መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / መክሊት የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ.
meklit-logo

መክሊት የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ.

መክሊት የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው አዋጅ ቁጥር 40/96 ከዚያም ተሻሽሎ በወጣው አዋጅ ቁጥር 626/2009 መሠረት በከተማና በገጠር ለሚኖሩ ምርታማ ዜጎች በተለይም የባንክ አገልግሎት ዕድል ላላገኙ ሴቶች እና ወጣቶች የብድር፤ የቁጠባና አነስተኛ የመድን ዋስትና አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ሲሆን ላለፉት 19 ዓመታት አገልግሎቱን በጥራትና በብቃት እያቀረበ የሚገኝ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም ነው።

መክሊት፡- ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

ራዕይ

መክሊት የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ በሀገራችን ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን የሕብረተሰብ ክፍል አካታች የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት ቀዳሚ በመሆን ከድህነት ነፃ የሆነ ሕብረተሰብ ማየት ነው።

ተልዕኮ

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍል ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አክልነታቸውን እንዲያሻሽሉ የፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ በተለይም ሴቶችና ወጣቶች ተስማሚ የገንዘብ አገልግሎት እንዲያገኙ ፤ ገቢያቸውንና የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ተደራሽና ጥራት ያለው ፤ ደንበኛ ተኮርና ቀልጣፋ የፋይናንስ አገልግሎት በዘላቂነት መስጠት ነው።

ዓላማ

  • በገጠርና በከተማ ዝቅተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ አምራች የህብረተሰብ ክፍል የኑሮ ሁኔታቸው ፤ የገቢ አቅማቸው እና የሀብት መጠናቸው እንዲያሻሽሉ ተስማሚ የፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ
  • ለባንክ ተደራሽ ያልሆኑ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍል የብድርና ቁጠባ አገልግሎት መስጠት
  • በተለየ ሁኔታ ሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውና ማህበራዊ ተሳትፎአቸው አንዲጠናከር ቅድሚያ የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ ማገዝ
  • ድህነት እንዲቀረፍ ጥራቱን የጠበቀና የደንበኞችን ፍላጎት ያማከለ ፤ ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ አገልግሎት በከተማና ገጠር አምራች የሕብረተሰቡ ክፍል ማቅረብ
  • የተለያዩ የቁጠባ አይነቶችን በመቅረፅ የቁጠባ ልምድ እንዲያዳብሩና የተሻለ ሀብትና የሥራ ዕድሎችን እንዲፈጥሩ ማበረታታት
  • ለጥቃቅንና አነስተና የንግድ ሥራ አንቀሳቃሾች ፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጣሪ ሠራተኞች፤ አዋጭና ውጤታማ የሥራ መስክ ላይ ለተሰማሩ ከሙያዊ ድጋፍ ጋር የፋይናንስ አገልግሎት ይሰጣል
  • መክሊት፦ የተቋሙ አገልግሎቶች

    1. የብድር አቅርቦት
    2. የቁጠባ አገልግሎት
    3. የአነስተኛ ብድር የህይወት መድን ሽፋን
    4. ለደንበኞቹ የንግድ ሥራና ቢዝነስ አስተዳደር፤ የብድር እና ቁጠባ ደንቦችንና ጠቀሜታ ግንዛቤ ማስጨበጫ ምክሮችን ይሰጣል
    1. የአግሪ (ግብርና) ብድር
    2. የአግሪ (ግብርና) ቢዝነስ ብድር
    3. የንግድ የቡድን ብድር
    4. የግል ንግድ ብድር
    5. የፍጆታ ብድር
    6. የታዳሽ ኃይል ማመንጫ ብድር
    7. የሴቶች ኢንተርፕራይዝ የግል ብድር
    8. የወጣቶች ኢንተርፕራይዝ ብድር
    9. የመልሶ ማቋቋሚያ ብድር
    10. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ብድር
    11. የባጃጅ መግዣ ብድር
    12. የሠራተኛ ብድር
    13. በመሬት ይዞታ ዋስትና የግል የግብርና ብድር
    1. የፍቃደኝነት የደብተር ቁጠባ
    2. የጊዜ ገደብ ቁጠባ
    3. የሳጥን ቁጠባ
    4. ወለድ አልባ ቁጠባ
    5. የህጻናትና ወጣቶች ቁጠባ ናቸው
    1. ጠቀም ያለ የቁጠባ ወለድ ይከፍላል
    2. ባሉበት ስፍራ ፈጣን አገልግሎት በመስጠት አላስፈላጊ የሆነ ወጪንና የጊዜ ብክነትን ያስቀራል
    3. ለሴቶች ልዩ ትኩረት ይሰጣል።
    በአሁን ሰዓት የካፒታሉን መጠን በማሳደግ የበለጠ ተደራሽነቱን ለማስፋፋት አዳዲስ አክሲዮን በመሸጥ ላይ ይገኛል
    • ተቋሙ በ2010 በጀት ዓመት ከ10.8 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማስመዝገብ እያንዳንዱ ባለአክሲዮን 89% የአክሲዮን ዕድገት እንዲያገኝ አድርጓል። አሁንም ተጠቃሚዎች አክሲዮን በመግዛት የከፍተኛ ትርፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይጋብዛል
    • እንድ ሰው መግዛት የሚችለው ዝቅተኛ የአክሲዮን ብዛት 5 (አምስት) የአንዱ ዋጋ ብር 1000 በጠቅላላው 10% ፕሪምየም ጨምሮ ብር 5,500 (አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) ሲሆን ከፍተኛ 5,000 (አምስት ሺህ) አክሲዮን በዋጋ 10% ፕሪምየም ጨምሮ ብር 5,500,000 (አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺ ብር) ነው
    • የአክሲዮን ሽያጭ ቦታ በዋና መሥርያ፦ ቤትና በሁሉም ቅርንጫፎች በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤ እንዲሁም በአዋሽ ባንክ በተከፈተው በባንክ ሂሳብ ቁጥር C/A 01302212680900 ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር C/A1000291863586 ወይም ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ቁጥር 619054 ገቢ በማድረግ መግዛት ይችላሉ። ለተጨማሪ መረጃ ከታች ቀጥሎ በተገለጸው የዋና መሥርያ ቤት ስልክ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
     

    መክሊት የአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አድራሻ

    ዋና መሥርያ ቤት እና ቅርንጫፍ ቢሮዎችስልክ ቁጥር
    ዋና መሥርያ ቤት፦ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስትያን አትላስ መንገድ ደጎል ሕንጻ 1ኛ ፎቅ011 3 69 40 33፣ 011 3 48 41 52፣ 011 3 48 21 83
    ሾላ መገናኛ011 6 58 65 52
    አየር ጤና011 3 69 30 26
    ኮልፌ011 2 79 94 82
    ልደታ011 5 52 36 87
    ሰበታ011 3 38 01 30
    አዳማ022 3 33 03 00
    ዴራ022 1 18 11 37
    መቂ022 4 41 07 27
    አቦምሳ022 4 43 03 65
    አርሲሮቢ022 4 44 01 59
    ጢቾ022 3 30 02 63
    ስሬ046 1 15 12 50
    ብታጅራ046 5 58 03 38
    እንሴኖ011 3 30 01 99
    ወልቂጤ011 3 31 03 79
    እምድብር011 3 32 04 44
    ጉንችሬ046 8 82 04 39
    ስልጢ046 8 82 04 39
    ባቱ046 1 41 66 90
    በተጨማሪም አዳዲስ ቅርንጫፎች በእነኝህ ከተሞች ውስጥ በመክፈት ላይ ይገኛል።
    • በአዲስ አበባ፦ አቃቂ ቃሊቲ
    • በኦሮሚያ፦ በሱሉልታ፣ በለገጣፎ ለገዳዲ፣ በቡራዩ፣ በቢሾፍቱ እና በአሰላ

    ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው መክሊት የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

    ይህንንም ይመልከቱ

    ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

    ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …