መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ በብድር ሊያገኙ ነው

ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ በብድር ሊያገኙ ነው

አዋሽ ባንክ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ ለተለያዩ የማክሮ ፋይናንስ ተቋማት 5.5 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ባንኩ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት (ለአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት) ለማበደር ካቀደው በጀት ውስጥ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ብድር ተጠቃሚ ከሚሆኑ ዘጠኝ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ጋር ባለፈው ሐሙስ ሐምሌ 21 ቀን 2014 ዓ.ም. ተፈራርሟል፡፡

ባንኩ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ለማክሮ ፋይናንስ ተቋማቱ ለመስጠት ያቀደውን ብድር በተለዋዋጭ ውሎችና ሁኔታዎች፣ ማለትም በዝቅተኛ የወለድ ተመኖች፣ ጥብቅ ባልሆነ የመልሶ ክፍያ ውልና ተለዋዋጭ የዋስትና አማራጮችን፣  ማለትም እንደ ንፁህ ብድር (መያዣ የሌለው) በመጠቀም እንደሚያቀርብ ገልጿል።

ለተጨማሪ፦ ሪፖርተር ጋዜጣን ይመልከቱ

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …