መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ውለታው ብዙ እንጨት፣ ብረታ ብረት እና አልሙኒየም ሥራ

ውለታው ብዙ እንጨት፣ ብረታ ብረት እና አልሙኒየም ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ውለታው ብዙ እና በሦስት ባልደረቦቻቸው በ 2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የእንጨት፣ ብረታ ብረት እና አልሙኒየም ሥራዎችን በጥራት እና በታማኝነት የመሥራት አቅም አለው።

የሚያመርታቸው ምርቶች

  • የብረት እና የእንጨት አልጋዎች
  • የተለያየ መጠን ያላቸው ቁምሳጥኖች
  • ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ የግድ ግዳ ቁምሳጥኖች
  • ሶፋዎች
  • በር እና መስኮቶች በብረት፣ እንጨት እና በአልሙኒየም ማምረት
  • አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎች

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ውለታው ድርጅቱን ከመመሥረታቸው በፊት በአንጨት ሥራ ተቀጥረው ከዐሥር ዓመት በላይ ሠርተዋል። በዚህም ሂደት ሥራ እንዴት እንደሚሠራ ሊማሩ ችለዋል። በሥራ ላይ እያሉም አንዳንድ መሠረታዊ የሚባሉ የሥራ መሣሪያዎችን በመግዛት፤ በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞ አንዳንድ ቀለል ያሉ ሥራዎችን እና ጥገና በመሥራት ቆዩ። ከዚያም በኋላ የሚሠሩበት ድርጅት ያመጣውን ትልቅ ለውጥ በማየት አብረዋቸው ከሚሠሩ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ውለታው ብዙ እንጨት፣ ብረታ ብረት እና አልሙኒየም ሥራ ድርጅት እንጀምር እና እኛም እንለወጥ ብለው ድርጅቱን መሥርተዋል።

አቶ ውለታው ከድርጅቱ ምሥረታ በኋላ ትንሽ አስቸግሯቸው የነበረው ደንበኛ ማግኝት ነበረ። ይህንንም ችግረ ለሥራ የሚመጡትን ደንበኞች በአክብሮት በመያዝ እና ከምንም በላይ የሚሠሩትን ሥራ በጥራት በመሥራት ሊፈቱት ችለዋል። ይህም በጣም እንደጠቀማቸው ገልጸዋል። በዚህም ወደ ዘጠኝ የሚጠጉ ነጋዴዎችን እንደ ደንበኛ ማፍራት ችለዋል።

ድርጅቱ በሳምንት ሃያ የሚደረሱ ቁምሳጥኖችን እና ቡፌዎችን አጠናቅቆ የማምረት አቅም አለው። እንዲሁም አንድ ሦስት ፎቅ ለሆነ ሕንጻ ሙሉ ሥራ በር፣ መስኮት፣ አልጋ፣ ኪችን ካቢኔት እና የደረጃ መወጣጫ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የማጠናቀቅ አቅም አለው። በተጨማሪ ለሰባት ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር የቻለ ሲሆን፤ እንዲሁም ከነበረው መነሻ ካፒታል ብር አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር አሁን ወደ ሁለት መቶ ሺህ ብር ካፒታል አድጓል።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች ዋጋ

  • የልብስ ቁምሳጥን እንደ ጥሬ እቃው ዓይነት ቢለያይም አንድ ሜትር ከሃያ ሴንቲሜትር (1.20 cm) ከዘጠኝ ሺህ ብር ጀምሮ፤ ሰማንያ ሴንቲሜትር(80 cm) ደግሞ  ከስምንት ሺህ ብር ጀምሮ እንዲሁም፤ አንድ ሜትር ከሃምሳ (1.50 cm)  ከአሥራ አምስት ሺህ ብር ጀምሮ ለገበያ ያቀርባል።
  • ኪችን ካቢኔት ደግሞ በካሬ ሲሆን ዋጋ የሚወጣው የአንድ ካሬ ዋጋ ስድስት ሺህ ብር ነው። በግራናይት ከሆነ ደግሞ አንድ ካሬ ዋጋ ላይ የግራናይት ዋጋ ባለው የገበያ ዋጋ ይጨመርበታል።

ድርጅቱ ምርቶቹን አዲስ አበባ ላይ ከአሸዋ ሜዳ እስከ ጣፎ ድረስ ያቀርባል ከአዲስ አበባ ውጪ ደግሞ ባህርዳር፣ ደብረማርቆስ፣ ፍቼ አካባቢዎች አምርቶ አስረክቧል።

ይህ ድርጅት ሥራዎችን የሚያገኘው በዋናነት በሰው በሰው ሲሆን ይህም ጥሩ ሥራ ከተሠራ ሠው ራሱ ይመጣል፤ አንዳንዴ ደንበኛው ራሱ በሥራው በመተማመን ራሱ ኃላፊነት ወስዶ የሚመጡ ሥራዎች አሉ። በተጨማሪ ደግሞ ስድስት ለሚሆኑ አከፋፋዮች ምርቱን ያቀርባል። ይህንንም ሥራ የሚሠራው ሁሉም አንድ ላይ ሥራ አያመጡም አንዱ ሲጠይቅ ሌላው ይወስዳል እንዲህ እንዲህ እያለ አንዱ ሲመጣ አንዱ አይመጣም እንዲህ አድርጎ በማመጣጥን ነው ሥራዎችን የሚሠራው። እንዲሁም 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት መጠቀም ከጀመረ ጥቅሙን ይበል በመረዳት ጊዜያዊ ሠራተኞችን በማስገባት ትልቅ ሥራዎችን የመሥራት አቅም ላይ ድርሷል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

በኮሮና ወረርሽን ወቅት ብዙም ችግር አላጋጠማቸውም፤ የያዟቸው የኮንትራት ሥራዎች ስለነበሩ እነዛ ላይ በደንብ መሥራት እንዲችሉ አድርጓቸዋል። ሌሎች ሥራዎችን ሳይፈልጉ እንዲሁም አንዳንድ የሚመጡ ትንንሽ ሥራዎችን በመሥራት ነው ያሳለፉት።

ምክር እና እቅድ

አዲስ ወደ ዘርፉ የሚገቡ ሰዎች አንደኛ ገንዘብ ያስፈልጋል። አሁን ጥሬ እቃ በጣም ነው የተወደደው። ሥራ ለመሥራት ቢያንስ ግማሽ እንኳን መግዛት የሚችል ገንዘብ ያስፈልጋል። ከዛ ደግሞ ያንን አብቃቅቶ ለመሥራት እውቀት አስፈላጊ ነው። ቀጥሎ ደግሞ ሥራ ሁል ጊዜ እንዲኖር ደንበኛን በትህትና እና በአክብሮት ማናገር በጣም አስፈላጊ ነው፤ በፈገግታ ማናገር ያለው ትልቅ ቦታ ከሩቅ ቦታ ያንን ትህትና ብለው የሚመጡ ደንበኞች አሉ። ስለዚህ ለማንኛውም ቢዝነስ የሚናደድ የሚቆጣ ደንበኛ ቢመጣ አረጋግቶ መሸኘት ያስፈልጋል። ደንበኞችን በፍጹም አለማስቀየም፣ በተባለው ጊዜ ሥራ ማድረስ አስፈላጊ እንደሆነ ምክራቸውን አክለዋል።

እንደ ተጨማሪ “ቱመርካቶ ደንበኞቹ ቀላል የሆነ ምርታቸውን የሚያስተዋቅቁበት እንደ ጨረታ መከታተያው ዓይነት መተግበሪያ ቢያዘጋጅ ጥሩ ነው” ብለው አቶ ውለታው ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …