ባለፉት ሶስት ወራት ከማዕድን ዘርፍ ከ178 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ መገኘቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናገሩ። ይህንንም ያሉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የሶስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።
ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዛሬ ካስገኙት ማዕድናት መካከል ወርቅ፣ ታንታለም፣ ኳርትዝ፣ ኢመራልድ፣ ሳፋየር እና እምነበረድ ተጠቃሾች ናቸው።
ወርቅን በተመለከተ በባህላዊ መንገድ ከሚያቀርቡ አቅራቢዎች 2ሺህ 241 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል። በእቅድነት ተይዞ የነበረው 251 ኪ.ግ ወርቅ ለውጭ ለማቅረብ ነበር። ነገር ግን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል የተደረገው የወርቅ ማሻሻያ ዋጋ የወርቅ አቅራቢዎችን በመሳቡ ምክንያት ከታቀደው በ298ነጥብ9 በላይ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል።
የዜና ምንጭ፦ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኦፊሺያል የፌስቡክ ገጽ