የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር

“የኛ ሁሌም የኛ የሁላችንም ነው!!” በሚል መሪ ቃል የሚታወቀው የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚገኙ እና በትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛ የሆኑትን፣ እንዲሁም መካከለኛውን የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በገንዘብ አስተዳደር እና አጠቃቀም እና በተለያዩ ሥልጠናዎች በማገዝ የኑሮና አኗኗር ለውጥን ለማምጣት እና ለመሥራት የተቋቋመ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ማኅበር ነው።

በየኛ የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ሁሌም የአባልነት ምዝገባ አለ።

የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

ራዕይ

ቀጣይነት ያለው የገንዘብ ተቋም በመፍጠር በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ዕሴቶች የዳበረ ኅብረተ ሰብ ለማየት ለሁሉም በሁሉም የተቋቋመ ማኅበር ነው።

ተልዕኮ

የሀገራችንን ኅብረተ ሰብ በማስተባበር ዘመኑ በፈቀደው ሥልጣኔ በመጠቀም የአባላቱን የገንዘብ ቁጠባ እና አቅርቦት አስተማማኝ ማድረግ።

ዓላማ

  • አስተማማኝ ባንክ ነክ አገልግሎቶችን መስጠት
  • የአባላትን የቁጠባ ባሕል ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ
  • ለአባላት ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ማቅረብ
  • አባላት ከገንዘብ ቁጠባና ብድር በተጨማሪ መሠረታዊ የፍጆታ ቁሳቁሶችን በዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ ተጠቃሚ ማድረግ
  • ለአባላት የተለያዩ ስልጠናዎችን ማመቻቸት
  • እገዛ የሚያስፈልጋቸውን የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በተለያየ የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ ማገዝ
  • አባላትን በከፍተኛ ቁጥር በመጨመር አቅሙን ማሳደግ

የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  • የማኅበሩን ዓላማና ደንብ የተቀበለ
  • ዝቅተኛ ክፍያ የሚከፍል ማለትም 1 እጣ 500 ብር ሲሆን 2 እጣ መግዛት የሚችል
  • የመመዝገቢያና ሌሎች ወጪዎችን 700 ብር ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ
  • በየወሩ 400 ብር የግዴታ ቁጠባ ለመቆጠብ የተስማማ
  • የራስዎ የሆነ ድርጅት ባለቤት ይሆናሉ
  • ትርፍ ተካፋይ ይሆናሉ
  • ገንዘብ ለመበደር የራስዎን ድርጅት እጅ እንጂ የሰው እጅ እና ፊት አያዩም
  • የቁጠባ ባሕልዎትን በቀላሉ ያሳድጋሉ

የመደበኛ ቁጠባ

መደበኛ ቁጠባ ማለት አንድ የማኅበሩ አባል የሆነ ሰው በየወሩ 400 ብር የሚቆጥብበት የሂሳብ ደብተር (አካውንት) ሲሆን አባሉ ከማኅበሩ አስካልወጣ ድረስ 400 ብር መቆጠብ አያቆምም። በዓመት 7% ወለድ ይታሰባል። በተጨማሪ ይህን  የሂሳብ ደብተር (አካውንት) ማንቀሳቀስም ሆነ በአንድ ወር ከ400 ብር በላይ መቆጠብ አይቻልም፤ ግን አባሉ ከ400 ብር በላይ መቆጠብ ከፈለገ ወደ ቀጣዩ ወር ይተላለፍለታል።

የፈቃደኝነት ቁጠባ

የፍቃደኝነት ቁጠባ ማለት በአንድ ወር ከ400 ብር በላይ መቆጠብ ለሚፈልጉ አባላት የተዘጋጅ የሂሳብ ደብተር ሲሆን አባላት በፈለጉት ጊዜ ማውጣት ሆነ ማስገባት (ማንቀሳቀስ) ይችላሉ። በዓመት 7% ወለድ ይታሰባል።

የጊዜ ገደብ ቁጠባ

የጊዜ ገደብ ቁጠባ ማለት አንድ የማኅበሩ አባል ከድርጅቱ ጋር ውል ተዋውሎ የሚቆጥበው የቁጠባ ዓይነት ነው። በተጨማሪም ውል ላይ ያለው የጊዜ ገደብ ሳያልቅ ገንዘብ ማንቀሳቀስ አይቻልም። ሆኖም የተባለው ጊዜ ሳይደርስ ውሉን አፍርሶ ገንዘብ ማውጣት የሚፈልግ አባል ሙሉ በሙሉ ወለድ አይታሰብለትም እናም ካስቀመጠው ብር ላይ 10% ተቀንሶ እንዲወስድ ይደረጋል። የጊዜ ገደብ ቁጠባ አገልግሎት ከሦስት ወር እስከ ሦስት ዓመት የብር መጠን ከ500-100,000 ብር ላስቀመጠ ከ7.2%-10% የወለድ መጠን ይከፍላል።
  • የሴቶች ቁጠባ - የወለድ መጠን  7.8%
  • የዓመት በዓል ቁጠባ - የወለድ መጠን 8%
  • የልጆች ቁጠባ - የወለድ መጠን 7.5%
  • የሊስትሮ ሰራተኞች ቁጠባ - የወለድ መጠን 7.5%
  • የታክሲ አገልግሎት ቁጠባ - የወለድ መጠን 7.5%
  • የቤት ሠራተኞች ቁጠባ - የወለድ መጠን 8%
  • ሥራ ማስኬጃ ብድር - የብድር ወለድ 11%፣ የውል ዘመን 3 ዓመት
  • ቤት መሥርያ ማደሻ (መግዣ) - የብድር ወለድ 14%፣ የውል ዘመን 6 ዓመት
  • የመኪና መግዣ - የብድር ወለድ 13%፣ የውል ዘመን 4 ዓመት
  • ለወሊድ የሚሰጥ - የብድር ወለድ 8%፣ የውል ዘመን 3 ዓመት
  • ለሠርግ መሰረጊያ - የብድር ወለድ 9%፣ የውል ዘመን 3 ዓመት
  • ለትምህርት መማሪያ - የብድር ወለድ 9.5%፣ የውል ዘመን 3 ዓመት
  • መግዛት የሚገባውን እጣ የገዛ እና በተከታታይ የቆጠበ
  • መበደር የሚፈልገውን 15% የቆጠበ
  • ለጠየቀዉ ብድር ተመጣጣኝ የሰው ውወይም የንብረት ወይም የዕጣ ዋስትና ማቅረብ የሚችል

የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር፦ አድራሻ እና ስልክ

  • አድራሻ፦ 4 ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ወ/ወ/ክ/ማፊት ለፊት 50ሜ. ገባ ብሎ
  • ስልክ ቁጥር፦ 0943 114300

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው የኛ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው። 

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …