መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / በኮሮና ቫይረስ ለተጎዱ ኢንተርፕራይዞች የቀረበ ዝቅተኛ ወለድ እና እፎይታ ያለው ብድር

በኮሮና ቫይረስ ለተጎዱ ኢንተርፕራይዞች የቀረበ ዝቅተኛ ወለድ እና እፎይታ ያለው ብድር

በኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ የተነሣ በደረሰው የንግድ መቀዛቀዝ ውስጥ፣ ሥራቸውን ለመቀጠል እየጣሩ ያሉ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመደገፍ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን፣ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን እና ፈርስት ኮንሰልት በጋራ ኢንተርፕራይዞቹ ድጋፍ የሚያገኙበት ፕሮጀክት አዘጋጅተዋል።

በፕሮጀክቱም መስፈርቱን የሚያሟሉ ኢንተርፕራይዞች ዝቅተኛ ወለድ እና የእፎይታ ጊዜ ያለው ብድር ተመቻችቶላቸዋል።

በዚህም መሠረት፡-

የሠራተኞች ብዛት፡- ከ 2 እስከ 5 ለጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ፣ ከ 6 እስከ 30 ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዝ
እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም ድረስ ቢያንስ አንድ ዓመት ሥራ ላይ የቆየ

በተለይ፣ በሴቶች እና በወጣቶች ለሚተዳደሩ ኢንተርፕራይዞች ፕሮጀክቱ ቅድሚያ እንደሚሰጥም ተገልጿል።

መስፈርቱን የምታሟሉ ኢንተርፕራይዞች፣ ወይም ዝርዝሩን ለመመልከት ይህንን ሊንክ ይከተሉ፡-

https://www.ethiomsefund.com/landing/home/info

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …