ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ፍቅር መላኩ በ2003 ዓ.ም. ነበር። ተመሥርቶ በነበሩ አንዳንድ ሁኔታዎች ለተወሰነ ጊዜ ከቆመ በኋላ እንደገና በ2009 ዓ.ም. አንደ አዲስ ሥራ ቀጥሏል። ድርጅቱ አጠቃላይ የፊኒሽንግ ሥራዎች እና ተያያዥ የሆኑ የብረት ሥራዎችን ይሠራል።
ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች
- የሕንጻ ልስን ሥራ
- የሕንጻ ፓርቲሽን ሥራ
- የኳርትዝ ሥራ
- የኤሲፒሲ ሥራ
- የቀለም ቅብ ሥራ
- የበረንዳ ሥራ እና
- የመወጣጫ ደረጃዎች ሥራ
ድርጅቱ አገልግሎቱን ካቀረበባቸው ቦታዎች መካከል
- ቦሌ አየር ማረፍያ እና ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን (አዲስ አበባ) የኤስፒሲ ሥራ
- ቦሌ መድኃኒዓለም አካባቢ ወርቁ ሕንጻ
- ቦሌ ትምህርት ቤት አጠገብ ሳውዝ አፍሪካ ሕንጻ
- ብርሃኔ አደሬ ሕንጻ አጠገብ የሚሠራው ሕንጻ የልስን ሥራ እንዲሁም
- ከመከላከያ እና ከሱር ኮንስትራክሽን ጋር በመሆን ሥራዎችን ሠርቷል።
ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት
ድርጅቱ ሲመሠረት የነበረው መነሻ ካፒታል ብር 50,000 (ሃምሳ ሺሕ ብር) ሲሆን ካፒታሉን ወደ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺሕ ብር) ማሳደግ ችሏል። የነበሩት መሥራች አባላት ቁጥር ሦስት የነበረ ሲሆን አሁን የግል ኢንተርፕራይዝ ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ድርጅቱ አሁን ባለው ሁኔታ ለሦስት ዜጎች ቋሚ የሥራ እድል እና ለሃያ ዜጎች ደግሞ ጊዜያዊ የሥራ እድል መፍጠር የቻለ ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት አሁን ባለው የማምረት አቅም ላይ ማንኛውም ዓይነት የተረከበውን ሥራ በተባለው ጊዜ የማስረከብ ብቃት አለው።
አቶ ፍቅር ወደ ኮንስትራክሽን ዘርፍ የገቡት ራሳቸውን ለማስተዳደር እና የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ብለው ነበር። ሊሠሩት የሚችሉት ሥራ አናጺነት ስለነበር ቀን እየሠሩ ማታ ደግሞ እየተማሩ በሥራው ደግሞ ቤተሰብ እየረዱ መሥራት ይጀምራሉ። ቀስ በቀስ የቀለም ሥራ እያዩ እና እየተማሩ መጡ፤ በሂደት ሙሉ የፊኒሽንግ ሥራ አጠናቅቀው መሥራት ሲችሉ በንዑስ ተቋርጭነት (sub contractors) ቀለል ያሉ ሥራዎችን መሥራት ጀምሩ። ሥራዎችን በሚሠሩበት ጊዜ የወደፊቱን እያሰቡ ስለነበር የሚሠሩት ሥራቸው ጥራት ነበረው። ይህም ብዙ ሥራዎችን በሰው በሰው እንዲሠሩ አስችሏቸዋል። በዚህም አጠቃላይ የዐሥራ ዐምስት ዓመት የሥራ ልምድ አዳብረዋል። ይህም አቅመ ደካማ የሆኑትን ቤተሰባቸውን እንዲረዱ እና ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እንዲችሉ አድርጓቸዋል።
ድርጅቱ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኘው በዋናነት በሰው በሰው ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ የሚሠራቸው ሕንጻዎች ላይ የባነር ማስታወቂያ በመለጠፍ ነው። ሌላው ደግሞ በጨረታዎች ላይ በመሳተፍ ነው፤ በዚህም ወደ ስድስት ጨረታዎችን ማሸነፍ ችሏል። ለምሳሌ ሰላም ለኢትዮጵያ የጋራ መኖሪያ ቤት ሁለት አፓርታማ የደረጃ እና የበረንዳ ብረት ሥራ በአንድ ወር ሠርተው አስረክበዋል። አቶ መላኩ የከፍታ አገልግሎት መረጃ ተደውሎላቸው ነበር፤ ከዛም በወረዳ ቢሮ በኩል ሲነገራቸው 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት መጠቀም ጀምረዋል።
የኮቪድ ተፅዕኖ
በኮቪድ ጊዜ ሁኔታዎችን በጣም አስቸጋሪ ነበሩ። እንደምሳሌ በወቅቱ አንድ ሥራ ሳር ቤት አካባቢ እየሠሩ ነበር። ነገር ግን ትራንስፖርት አልነበረም ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት እየወጡ ነበር የሚሠሩት። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ ሠራተኞች ደግሞ አይቆዩም ነበር፤ ቶሎ ቶሎ ይለቁ ስለነበር በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነበር ድርጅቱ ያሳለፈው።
ምክር እና ዕቅድ
ድርጅቱ አሁን ያለውን ሂሳብ አሠርቶ ወደ መካከለኛ ተቋራጭ የማደግ ዕቅድ አለው።
አዲስ ወደ ዘርፉ የሚገቡ ሰዎች ማወቅ ያለባቸው አንደኛ ሥራ መናቅ የለባቸውም፤ ትንሽ የአንድ ክፍል ቤት ሥራም ቢሆን መሥራት አለባቸው። ቀስ በቀስ ነው ሥራው ማደግ የሚችለው። ያ ሰው ሌላ ሥራ ያመጣላቸዋል። ያንንም ሥራ እንደማሳያ መጠቀም ይችላሉ፤ ይህ ደሞ ምንም ሥራ ካለመሥራት በጣም የተሻለ ነው። ስለዚህ በዚህ ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን ያገኙትን መሥራት እና በተግባር ሠራተኞችን እየመሩ ሲሠሩ ማሳየት አስፈላጊ ነው።
የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ።