መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር
ae-logo

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር

ኅብረት ሥራ ማኅበር ማለት ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን ዕውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ ማኅበር ነው።

መቆጠብ መሰሰት አይደለም!!!
ለለውጥ ይቆጥቡ!!!
ለቁም ነገር ይበደሩ!!!

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር የሚሰጠው አገልግሎት

  • ለመሠረታዊ አገልግሎት ብድር
  • መደበኛ ቁጠባ ብድር
  • አስቸኳይ የቁጠባ ብድር
  • የንግድ ብድር
  • ለተሽከርካሪ የቤት እና የንግድ ብድር
  • ለቤት ግንባታ ግዥ እና ዕድሳት ብድር
  • ለመኪና መግዣ እስከ 2 ሚሊዮን ብር ብድር
  • ለቤት መግዣ እስከ 3 ሚሊዮን ብር ብድር
  • ለሴቶች፣ ለታዳጊ ወጣቶችና ለተማሪዎች ልዩ የገንዘብ ቁጠባ ብድር
  • ለአካል ጉዳተኞች እና ለአቅመ ደካሞች የሚሆን ብድር
እንዲሁም አስቸኳይ ለሆኑ ጉዳዮች ፈጣን የብድር አገልግሎት ይሠጣል፤ ማለትም፦
  • ለህክምና
  • ለትምህርት
  • ለኮንዶሚኒየም ቅድመ ክፍያ
  • ለፍርድ ቤት ጉዳይ
  • የብድር ወለድ 14% መሆኑ
  • ለተቀማጭ 10% ወለድ መታሰቡ
  • አባል ከሆኑ ከ3 ወር በኋላ የብድር ጥያቄ መቀበሉ
  • የቆጠቡትን 8 እጥፍ ብድር መስጠቱ
  • እስከ 15 ዓመት የመክፈያ ግዜ ማመቻቸቱ
  • ከ72 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱ
  • ከ2600 አባላት በላይ ማፍራቱ
  • ለሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ብድር በማመቻቸት እንዲበረታቱ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ያለው ፍላጎት
  • እድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
  • ብር 1000 መመዝገቢያ ክፍያ መክፈል የሚችል
  • ብር 500 የአባልነት ግዴታ ቁጠባ መቆጠብ የሚችል
  • የኅብረት ሥራ ማኅበሩን መብትና ግዴታ ለመፈፀም ፈቃደኛ የሆነ
  • ለተማሪዎችና ለታዳጊ ወጣቶች ወርሃዊ ቁጠባ ብር 100
  • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያና 3 ጉርድ ፎቶ በማቅረብ አባል መሆን ይቻላል

የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር አድራሻ እና ስልክ

ዋና መሥሪያ ቤት
  • አድራሻ፦  ከሰሜን ሆቴል ከፍ ብሎ፣ ዳሩሌ ሕንጻ፣ 8ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 801
  • ስልክ፦ 011 812 30 40፣ 011 862 54 53፣ 011 853 22 59
መገናኛ ቅርንጫፍ
  • አድራሻ፦ መተባበር ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 212
  • ስልክ፦ 011 862 50 66
ቀጨኔ ቅርንጫፍ
  • አድራሻ፦ ስምንት ቁጥር ማዞሪያ፣ ዘመን ሕንጻ፣ 4ኛ ፎቅ
  • ስልክ፦ 011 858 22 61

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …