ኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ የ100 ሚሊየን ዶላር ብደር ስምምነት ተፈራረሙ
ፕሮጀክቱ የገንዘብ እጥረት ያለባቸውን ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች ብድር የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት እና የኮቪድ ወረርሽኝ ስራቸው ላይ ጉዳት ላደረሰባቸው ሴቶች የሚውል መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታዋ ተናግረዋል።
የብድር ስምምነቱ በጥቃቅን እና አነስተኛ ስራ ዘርፍ ለተሰማሩ ሴት ስራ ፈጣሪዎች የሚውል ነው ተብሏል።
የስምምነት ፊርማውን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ያስሚን ወሀብሬቢ እና በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ኤርትራ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ናቸው።
እንዲሁም ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን ለሚመሩ ሴቶች የንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና እንደሚያገኙም ገልጸዋል።
በተጨማሪም ለቴክኒክና ሙያ ተቋሟትና ለጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ቢሮዎች የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ይውላልም ነው የተባለው፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የብድር አገልግሎት የሚያገኙ ተጠቃሚዎች ያለ ከፍተኛ ማስያዣ ብድር ማግኘት የሚችሉባቸው መንገዶች መመቻቸቱም በዚህ ወቅት ተገልጿል።
የዓለም ባንክ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ በመስጠቱም ሚኒስትር ዲኤታዋ አመስግነዋል፡፡
የዜና ምንጭ ፋና ብሮድካስቲንግ