መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ዓላማ እና የሙያ ፍቅር – ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች

ዓላማ እና የሙያ ፍቅር – ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች

ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች የተመሠረተው በ2011 ዓ.ም በአቶ ሰዋሰው ፍቅሬ ነው።ድርጅቱ በቡልቡላ አካባቢ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12  አስተዳደር ሥር የተመሠረተ ቢሆንም በቂ የሆነ የኢንተርፕራይዞች ሼድ በወረዳው ባለመኖሩ ተቸግሮ ነበር። ይህ ችግር ወረዳው ከቦሌ ወረዳ 13 ጋር በገባው ስምምነት መሠረት ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች የሼድ ተጠቃሚ እንዲሆን ያደረገ ሲሆን ይህም ለሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች ሥራ መጠናከር ትልቅ አስተዋጽዖ አንዳበረከተ አቶ ሰዋሰው ገልጸዋል።

ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች አጠቃላይ የቆዳ ውጤቶችን ከድፍን ጫማ በስተቀር በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያመርት ድርጅት ነው።
ሰዋሰው ቆዳ ከሚያመርታቸው ምርቶች መካከል

  • ጃኬት
  • ሳይድ ቦርሳ
  • ላፕቶፕ መያዣ ቦርሳ
  • ትራቭሊንግ ቦርሳ
  • ዶክመንት መያዣ ቦርሳ
  • ክፍት ጫማ፣ ቀበቶ እና ቁልፍ መያዣ ምርቶችን ያመርታል

ምሥረታና ዕድገት

አቶ ሰዋሰው ወደ ቆዳ ዘርፍ ሊገቡ የቻሉበትን ምክንያት ሲገልፁ እሳቸው ሲያድጉበት የነበረው ማደጎ ቤት በመጣ የሥልጠና እድል እሳቸውም የቆዳ ሥራ ስለሚያስደስታቸው የቆዳ ሥልጠና በመምረጥ ሁለት አመት ከስድት ወር ስልጠና ወሰዱ። በትምህርት ላይ ባሳዩት ብቃታቸው በመመረጥ ለስድስት ወር ያህል በጅማ፣ ደሴ እና የተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች እየተዘዋወሩ የአካል ጉዳተኞችን በመደገፍ በማሰልጠን እያስተማሩ እንዲቆዩ እንደል ፈጥሮላቸዋል ነበር። ትንሽ አቅም ሲኖራቸው ተደራጅተው በራሳቸው መሥራት መጀመራቸውን ይገልጻሉ።

ማስተማሩን እንደጨረሱ መርካቶ የጫማ ሥራ በመማር እና በመሥራት ለአንድ አመት የቆዩ ሲሆን ይህም በራሳቸው ሥራውን ለመጀመር ያሚያስፈልጋቸውን አጠቃላይ እውቀት ለመጨበጥ እንዲችሉ እንዳደረጋቸው አቶ ሰዋሰው ገልጸዋል። ለምሳሌ ጥሬ እቃ እቅርቦት የት እንደሚገኝ፣ ዋጋው ስንት እንደሆነ፣ የጥራት አይነቱን እንዴት ማወቅ እንደሚቻል እና አጠቃላይ የቆዳ ነክ ሥራዎች ላይ ልምድ እንዲያዳብሩ እንደረዳቸው ገልጸዋል።

የራስን ሥራ የመጀመር ትልቁ እና ዋናው እርካታ ሌላ ሰው እንዲሠራ ማድረግ መቻል እና ለሌላ ዜጋ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ነው፤ ከዛም ራስን ተጠቃሚ ያደርጋል ይላሉ አቶ ሰዋሰው።

አቶ ሰዋሰው ሥራውን ሲጀምሩ ብቻቸውን በመኖሪያ ቤታቸው በአንድ ማሽን ነበር የጀመሩት። በአሁን ጊዜ ቢዝነሱ ስምንት ማሽኞች እና ስድስት ቋሚ ሠራተኞች እንዲሁም ሥራ ሲበዛ (በዛ ያለ ሥራ ሲኖር) በኮንትራት እንደ ሥራው አይነት እየተቀጠሩ የሚሠሩ ሠራተኞችን ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ሰዋሰው ቆዳ ትልቅ ጥሩ የዶክንት መያዣ ቦርሳ በቀን አስራ አራት ቦርሳ የማውጣት አቅም አለው፤ አሁን ባለው የኮቪድ ተጽዕኖ  ምክንያትት በቀን ሦስት ቦርሳ ይሠራል።

ድርጅቱ ከተመሰረተ የሦስት አመታት ግዜ ያስቆጠረ ሲሆን ቢዝነሱን ለማሳደግ የሚጠቀመው መንገድ ዲዛየን ኢንተርኔት ላይ በማየት፣ ሌላው በሥራው ላይ ካሉ ወዳጆቻቸው ጋር በመነጋገር ልምድ በመለዋወጥ፤ እንዲሁም በቅርብ ሲኦሲ(COC) ሰርተፍኬት መጠይቅ መጀመሩ ከመጀመሪያው ደረጃ ጀምሮ የተሻለ እውቀት ሊጨምርላቸው አንደቻለ እና እንዲሁም በካይዘን ስለ ቦታ አጠቃቀም እና ምርት አያያዝ የወሰዱት ሥልጠና በጣም ለድርጅቱ ማደግ አስተዋጽዖ አንዳበረከተ ገልፀዋል።እንዲሁም ሥራውን ሲጀምሩ በፊት ሥራውን አስቀድመው ሲሠሩበት የነበረ ስለሆነ ምንም የሚቸግር ነገር እንዳልነበረ ጠቅሰዋል።

ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች ምርቶቹን የሚያስተውቅበት መንገድ በባዛር እና ባፈራቸው አምስት ተረካቢ ደንበኞች ነው።እንዲሁም ቴሌግራም እና ቢዝነስ ካርድ ይጠቀማል፤ ከዚህ በተጨማሪ በሰው በሰው በደንበኛ የሚመጣ ሥራ ብዙ ነው ሲሉ አስረድተዋል የድርጅቱ መስራች።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ኮቪድ ሙሉ በሙሉ የገበያውን ሁኔታ ነበር የዘጋው። የቆዳ ውጤቶች ብዙ ጊዜ ከውጭ በሚገቡ ዜጎች የሚገዙት፤ በኮቪድ ምክንያት ጉዞ ቆሞ በነበረበት ጊዜ ሥራው ተገድቦ ነበር። ይህን ለመቋቋም ሠራተኛ በመቀነስ፣ እንዲሁም ትርፍራፊ ቆዳዎችን መልሶ አገልግሎት ላይ በማዋል፣ የአጅ አምባር ጌጣጌጦችን እና የተለያዩ ነገሮችን መሥራት ተምረውበት እንደ ምንም ድርጅቱ ሳይዘጋ ሊቀጥል መቻሉን ገልጸዋል።

ማስተዋወቅ፣ ማስፋፋት እና ምክር

ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች እንደ ቢዝነስ ተምሮ ያስተካከለው ነገር ቁጠባ ነው፤ እቃ ሸምቶ ማስቀመጥ እቃ ላይ መቆጠብ እቃ መግዛት አሁን ባለው ሁኔታ የእቃዎች ዋጋ እየጨመረ ነው፤ ስለዚህ እቃዎችን በተቻለ መጠን ገዝቶ ማስቀመጥ ወሳኝ ነው ይላሉ አቶ ሰዋሰው።

ሥራን ውጤታማ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል ሥራው ላይ እንደ ቤተሰብ መተያየት፤ እያንዳንዱን ንብረት የጋራ ንብረት አድርጎ ማየት፤ አንዱ ሠራተኛ ቢቀር የእሱን ቦታ ተክቶ ለመሥራት እንዲቻል ብዙ ነገር መሥራት መቻልን ይጠቅሳሉ አቶ ሰዋሰው። የግል ሥራ የሚጀምር ሰው ከሱስ የጸዳ፣ አላማ ያለው እና ለሙያው ፍቅር ያለው ሊሆን ይገባል።


“ሁሉንም ሥራ ማወቅ መቻል አለበት የቆዳ ሥራ ላያተርፍ ይችላል ስለዚህ ቁርጥራጭ ሊሆን ይችላል ትርፉ፤ ስለዚህ እውቀቱን በደንብ ማወቅ መቻል አለብት አንድ ቆዳ ሠራተኛ ተረፈ ምርቱን መጣል ሳይሆን መልሶ መጠቀም መቻል አለበት። የቆዳ ሥራ በትንሹ ለመጀመር አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ያስፈልጋል።”

ሰዋሰው የቆዳ ውጤቶች በ2merkato የሚሰጠውን የከፍታ አገልግሎት የማስታወቂያ እና የጨረታ አገልግሎት ነገሮች ከተስተካከሉ በኋላ የመጠቀም ሀሳብ አለው።

ሰዋሰው ቆዳ ሥራ ወደ ፊት መንቀሳቀሻ መኪና የመግዛት እና ገበያውን በማስፋፋት ጥራት ያለውን ምርት ከሀገር ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለሃገሩ በማምጣት ትልቅ ድርጅት የመሆን አቅድ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ይህንንም ይመልከቱ

ሀሌታው ሀ ኅትመት እና ማስታወቂያ

ድርጅት የተመሠረተው በአቶ ዮናታን ታደሰ እና ሦስት መሥራች አባላት በ2012 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የኅትመት …