መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / በጃንሜዳ የነበሩ ነጋዴዎች ዛሬ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው የገበያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ
laphto-fruit-veg-market

በጃንሜዳ የነበሩ ነጋዴዎች ዛሬ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው የገበያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ

በጃንሜዳ የነበሩ ነጋዴዎች ከዛሬ ጀምሮ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በሚገኘው በላፍቶ የአትክልትና ፍራፍሬ የገበያ ማዕከል አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ። ይህንንም የተናገረው የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ነው።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ ዩሱፍ በትናንትናው ዕለት እንደገለጹት ጃንሜዳ የሚገኘው ጊዜያዊ አትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ የገበያ ስፍራ ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት በማቆም ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ አዲስ በተገነባው ወደ ላፍቶ የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ገበያ ማዕከል ይዘዋወራሉ ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በጃንሜዳ ጊዜያዊ አትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ይሠሩ የነበሩ ነጋዴዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ወደ ላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ አዲሱ የገበያ ማዕከል እንዲዘዋወሩ በወሰነው መሰረት የሱቆች ዕጣ የማውጣት እና ውል መዋዋል ሥራ መሠራቱን አቶ አብዱልፈታ ገልጸዋል።

የአትክልት መገበያያ ስፍራዎችን በተለያዩ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ የቦታ መረጣ እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሠራት ላይ እንደሚገኝ አቶ አብዱልፈታ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

laphto-fruit-veg-market-2

የዜና  እና የምስል ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …