መነሻ / የቢዝነስ ዜና / መንገዶች ባለሥልጣን በ10 ዓመታት የኢትዮጵያን ወረዳዎች ሁሉ በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት አቅጃለሁ አለ

መንገዶች ባለሥልጣን በ10 ዓመታት የኢትዮጵያን ወረዳዎች ሁሉ በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት አቅጃለሁ አለ

በመጪዎቹ 10 ዓመታት ሁሉንም የኢትዮጵያ ወረዳዎች በአስፋልት መንገዶች ለማገናኘት እቅድ መያዙን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ። ከዚህም በተጨማሪ ከጎረቤት አገራት ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ግንባታ ለማከናወንም መሪ እቅዱ ትኩረት እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ላይ እየተወያየ በሚገኘበት መድረክ ላይ እቅዱን አቅርቧል። ለሦስት ቀናት በሚቆየው ውይይት ላይ የ10ሩ ተጠሪ ተቋማት እቅድ እየቀረበ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

የመሪ ልማት እቅዱ ውይይት በተጀመረበት በዛሬ እለትም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በአገሪቱ ያሉ ሁሉንም ወረዳዎች በአስፋልት መንገድ ለማገናኘት፣ እንዲሁም ወደ ጎረቤት አገራት ከተሞች የሚደረግን ጉዞ የሚያቀላጥፍ 21 መንገዶች ግንባታ ለማከናወን ማቀዱን አስታውቋል።

በዚህም በዘርፉ ለ3.5 ሚሊየን በላይ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የመንገድ ዘርፉ ለኢኮኖሚው ትልቅ ድርሻ ያላቸውን የግብርና፣ የነዳጅ፣ የቱሪዝም እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚደግፍ ሥራ ትኩረት እንደሚሰጠው ተገልጿል።

የመሪ የልማት እቅዱ ውይይት ለፕላን ኮሚሽን ግብረ መልስ ግብዓት እንደሚሰበሰብበት ተነግሯል።


የዜና ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …