መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በቡና መቀበያ ቅርንጫፎች የቡና ናሙና ማሳያ ሥራ ላይ አዋለ
green-coffee-bean

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በቡና መቀበያ ቅርንጫፎች የቡና ናሙና ማሳያ ሥራ ላይ አዋለ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በቡና መቀበያ መጋዘኖች ለውጪ ገበያ የሚቀርብ የቡና ምርት ናሙና ማሳያ (Sample Display) አዘጋጅቶ ከነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡

በግብይት ሥርዓቱ ላይ የደንበኞችን ፍላጎት በማሟላት የወጪ ንግዳችንን ለማሳደግ የሚከናወኑ የማሻሻያ ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል በአቅራቢዎች፣ በገዢዎችና በምርት ገበያው መካከል ያለውን የአሰራር ግልጽነት ለማጠናከር ይህ የናሙና ማሳያው ተግባራዊ ተደርጓል፡፡እንዲሁም የናሙና ማሳያው እንዲዘጋጅ ከደንበኞች ይቀርብ የነበረውን ጥያቄ በመመለስ በተገበያዮች መካከል መተማመን እንዲኖርና በምርት ጥራት ላይ የሚቀርበውን ቅሬታ ለመከላከል ያስችላል፡፡coffee-bean

ላለፈው አንድ አመት ለሀገር ውስጥ ግብይት የሚውለውን ቡና ናሙና በአዲስ አበባ ሳሪስ ቅርንጫፍ ለተገበያዮች በማሳየት ስኬታማ አገልግሎት ለመስጠት ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከደንበኞች የሚነሱ ቅሬታዎችን በመቀበል በግብይት ሥርዓቱ የተለያዩ ማሻሻያዎችንም ማድረጉን ይቀጥላል፡፡

የዜና ምንጭ፦ የኢትዮጵያ  ምርት ገበያ የሊንክዲን (LinkedIn) ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …