መነሻ / የቢዝነስ ዜና / የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ከዛሬ ጀምሮ በሙሉ አቅሙ ማምረት ጀመረ
sheger-bread

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ከዛሬ ጀምሮ በሙሉ አቅሙ ማምረት ጀመረ

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ከዛሬ መጋቢት 7፣ 2013 ዓ/ም ጀምሮ በሙሉ አቅሙ ማምረት ጀመረ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመራ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ፋብሪካው ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ ጎብኝቷል። በጉብኝቱ ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዳቦ ፋብሪካው በዛሬ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ወደ ማምረት እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መደረሡን ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በሚያደርገው ድጎማና የግብዓት አቅርቦት በቀን 900 ሺህ ሲያመርት የነበረው አሁን 1.5 ሚሊዮን ዳቦ ማምረቱ የዋጋ ንረትን በማረጋጋት የበኩሉን አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል። ምክትል ከንቲባዋ ጨምረውም እንደተናገሩት የሸገር ዳቦ ፋብሪካ በከተማችን እና በዙሪያው በሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች የዳቦ ፍላጎት እንዲቀርፍ ታስቦ የተቋቋመ ቢሆንም ፋብሪካው ባለፉት ጊዜያት በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት ባለመግባቱ የዳቦ እጥረትና አጋጥሞት ነበር።

ፋብሪካውን ያጋጠመውን የስንዴ አቅርቦት ውስንነት በመፍታት በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት እንዲገባ ለማስቻል የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት ለሚቀጥሉት ሁለት ወራት የሚያገለግል 100 ሺህ ኩንታል ስንዴ በድጎማ ለፋብሪካው አድርጎለታል። ይሄም ፋብሪካው ምርቱን በማሳደግ በቀን ከ900 ሺ ዳቦ ወደ 1.5 ሚሊዮን ዳቦ እንዲያመርት ያስችለዋል ተብሏል።

ምክትል ከንቲባዋ ምርቱ በትክክል ለዝቅተኛው የሕብረተሰብ ክፍል ጋር ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል በተጠናከረ መንገድ በጋራ ስግብግብነትንና ሕገወጥነት መከላከል ከሁላችም ይጠበቃል ሲሉ አሳስበዋል።

የዜና ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ክፍል የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …