መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / አዲስ አበባ ውስጥ በ9 ወር ከ200,000 በላይ አዲስ ሥራ ተፈጥሯል ተባለ

አዲስ አበባ ውስጥ በ9 ወር ከ200,000 በላይ አዲስ ሥራ ተፈጥሯል ተባለ

የአዲስ አበባ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 205,477 የሥራ ዕድል ለከተማዋ ነዋሪዎች መፍጠሩን አስታወቀ።

የቢሮው ዳይሬክተር አቶ አብዮት ታደሰ ለኢትዮጵያ ሄራልድ እንደተናገሩት፣ አዲስ ከተፈጠሩት የሥራ ዕድሎች ውስጥ 167,138 የሚሆኑት ለወጣቶች ናቸው። ከአጠቃላይ ቁጥሩ ውስጥ ደግሞ 97,079ኙ ሴቶች፣ 21,342ቱ ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ምሩቃን ናቸው። በተጨማሪም ቢሮው ለ187,316 ሥራ አጥ ዜጎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ሠርቷል ተብሏል።

ቢሮው ለ874 ኢንትርፕራይዞች የመሥሪያ ቦታ ማስተላለፉን የተናገሩት አቶ አብዮት፣ የመሥሪያ ቦታ የተላለፈላቸው ኢንተርፕራይዞች በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በአግልግሎት፣ በንግድ እና በሌሎች ዘርፎች የተሰማሩ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ዳይሬክተሩ፣ የአዲስ አበባ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የመሥሪያ ቦታዎችን ከማስተላለፍ ጋር የተያያዙ የአስተዳደር ችግሮችን፣ በከተማ እና በፌደራል ደረጃ የተዘረጉ ሕጋዊ መዋቅሮችን በአግባቡ በመጠቀም ለመቅረፍ እየሠራ እንደሆነም ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ የቢሮውን መዋቅር በመቀየር የመሥሪያ ቦታዎችን የሚያስተዳድሩ ባለሙያዎች ተገቢውን ሥልጠና እንዲያገኙ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ ደረጃውን የጠበቀ የሰነድ አያያዝ ዘዴን ተግባር ላይ በማዋል ከሥራ ፈጠራ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ከሰነድ ጋር ተያያዥ የሆኑ እንከኖችን ለማስወገድ የሚመሩት ቢሮ ተፍ ተፍ እያለ እንደሆነም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። በተያያዘም፣ መንግስት የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማቅረብ ፈጣን እና አርኪ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ እንደሚገኝ አቶ አብዮት አብራርተዋል።

ምንጭ፡- https://www.press.et/english/?p=22297#

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …