድሮስ፣ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ የተመሠረተው በ2008 ዓ.ም መጨረሻ ሲሆን፤ በጥሩ ሁኔታ ምርት የማምረት ሂደት የጀመረው በ2009 ዓ.ም ነው። ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ቴዎድሮስ ይሉ እና በአራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ ሲመሰረት ጠንካራ እንዲሆን ያደረገው ሁሉም የድርጅቱ መሥራች አባላት በአንድ የእድሜ ክልል እና የኢንጂነሪንግ ትምህርት ምሩቅ መሆናቸው ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ገልጸዋል የድርጅቱ መሥራች አባል አቶ ቴዎድሮስ።

ቴዎድሮስ ኤልያስ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ አጠቃላይ የእንጨት እና የብረት ሥራዎችን የሚሠራ ሲሆን ድርጅቱ ከሚያመርታቸው ምርቶች መካከል:-

  • ለመኖሪያ ቤት ለድርጅቶች የሚሆኑ ትንንሽ ኩርሲዎች(ሶፋዎች)
  • ለሻይ ቡና የሚሆኑ ወንበሮች
  • የተለያየ መጠን ያላቸው ሶፋዎች
  • ትልልቅ የውስጥ እና የውጭ የብረት በሮች
  • የእንጨት ‘ታንቡራተር’ በሮች  እና መስኮቶች
  • ለፎቆች በእንጨት እና በብረት የሚሰሩ የእጅ መያዣዎች (መደገፊያዎች)
  • የኪችን ካቢኔት

ምሥረታና ዕድገት

ድርጅቱ ሲመሰረት አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልገው ካፒታል አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር (ብር 1,500,000) ነበር፤ በወረዳው በብድር መልክ የተመቻቸለት ግን አምስት መቶ ሺህ ብር (ብር 500,000) ነበር። ይህንንም ገንዘብ በአግባቡ በመጠቀም በጣም አስፈላጊ እና ወሳኝ ለሚባሉ ማሽኖች ቅድሚያ በመስጠት ድርጅቱ ተመሠረተ።

አቶ ቴዎድሮስ ወደ እዚህ ሥራ እንዴት ሊገቡ እንደቻሉ እንዲህ ሲሉ አስረድተዋል። ሁሉም የድርጅቱ መሥራች አባላት የኢንጂነሪንግ ትምሕርር ምሩቅ ሲሆኑ አባላቶቹ የራሳቸው(መሥራት የሚፈልጓቸው) ፕሮጀክቶች ነበሩ እነዚህን ፕሮጀክቶች ለማሳካት ብለው ነው እንግዲህ ድርጅቱን የመሠረቱት። ሀሳባቸውም የተለያዩ ማኅበረሰቡን የሚጠቅሙ የፈጠራ ውጤቶች ናቸው። ለምሳሌ የአቶ ቴዎድሮስ ሀሳብ የነበረው ሁሉም ሰው በቤቱ በትንሽ ወጪ የራሱን ዘይት በቤቱ ማምረት የሚችል ማሽን መሥራት ነበር። ይህም አገሪቱ ለዘይት የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ያስቀራል ቀጥሎ በአሁን ወቅት ለጤና ጎጂ የሆኑ የዘይት ምርቶች እየተሰራጩ ስለሆነ ይህንንም በመቀነስ ሁሉም ሰው በቤቱ ዘይት በጥራት እንዲያመርት የሚያደርግ የፈጠራ ውጤት ነው በማለት  አቶ ቴዎድሮስ አስረድተዋል። ነገር ግን የተሰጠው በጀት ትንሽ በመሆኑ በቅድሚያ ራስን ማጠንከር ስላለባቸው ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ምርቶች ማምረት ጀምረዋል።

ድርጅቱ እንዴት ጠንክሮ ሊቀጥል እንደቻለም ሲያስረዱ የድርጅቱ መስራች አባሎች ከመመረቃቸው በፊት እንዳንድ ሥራዎችን በበጎ ፈቃደኛነት በነጻ ሲሠሩ መቆየታቸው እና ተመርቀው እንደወጡም በመከፋፈል አንድ ሰው የእንጨት ሥራ አንድ ሰው የብረት ሥራ አንድ ሰው ደግሞ የሶፋ ሥራ በነፃ እየሠሩ ሥራውንም ሲማሩ ከቆዩ በኋላ ሁሉም የተማሩትን እውቀት አንድ ላይ በማድረግ እራስ በራስ በመማማር እና በመደጋገፍ ጥሩ ደረጃ ላይ ሊደርሱ ችለዋል። ሁሉም ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው በመሆኑ እና አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ስላላቸው ነው ድርጅቱ ዘላቂ ሊሆን የቻለው።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

ድርጅቱ በቀን ከሦስት እስከ አምስት ሶፋ የማምረት አቅም አለው። ይህንን ስኬት ለማሳካት “ዋናው ነገር ትምሕርት ነው፤ መሬት ላይ አይወርድም እንጂ ለሁሉም ነገር ትምሕርት በቂ ነው። በትምሕርት በቂ እውቀት ማግኘት ይቻላል የሀገራችን ሁኔታ ሆኖ በቂ ጥሬ እቃ አቅርቦት ጉድለት አለ እንጂ በትምሕርት ደፍሮ በመግባት ውጤት ማምጣት ይቻላል።”በተጨማሪ በወረዳ  የሚሰጡ ሥልጠናዎች ትልቅ አስተዋጽዖ እንዳላቸው አቶ ቴዎድሮስ አክለዋል።

ድርጅቱ ጠንክሮ በመሥራቱ የሚከተሉትን ውጤቶች ሊያገኝ ችሏል። ወደ ስምንት መቶ ሺህ ብር ካፒታል ማፍራት የቻለ ሲሆን በተጨማሪ የአባላቶቹ ኑሮ ተሻሽሏል። ለሌሎች ዜጎችም የሥራ አድል መፍጠር ችሏል። አዳዲስ ማሽኖት በመጨመር እና እንዳንድ ማሽኖችን በማዘመን (Modify) በማድረግ እየተጠቀም ይገኛል። ጥቂት የማይባሉ ደንበኞችንም ማፋራት ችሏል። እንዲሁም በመንግሥት በኩል በመጣ ሥራ የኮንዶሚኒየም ሥራዎችን በሚገባ በጥራት በማጠናቀቅ አስረክቧል። ለሰባት ቋሚ እና ለአራት ጊዜያዊ ሰራተኞች የሥራ እድል መፍጠር ችሏል።

የኮቪድ ተጽዕኖ

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ድርጅቱ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። ከአሥራ አምስት ቀን እስከ አንድ ወር ድረስ እንቅስቃሴ አልነበረም ስለዚህ ድርጅቱ ተዘግቶ ነበር፤ ሠራተኞችም አልነበሩም። ሥራ ሲጀምሩ ደግሞ ነገሮች በሙሉ እንደ አዲስ እንደ መጀመር ነው የሆነው ማንሰራራት በጣም ከባድ ነበር። ብዙ ደንበኞችም ከቤት አይወጡም ወረርሽኙ ንክኪን ስለሚከለክል ሰው እንኳን ሶፋ ሊገዛ በጣም አስፈላጊ የሚባሉትን ነገሮች ራሱ አቆሞ ስለነበር የነበረው ሁኔታ በጣም ከባድ ነበር። ከኮቪድ በኋላም ጠንካራ የሥራ እና የመለወጥ ፍላጎቱ ስላለ እንደ አዲስ በመፍጨርጨር ነው ወደ እንቅስቃሴ የገባው።

ቴክኖሎጂ መጠቀም ከምንምን በላይ ጊዜን መግዛት ያስችላል። “ጊዜን በሳንቲም መግዛት እንደማለት ነው። ለምሳሌ  ‘ታንቡራተር’ በር ታሽጎ  ሳምንት ይፈጃል በቴክኖሎጂ ግን አሁን በሰላሳ ደቂቃ ያደርሳል። ምን ያህል ጊዜ አተረፍን ማለት ነው ስለዚህ ጊዜ ገዛህ ማለት ከሁሉም ልቀሀል ማለት ነው” ብለው ስለ ቴክኖሎጂ ጥቅም ገልፅዋል።

ድርጅቱ አብዛኛውን ምክር የሚያገኘው ኢንተርኔትን በመጠቀም ሲሆን እንዲሁም 2merkato.com በሚሰጠው የከፍታ አግልግሎት ላይ የሚወጡ ልምድ እና ተሞክሮዎችን በመከታተል ብዙ ነገር ሊማር ችሏል። ከፍታ እየሠራው ያለው ሥራ በመከታተል አዳዲስ ነገሮችን ተምረዋል። “ይህ ደግሞ እንደ ምክር ነው የግድ ሰው ብቻ ማናገር አይደለም በዚህ መድረክ መማማር ይቻላል” ብለዋል አቶ ቴዎድሮስ። የከፍታን አግልግሎት ከከፍታ ስልክ ተደውሎላቸው ነው ያወቁት።

ምክር እና እቅድ

ድርጅቱ በጣም የተጠቀመበት ነገር ኢንተርኔትን በመጠቀም የተለያዩ ሥራዎችን ከአባላቱ የፈጠራ ችሎታ ጋር በመጨመር በድፍረት ለየት እና ወጣ ያሉ ሥራዎችን ለመሥራት በመሞከሩ በጣም አስደሳች ውጤት ሊያመጣ ችሏል። ተጠቃሚ ወዶት በእጥፍ ዋጋ እንውሰድ ያሉ ደንበኞችም ነበሩ። እንዲሁም በአዲሱ ዲዛይን ሥራ እንዲሠራላቸው ያዘዙም ደንበኞች ነበሩ። ይህ የድፍረት ውጤት ነው። ስለዚህ የዚህን ውጤት በመመልከት የተለያዩ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችን እንዲሰሩ መነሳሳትን ፈጥሎላቸዋል።

አዲስ ወደ ዘርፉ የሚሰማሩ በሥራው(በሙያው) ከነሱ የቀደሙትን ማማከር ሁለተኛ ደግሞ በቃለ ጉባዔ ወስኖ ለድርጅቱ ውሳኔ ሕግ እና ደንብ መገዛት በጣም አስፈላጊ ነው። እነዚህ ነገሮች በሚገባ ከተገበሩ ውጤታም መሆን ይቻላል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል።

ድርጅቱ ወደፊት አሁን እየሠራቸው ያሉትን ትንንሽ ነገሮችን ወይም አሁን ለሰው የሚሠራውን ሥራ በሀገር ደረጃ የታወቀ በማድረግ ታዋቂ መሆን እና ደንበኛ ራሱ ሥራውን ፈልጎ እንዲጠቀም ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

አቶ ቴዎድሮስ በቦሌ ክ/ከተማ ላሉት እንደ ወንድም እንደ አባት አይዞአችሁ እያሉ የደገፏቸውን አቶ ሚሊዮን እና እንዲሁም አቶ አማን እና አቶ ተስፋዬን፤ አጠቃላይ ደንበኞቻቸውን በድርጅታቸው ስም አመስግነዋል።

 

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …