መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ጽጌረዳ ካሳሁን ልብስ ስፌት (ኪያ ዲዛይን)

ጽጌረዳ ካሳሁን ልብስ ስፌት (ኪያ ዲዛይን)

ድርጅቱ የተመሠረተው በወ/ት ጽጌረዳ ካሳሁን 2012 ዓ.ም የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የልብስ ስፌት ሥራዎችን የሚሠራ ሲሆን በዋናነት ግን የአፍሪካ የባህል ልብሶችን ያመርታል።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች

  • ጉርድ ቀሚሶች
  • ታይቶች
  • አጭር ጃኬቶች
  • ቲሸርቶች
  • ቀሚሶች
  • ሸሚዞች
  • የተለያዩ ጋዋኖች

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

ወ/ት ጽጌረዳ ወደ ልብስ ስፌት ሥራ ከመግባቸው በፊት በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ተሰማርተው ሲሠሩ ቆይተዋል። ለምሳሌ በሴቶች የውበት ሳሎን እንዲሁም በአልባሳት ሽያጭ ሥራ ተሰማርተው ነበር። የውበት ሳሎን ሥራው እሳቸው ትምህርት እየተማሩ ስለነበር እንደልብ በሥራው ላይ መገኘት ባለመቻላቸው፣ ብዙም አዋጭ ሳይሆን ሥራውን ለማቆም በመገደዳቸው ምክንያት ነው ወደ ልብስ ሽያጭ ሥራ የገቡት። በዚህም ሥራ ለሁለት ዓመት ቆይተዋል። እናም በሽያጭ ሥራ ውስጥ ሆነው ነበር እንግዲህ የልብስ ስፌት ሃሳብ የመጣላቸው። ምክንያቱም አንዳንድ ደንበኞች የሚፈልጉት ልብስ ወይ ይጠባቸዋል ወይ ደግሞ ይሰፋቸው ስለነበር ይህን አስጠብቢልን ወይም አሰፊልን እያሉ ሲመጡ እሳቸውም የተማሩት ትምህርት የልብስ ዲዛይን ትምህርት ስለሆነ እራሴ ለምን አላመርትም እንዲሁም የልብስ ስፌት ሥራ ስለሚያስደስታቸው ልሞክረው ብለው በአንድ ሺህ ብር መነሻ ካፒታል ኪያ ዲዛይንን የመሠረቱት።

ወ/ት ጽጌረዳ የልብስ ስፌት ሥራ ላይ በአብዛኛው እራሳችውን በራሳቸው በማስተማር ብሎም የሚያስቧቸው ዲዛይኖች ስለነበሩ እንዚህን ዲዛይኖች እራሳቸው ሠርቶ በማውጣት እና በማምረት ተወዳጅነትን አትርፈዋል። እርሳቸውም ምርታቸውን ባዛር ላይ፣ ሄሎ ማርኬት ላይ፣ ጅማ፣ አጋሮ እንዲሁም ሱሉልታ ድረስ በመሄድ እና ከሶሻል ሚዲያ ደግሞ ፌስቡክ እና ቴሌግራም ቻናል በመጠቀም ምርታቸውን ያስተዋውቃሉ።

 

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች ዋጋ እንደሚከተለው ነው

  1. ሸሚዝ፦ 600 – 700 ብር
  2. ጉርድ ቀሚስ፦ 350 ብር
  3. የሴቶች ሸሚዝ፦ 250 ብር
  4. ታይት፦ 400 ብር
  5. የጨርቅ ሱሪ፦ 300 ብር
  6. የአፍሪካ ጉርድ ቀሚሶች፦ 500 ብር
  7. የሴቶች አጭር ጃኬቶች፦ 300 ብር

 

 

የድርጅቱ መሥራች የልብስ ዲዛይን ሙያ ከትምህርት ቤት ከተማሩት ይልቅ ራሳቸውን በራሳቸው ያስተማሩት በጣም የተሻለ እደሆነ ገልፀዋል። ራሳቸውን ማስተማር ሲባል ጥሬ እቃ ከመግዛት ጀምሮ የዲዛይን ንድፍ ሰዎችን በመጠየቅ፣ ኢንተርኔት በመጠቀም፣ ጉግል ላይ በመፈለግ እና በማንበብ እንዲሁም የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን በመከተታል፣ ያዩትንም በመሞከር ነው ራሳቸውን ያሳደጉት። ስለዚህ ቴክኖሎጂ መጠቀም ወሳኝ እንደሆነ ይመክራሉ።

በአንድ ሺህ ብር መነሻ አቅም የተጀመረ ድርጅት አሁን ካፒታሉ ሰማንያ ሺህ ብር ደርሷል። ለሁለት ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ሲሆን ምርት የማምረት አቅሙንም በቀን ወደ ሰላሣ ሸሚዞች ማሳደግ ችሏል። ሥራ ከመጣ ግን ሰዎችን በመጨመር በቀን እስከ መቶ ሸሚዞች በጥራት የማምረት አቅም አለው። ድርጅቱ በአምራችነት ሥራ ከጀመረ ቅርብ ጊዜ ስለሆነ ምርት አምርቶ ለመሸጥ በጣም አስቸጋሪ ነበር። ነገር ግን በታታሪነት በመሥራትና በማስትዋወቅ ጥቂትም ቢሆን ጥሩ ተስፋ እያሳየ እንደሆነ የድርጅቱ መሥራች ገልፀዋል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

የኮቪድ ወቅት በጣም አስቸጋሪ ነበር። ምክንያቱም የሽያጭ ሥራ ስለነበር ያንን ማድረግ ደግሞ አይቻልም ነበር። በተጨማሪ ደግሞ የሰውም ፍርሃት ስለ ነበር ብዙ ሥራ አልተሠራም።

ምክር እና እቅድ

ድርጅቱ ወደ ፊት ማሽን በመጨመር እና ለብዙ ዜጎች የሥራ እድል በመፍጠርእራሱ በሚነድፋቸው ዲዛይኖች ታዋቂ ለመሆን እና የገበያውን ሁኔታ በማየት እና በማጥናት አዋጭ ከሆነ የጥልፍ ሥራ የመጀመር እቅድ አለው።

ወደ ልብስ ስፌት የሚገባ ሰው ለማን ነው የሚያስረክበው? ሁለተኛ ደግሞ ምርት የት እንደሚያገኝ አውቆ ቢገባ መልካም ነው ብለዋል። ለምሳሌ የጨርቁ ዓይነት አለ፤ ይህ መታወቅ አለበት የኪሎ እና የጣቃ የሚባሉ የጨርቅ አይነቶች አሉ እነኝህን ማወቅ እና የደንበኛውን ፍላጎት በሚገባ መገንዘብ ያስፈልጋል ሲሉ ምክራቸውን ለግሰዋል።

የድርጅቱ መሥራች ወደፊት 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት በሚገባ እንደሚጠቀሙ ገልጸዋል።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …