መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ
kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ።

ሥልጠናው ያተኮረው ኢንተርፕራይዞቹ በኬር ኢትዮጵያ በተመቻቸላቸው ዕድል የ”ከፍታ” አገልግሎትን ተጠቅመው እንዴት የጨረታ መረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ በተጨማሪም እንዴት አድርገው ድርጅታቸውን፣ ምርታቸውን እና አግልግሎታቸውን እንደሚያስተዋውቁ ነው። ኢንተርፕራይዞቹ “ከፍታ” ፖርታል (kefta.2merkato.com) ስላቀረባቸው መረጃዎች፤ የtender.2merkato.com ወይም 2merkato Tenders ላይ ያሉትን የቢዝነስ ዕድሎች እንዴት በቀላሉ መጠቀም እንደሚቻል፤ በ2merkato የB2B መድረክ አማካኝነት እንዴት የገበያ ትስስር እንደሚፈጠር በዝርዝር ተመልክተዋል። ኢንተርፕራይዞቹ በማኑፋክቸሪንግ (ጋርመንት/ልብስ ስፌት፣ የሻማ ማምረት፣ ሳሙና ማምረት፣ የምግብ ዝግጅት፣ ዳቦ እና ጣፋጭ ዝግጅት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ የእንጨት ሥራ፣ ከሲሚንቶ የሚሠራ የአበባ መትከያ ሥራ፣ የባሕል አልባሳት፣ የጥልፍ ሥራ፣ ዕደ ጥበባት (ቅርጻ ቅርጽ))፤ በከተማ ግብርና (ኮምፖስት ዝግጅት)፤ በአግልግሎት (ኅትመት፣ ጥልፍ ሥራ እና ኅትመት)፤ እና በኮንስትራክሽን (ቴራዞ አምራች) ዘርፎች መሰማርታቸውን ገልጸዋል። በሥልጠናውም ላይ በሚሠሩት ሥራ ዘርፍ የሚወጡ ጨረታዎችን፤ በB2Bው ደግሞ የተመዘገቡ ድርጅቶችን በዝርዝር በማሳየት እንዴት ሥራቸውን ማሳደግ እንደሚችሉ በደንብ ተገንዝበዋል።kefta-care-training-1

ከዚህም በተጨማሪ የዲጂታል ሊትሬሲ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ጥቅሙን የተመለከተ ዐጭር ሥልጠና በ”ከፍታ” ተሰጥቷል።

ይሄ የመጀመርያ ዙር ሥልጠና ሲሆን ለሌላ በሴቶች ለሚተዳደሩ 25 ኢንተርፕራይዞች ሁለተኛ ዙር ሥልጠና በኬር ኢንትዮጵያ እና በ”ከፍታ” ትብብር ይዘጋጃል። ኬር ኢትዮጵያ 50 ኢንተርፕራይዞችን በሁለት ዙር የ”ከፍታ” አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ የ”ከፍታ” ባለቤት ከሆነው ከኢቢዝ ኦንላይን ሶሉሽንስ ኅላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር ውል ተፈራርሞ እየሠራ ይገኛል።

“ከፍታ” በ2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተሟላ መረጃ ለመስጠትና ኢንተርፕራይዞቹን ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዲደርሱ ለማገዝ የተዘጋጀ ፖርታል ሲሆን፤ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢንተርፕራይዞች አግልግሎቱን በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። ኢንተርፕራይዞች ጨረታ እያሸነፉ፣ የገበያ ትስስር እያገኙ ሲሆን በሥልጠናው ላይ የተገኙ ሁለት የኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች የ “ከፍታ” ተጠቃሚ እንደሆኑና በ “ከፍታ” አማካኝነት ጨረታ እንዳሸነፉ፣ የገበያ ትስስርም እንደተፈጥረላቸው ገልጸዋል። “ከፍታ” የተሠራው በ2merkato.com ባለቤት በሆነው ኢቢዝ ኦንላይን ሶሉሽንስ ኅላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እና በኔዘርላንድስ የልማት ድርጅት (SNV)/ ሊዌይ (LIWAY) ፕሮጀክት ትብብር ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

TUC_NSP_2merkato_poster_ad_20221031-04

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የ4 ሳምንት የሙያ ክህሎት ሥልጠናዎች

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማራችሁ ኢንተርፕራይዞች ከቤት እስከ ከተማ የከተማ ማዕከል (The Urban Center) የ4 ሳምንት የሙያ …