መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / ለሲሚንቶ አቅርቦት እጥረት እና ዋጋ ጭማሪ መፍትኄ
cement-factory

ለሲሚንቶ አቅርቦት እጥረት እና ዋጋ ጭማሪ መፍትኄ

በገበያ ላይ እያጋጠመ ያለውን የሲሚንቶ አቅርቦት እጥረትና ዋጋ ጭማሪ ለመፍታት የአቅርቦት መጠንን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ።

በኢፌዴሪ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አካላት የተመራ ልዑክ በገበያ ላይ የተከሰተውን የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ በአምራች ድርጅቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

ለሁለት ቀናት የቆየው የሥራ ጉብኝት ዋና ዓላማም ለምርት እጥረቱ በምክንያትነት የሚነሱ ጉዳዮችን በተጨባጭ ለማየት፣ በምርት ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ማነቆዎችን ለመለየትና ለችግሮቹ እልባት ለመስጠት፣ የአቅርቦት መጠንን በማሳደግ በገበያ ላይ የሚስተዋለውን እጥርት ለማሻሻል መሆኑን የገለጹት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል ችግሩ በቁጥጥር ብቻ እንደማይፈታ እና አቅርቦት ላይ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የመለዋወጫ እቃዎችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የሚያስችል በቂ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና የመብራት መቆራረጥ ችግሮች በአምራቾቹ የሚነሱ ተግዳሮቶች እንደሆኑ የጠቆሙት ሚኒስትሩ የውጪ ምንዛሬ እጥረቱን ለመፍታት ከውጪ የሚገቡትን እቃዎች በአገር ውስጥ የመተካት (import substitution) ስትራቴጂ መንግስት እየተከተለ በመሆኑ ሀገሪቱ በ 220 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ ወደ አገር ውስጥ ታስገባ የነበረውን የድንጋይ ከሰል ምርት በአገር ውስጥ በመተካት ለዚህ ይወጣ የነበረውን ወጪ ለመለዋወጫ ማዋል የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር የጀመረው በ2011 ሚያዝያ ወር ከመብራት መጥፋትና ፋብሪካዎች በ 50 በመቶ እንዲያመርቱ መደረጉን እና በተያዘው የ2012 በጀት መጋቢት ወር ላይ ለ75 ቀናት ከማምረት መቆጠባችንን ተከትሎ ነው ያሉት የደርባ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሌ አሰግዴ ተወዳዳሪ ድርጅቶችም ከጥገናና ከመብራት መቆራረጥ ጋር ተያይዞ ላለፉት 2 ወራት ማምረት ባለመቻላቸው እጥረቱ እንዲፈጠር ማድረጉንና ለዋጋ ንረቱ ምክንያት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …