credit-and-saving

ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር

ተደራሽ ማኅበረ ሰብ አቀፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር “ትንሽ ቆጥበው ትልቅ ይሁኑ” የሚል መሪ ቃል ይዞ የተመሠረተ ተቋም ነው።

ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዐላማ

ራዕይ

በጋራ ሆነን እንደ ቤተ ሰብ በመሥራት ማኅበረ ሰብ አቀፍ ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ተቋም በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍ የዳበረ ኅብረተ ሰብ ፈጥሮ ማየት ነው።

ተልዕኮ

ኅብረተ ሰብን በማነቃቃትና በማስተባበር ዕውቀትንና ወቅቱ የሚፈልገውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በፍላጎት ላይ የተመሠረተ አባልነትና ኅብረት በመፍጠር አስተማማኝ የሆነ የፋይናንስ/የገንዘብ አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ

ዓላማ

 • ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ተቋም መፍጠር እና ባንክ ነክ አገልግሎት መስጠት
 • ቁጠባ የሥልጣኔ መገለጫና የእድገት መሠረት መሆኑን ማስተማር
 • የኅብረት ሥራ ማኅበሩ የሚሰጠው የብድር አገልግሎት ለአባላት ሆኖ አንደስፈላጊነቱ ለመሰል አቻ ኅብረት ሥራ ማኅበራት መስጠት
 • ኅብረተ ሰቡን ኋላ ቀር ከሆኑና ለብዝበዛ ከሚያጋልጡ አራጣ አበዳሪዎች ማላቀቅ
 • ኅብረት ሥራ ማኅበሩ የሚሰጠው ተቀዳሚ የብድር አገልግሎት እለታዊ የፍጆታ ችግር ለማስወገድ ሳይሆን አባላቱ በየጊዜው ኑሮአቸውን ለማሻሻል ለሚያደርጉት ልዩ ልዩ ጥረት እገዛ ለማድረግ ይሆናል
 • የብድሩ ዐቢይ ዐላማ ከአባላት ከፍተኛ ወለድ በማሰባሰብ ትርፍ ለማግኘት ሳይሆን አባላት ጠቀም ያለ ገንዘብ አግኝተው ላቀዱት ዐላማ እንዲያውሉትና ክፍያውም ሳይሰማቸውና በበጀታቸው ላይ ተጽዕኖ ሳይፈጥር ከፍለው የሚጨርሱበትን መንገድ ለማመቻቸት ይሆናል
 • የአባላት ኢኮኖሚያዊ ማኅበራዊ ሕይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ለማድረግና ይህም እድገት ቋሚና ዘላቂ እንዲሆን ጥረት ማድረግ
 • ለኅብረት ሥራ ማኅበሩ የሚያስፈልጉ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ማፍራት ማስተዳደር
 • የአባላትን ቁጥር በመጨመር ለብድር አገልግሎት የሚውል የኅብረት ሥራ ማኅበሩን የገንዘብ አቅም ማሳደግ
 • ከተመሳሳይ ገንዘብ ተቋም ጋር ዩኒየን/ፌዴሬሽን አባል መሆን ዕጣዎችን መግዛት እና ቁጠባዎችን መቆጠብ
 • ኅብረት ሥራ ማኅበሩ በተቻለ መጠን ከባንክ የብድር ወለድ ባነሰ ስሌት አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ያደርጋል
 • ሌሎች የገቢ ምንጮችን በመፍጠር በኢንቨስትመንትና ፕሮጀክቶች አባላትን ያቀፈ የአክስዮን ማኅበር በመመሥረት የአባላትን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግ

ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

 • መደበኛ ቁጠባ (Compulsory Saving)
 • የፈቃደኝነት ቁጠባ (Voluntary Saving)
 • የጊዜ ገደብ ቁጠባ (Time Loan Saving)
 • የንግድ፣ የቀን ግቢ ቁጠባ (Trade)
 • የቤት ቁጠባ (Housing Saving)
 • የመኪና ቁጠባ (Car Saving)
 • የሴቶች ልዩ ቁጠባ (Women's Special Saving)
 • የወጣቶች / ተማሪዎች ቁጠባ (Youth Saving)
 • የህጻናት / ልጆች ቁጠባ (Children Saving)
 • የድርጅት ቁጠባ (Institutional Saving)
 • በአዲስ ንግድ ሥራ ለሚሰማሩ እና ለነባር ንግድ ማስፋፊያ
 • ለቤት ግንባታ፣ ግዥና እድሳት
 • ለኮንዶሚኒየም ክፍያ
 • ለመኪና ግዥ
 • ለማኅበራዊ ጉዳይ፣ ለህክምና፣ ለትምህርት፣ ለሥልጠና፣ ለንብረት ግዥና ዕድሳት፣ ለቀለበትና ጋብቻ
 • የምርትና አገልግሎት
 • ለብድር መድኅን ዋስትና
 • የተለያዩ ኑሮን ለማሻሻል ለሚያስችሉ ጉዳዮች
 1. ለ6 ወር በተከታታይ መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ/ች
 2. የጠየቁትን የብድር መጠን አንድ አራተኛ (25%) ያህል የቆጠበ/ች
 3. የብድር ማመልከቻ ላይ በአካል ተገኝተው ማመልከት የሚችሉ
 4. የመደበኛም ሆነ የፈቃደኝነት ቁጠባ መጠን ያህል 100% ያለምንም ዋስትና መበደር ይቻላል።
 5. ለብድሩ ገንዘብ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ማቅረብ የሚችል | ተበዳሪው ተመጣጣኝ ቋሚ ገቢ ምንጭ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
 6. ያገባ/ች፣ ያላገባ/ች የምስክር ወረቀት ማቅረብ፣ ባለትዳር ከሆነ በአካል መገኘት የሚችሉ
 7. የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ኮፒ ከነዋሶቹ ማቅረብ እንዲሁም ባል/ሚስት በአካል በመገኘት መፈራረም አለባቸው።
 8. ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ (ያገባ/ች ከሆነ የባለቤትን ይጨምራል)
 • የብድር አመላለስ በየወሩ ይሆናል።
 • የብድር ወለድ በየወሩ የሚቀንስ (Amortization) ነው።
 • የሴቶች ልዩ ቁጠባ ያላቸውና እየቆጠቡ ላሉ 0.25% የወለድ ቅናሽ አላቸው።
 • በቡድን የተበደሩ በቡድን ተመላሽ ያደርጋሉ።
 1. እድሜ 18 እና ከዛ በላይ የሆነ/ች
 2. እድሜ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ በልጆች ቁጠባ (ያለምንም ክፍያ)
 3. የኅብረት ሥራ ማኅበሩን ዐላማና ደንብ የተቀበለ/ች እና ግዴታና ኅላፊነትን ለመወጣት ቁርጠኛ የሆነ/ች
 4. ገቢ ያለውና ከወር ገቢው ላይ ለመቆጠብና እና/Share ለመግዛት ኅላፊነቱን የሚወጣ
 5. የማይመለስ የመመዝገቢያ ክፍያ መክፈል የሚችል/የምትችል
 6. የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ የመሥርያ ቤት ወይም መንጃ ፈቃድ 1 ኮፒ
 7. ሥስት ጉርድ ፎቶግራፍ
 8. ባሉበት አካባቢ በሂሳብ ቁጥራችን "Narrative" ላይ የአስገቢውን ስም በማስገባት በተመቸ ጊዜ ቢሮ በመምጣት ፎርም በመሙላት ቡክ መውሰድ ይቻላል።
 • አሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ - 1000029243887
 • ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000365891404
 • አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ - 263711
 • አዋሽ ባንክ - 01322744781600
 • ደቡብ ግሎባል ባንክ - 1541106306721
 • አቢሲንያ ባንክ - 96563949
 • ዳሽን ባንክ - 5499323535011
 • እናት ባንክ - 0451128453080001

ተደራሽ የገንዘብ ቁጠባና ብድር አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

ፒያሳ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ፣ ገነት ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕንጻ ዐምስተኛ ፎቅ

ስልክ

 • 0111264139
 • 0118122221
 • 0913276538
 • 0913541997

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ተደራሽ ማኅበረሰብ አቀፍ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …