amard-coffee

አማርድ ቡና

አማርድ ቡና ድርጅት የተመሠረተው በ2007 ዓ.ም በአቶ አብዱ ሲራጅ እና ዘጠኝ መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የሚሰጠው አገልግሎት በዋናነት የቡና ምርቶች ሲሆን በተጨማሪ የባልትና ውጤቶችንም አብሮ ይሠራል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

ድርጅቱ የቡና ምርቱን በሁለት አይነት መንገድ (የተቆላ ቡና እና የተፈጨ ቡና) ለተጠቃሚ እያቀረበ ይገኛል። ይህንንም ምርት እንደ ጥራት ደረጃው አዲስ አበባ ብሎም በክልል ከተሞች ሐረር፣ ጅግጅጋ እንዲሁም ከአገር ውጭ ደግሞ በሱዳን እና ሳውዲ አረቢያ ምርቱን እያቀረበ ይገኛል።

አቶ አብዱ ወደ ቡና እና ባልትና ሥራ ሲገቡ በጊዜው የቡና ዋጋ በጣም ርካሽ ስለነበር እና ደግሞ ቡና ማንም ሰው ገዝቶ አፍልቶ መጠቀም የሚችልበትን ሁኔታ በመፍጠር ጊዜ እና ጉልበትን ለመቀነስ ታስቦ እንደሆነ እና አብሮ ደግሞ የባልትና ሥራ ለመሥራት አስበው ከአባሎቻቸው ጋር እንሞክረው በማለት ሁለት ሴቶች እና ስምንት ወንዶች በመሆን ነው ድርጅቱን የመሠረቱት። አቶ አብዱ ይህን ድርጅት ከመጀመራቸው በፊት በንግድ ሥራ ተቀጥረው ሲሠሩ ቆይተዋል። የባልትናው ሥራ ብዙም ሳያዋጣ ሲቀር ሙሉ አቅማቸውን ወደ ቡናው በ2008 ዓ.ም በማዞር በሙሉ አቅማቸው ሥራ ጀምረዋል። ድርጅቱ ሲመሠረት በአርባ ሺህ ብር ካፒታል ነበር ሥራ የጀመረው፤ አሁን ካፒታሉ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ደርሷል።

ድርጅቱ ወደ ቡና ሥራ ካተኮረ በኋላ ሥራውን እና ተጠቃሚዎችን ብሎም ደንበኞችን ማግኘት ትልቁ አስቸጋሪ ነገር ነበር። ነገር ግን ቀስ በቀስ ስለቡና አሠራር፣ አያያዝ አቆላል፣ አቀማመጥ እንዲሁም አቀማመስና የተለያዩ ነገሮችን ራሳቸውን በማስተማር ሲያበቁ የምርት ጥራታቸውም አብሮ ስለጨመረ ደንበኛም ማግኘት ችለዋል። ሥራውን እያደገ መጥቷል። ሌላው የድርጅቱ ችግር የማሽን አጥረት በመሆኑ በእንጨት እና በኤሌክትሪክ መሥራት በጣም ሰፊ ልዩነት አለው የኤሌክትሪክ ሂደት በጣም ፈጣን ከመሆኑ በላይ ጊዜ ይቆጥባል። የኤሌክትሪኩን ማሽን ማሟላትና የኃይል አቅርቦት ዋናዎቹ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ናቸው። ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት ለሦስት ቋሚ እና ለአራት ጊዜያዊ ሠራተኞች የሥራ እድል መፍጠር ችሏል።

ድርጅቱ ቡና በአዳር ጭምር በመሥራት በሌሊት ፈረቃ በመቁላት እና ቀን በመፍጨት በቀን አምስት መቶ ኪሎ የተፈጨ ቡና የማምረት አቅም ደርሷል።

ድርጅቱ የተፈጨ ቡና ዋጋ እንደሚከተለው ለተገልጋይ ያቀርባል፡፡

  • ሩብ ኪሎ ቡና ሰባ አምስት ብር
  • ግማሽ ኪሎ መቶ ሃምሳ ብር
  • አንድ ኪሎ ሶስት መቶ ብር ዋጋ ይሸጣል

የኮቪድ ተፅዕኖ

የኮቪድ ተፅዕኖ ብዙም ባይባል ጉዳት ነበረው። ደንበኛ ቀንሷል የቡና ዋጋ በጣም እንዲወደድ አድርጓል። ያስቀመጡትን በመጠቀም እና የቡናውን ምርት የሚያቀርቡ ሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ስለነበራቸው ከእነሱ ጋር በመነጋገር ሊያልፉት ችለዋል።

ድርጅቱ ሥራዎቹን በተለያየ መንገድ ያስተዋውቃል፤ ለምሳሌ ሶሻል ሚዲያ እና እስቲከሮችን እንዲሁም ባነሮችን በመጠቀም ምርቱን እያስተዋወቀ ይገኛል።

ምክር እና እቅድ

አማርድ ቡና ድርጅት በጊዜ ሂደት አሠራሩ ላይ የተለያዩ ነገሮችን በመጨመር የተሻለ እድገት ሊያመጣ ችሏል። ካስተካከላቸው ነገሮች ውስጥም በማሸጊያው ላይ የምርቱ አገልግሎት ማብቂያ ቀን መፃፍ በጣም ብዙ የተጠቃሚ ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል፤ በመቀጠል የማሸጊያውን ቀለሙንም በመቀየር ጥሩ ለውጥ አምጥቷል። ይህም ዐይን ውስጥ ቶሎ ይገባል። በዚህም ድርጅቱ ጥሩ ምርት እየሸጠ ይገኛል።

ወደ ፊት አማርድ ቡና የሥራ ቦታውን ሰፋ በማድረግ ሥራውን ማስፋት እና ሌሎች ድርጅቱ ያጠናቸው ሥራዎች አሉ አነሱን ለመጀመር እቅድ አለው።

አዲስ ወደ ሥራ ለሚገቡ ሰዎች አቶ አብዱ የሚከተለውን ምክር አስተላልፈዋል። “ወደ አምራች ሥራ የሚገቡ ሰዎች ሥራውን ወደውት እና ሥራውን አውቀውት መሆን አለበት። ሁለተኛ ደንበኛ ምን ይፈልጋል? የሚለውን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፤ ቀጥሎ ሥራንው ማስተዋወቅ እነዚህ ዋና መሠረታዊ ነገሮች ናቸው። በእነዚህ ነገሮች ላይ ተዘጋጅተው ከገቡ ውጤታማ መሆን ይችላሉ።”

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …