ድርጅቱ የተመሠረተው በ2012 ዓ.ም. መጨረሻ በወ/ት ሠርካለም ተሰማ የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ ነው። ድርጅቱ የላብራቶሪ እቃዎችን እና የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች ያቀርባል።
ድርጅቱ ከሚያቀርባቸው እቃዎች በጥቂቱ
- ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኬሚካሎች
- ለትምህርት መማሪያ የሚያገለግሉ ሞዴሎች፣ ቅርፃ ቅርፆች ለምሳሌ እንደ ልብ፣ ሳንባ፣ አይን እና ሌሎችም ሞዴሎች
- የተለያየ የሙቀት መጠን የሚለኩ ቴርሞ ሜትሮች
- ለደህንነት መጠበቂያ የሚያገለግሉ ግላስ ዌሮች እንዲሁም
- የተለያዩ የትምህርት መሣርያዎች፣ ቻርቶች እና አጠቃላይ የትምህርት መርጃ መሣርያዎች
ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት
ወ/ት ሠርካለም የግላቸውን ድርጅት ከመጀመራቸው በፊት ኬሚስትሪ ተምረው በዲግሪ ተመርቀዋል። በመቀጠልም የላብራቶሪ እቃዎችን በሚያመጣ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ገደማ ሠርተዋል። በዚህ ጊዜ በትምህርት የተማሩትን በተግባር በደንብ የማወቅ እድል አገኙ። ከአለቃቸው ጋር በመመካከር አንድም የተማሩበት ዘርፍ ስለሆነ፣ እንዲሁም አንዳንድ ችግሮች ቢገጥሟቸው ከአለቃቸው ጋር በመተጋገዝ ለመሥራት በማሰብ ነው የግላቸውን ድርጅት የመሠረቱት።
ድርጅቱ ሥራዎችን የሚሠራው በዋናነት ጨረታ በመጠቀም ሲሆን በመቀጠል ደግሞ በሰው በሰው የሚመጡ ሥራዎችን ይሠራል። ለዚህ ደግሞ 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ባዘጋጀው የከፍታ ፓኬጅ በኩል ጨረታዎችን በቀላሉ በመከታተልና በመሳተፍ ተጠቃሚዎች ሆነዋል። ይህንን ፓኬጅ በመጠቀም የተለያዩ ጨረታዎች ላይ ተሳትፈዋል እየተሳተፉም ይገኛሉ፤ በዚህም ከአምስት በላይ ጨረታዎችን በማሸነፍ ያሸነፉትን ጨረታ በጥሩ አፈጻጸም ከዳር ማድረስ ችለዋል።
ድርጅቱ ሲመሠረት ከነበረው አንድ ሠራተኛ በተጨማሪ አሁን ላይ ለአንድ ዜጋ ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ሲሆን፤ እንዲሁም በፊት እቃዎችን ለመግዛት ከተለያየ ቦታዎች በማሰባሰብ ይገዛ የነበረውን የፋይናንስ አቅም በማሳደግ ለሥራ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም እቃ በራሱ ገዝቶ ማቅረብ የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረስ ችሏል።
ድርጅቱ ምርቱን ካቀረባቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨሲቲዎች መካከል ጥቂቶቹ
- አፄ ቴዎድሮስ ት/ቤት
- ሀምሌ 19 ት/ቤት
- አዳማ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም
- በብዛት አዲስ አበባ ላይ የሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ የላብራቶሪ እና የትምህርት መርጃ መሣርያዎችን አቅርቧል።
ወ/ት ሠርካለም በሥራ ወቅት ለሚያጋጥማቸው ችግር የሚያማክሩት በፊት ሲሠሩበት የነበረውን ድርጅት ሲሆን፤ ከነሱ ጋር በመመካከር እንዲሁም አዳዲስ መንገዶችን በማየት ችግሮችን እንደሚፈቱ ጠቅሰዋል።
የኮቪድ ተፅዕኖ
በኮሮና ወቅት ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ሥራ አቁሞ ነበር። ይህም ይወጣ የነበረው የጨረታ መጠን ቀንሶ ስለነበር እና በሰው በሰው የሚመጣም ሥራ ቆሞ ነበር። ትምህርት ቤቶችም ተዘግተው ስለነበር ብዙ ሥራ አልነበረም፤ የቀዘቀዘ ሁኔታ ነበር። በዛም ምክንያት ሥራ ለማቆም ተገዶ ነበር።
ዕቅድ
ድርጅቱ ወደ ፊት በአስመጪነት ሥራ ላይ የመሰማራት እቅድ አለው። እንዲሁም የከፍታ ፓኬጅ በጣም እንደጠቀማቸው እና በአገልግሎቱ ደስተኛ እንደሆኑ የደርጅቱ መሥራች ወ/ት ሠርካለም ጠቅሰዋል።