አማራጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር

አማራጭ የኮድ 3 ሜትር ታክሲ እና የኮድ አንድ ታክሲ ባለንብረቶችና አሽከርካሪዎች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ኅብረተ ሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ ራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባን ባሕል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ታኅሳስ 9 ቀን፣ 2014 ዓ.ም. በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 50 አባላትን በመያዝ በአዋጅ 985/2009 መሠረት ተመሠረተ።

“እንቆጥባለን፤ ያሰብነውን እናሳካለን”

አማራጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

  • የኅብረት ሥራ ማኅበሩ በዋናነት ትኩረት አድርጎ የተመሠረተው በአገራችን ውስጥ በኮድ 3 ሜትር ታክሲ እና በኮድ 1 ታክሲ አገልግሎት ላይ በተሰማሩ የማኅበረ ሰብ ክፍሎች ላይ ሲሆን፣ እነዚህ የማኅበረ ሰብ ክፍሎች አሁን ባለው መረጃ መሰረት ከ30,000 (ሰላሳ ሺህ) እስከ 40,000 (አርባ ሺህ) የሚደርሱ እንደሆኑ ተጨባጭ ማስረጃዎች አሉ።
  • እያንዳንዱ የታክሲ አገልግሎት ሰጪ በቀን በአማካይ እስከ ብር 1፣000.00 (አንድ ሺህ ብር) ገቢ የሚያስገባ ሲሆን ይህ ማለት ማኅበሩ ትኩረት ያደረገበት የማኅበረ ሰብ ክፍል በቀን እስከ ብር 30,000,000.00 (ሰላሳ ሚሊዮን ብር) ብር ድረስ የማንቀሳቀስ አቅም አለው።
  • ስለሆነም ማኅበሩ ይህን ቁጥር ሰፊ የሆነ የማኅበረ ሰብ ክፍል ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል መልኩ የተደራጀ ሲሆን ከእነዚህ የማኅበረ ሰብ አባላት በተጨማሪም የማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ የሚጠይቀውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የማኅበሩ አባል መሆን በሚያስችለው መልኩ የተቋቋመ ነው።

ራዕይ

በ2019 ዓ.ም. ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ተመራጭ የሆነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ሆኖ ማየት

ተልዕኮ

አባላትን ቆጥቦ ስለመለወጥ ያላቸውን ግንዛቤ በማሻሻል በፍላጎታቸው ላይ የተመሠረተ ቁጠባ እንዲቆጥቡ በማድረግና ብድር በማበደር በማኅበረ ሰባችንና በአገራችን ኢኮኖሚ ላይ የራሳችንን አስተዋጽዖ ማበርከት ነው።

ዓላማ

  • አባላት በተናጠል በመሥራት ሊወጡዋቸው የማይችሏቸውን የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ችግሮችን በተባበረ ጥረት መወጣት፣ መቋቋምና መፍታት
  • አባላት ያላቸውን ዕውቀት፣ ሀብትና ጉልበት በማቀናጀት የተሻለ ውጤት ማግኘት
  • አባላት በዓላማ ላይ የተመሰረተ የቁጠባ ባሕል አንዲያዳብሩ ማድረግ
  • የአባላትን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጋራ በመሆን የሚቀረፍበትን የገንዘብ አቅም መፍጠር
  • አባላት ያላቸውን ዕውቅት፣ ሀብት እና ጉልበት በማቀናጀት የተሻለ ውጤት ማግኘት
  • ሌሎች የኅብረት ሥራ ማኅበርን መርህ የማይቃረኑ ተመሳሳይ ተግባራት ማከናወን

አማራጭ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር፦ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

  1. እድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
  2. ከአባላት ጋር ተመሳሳይ ፍላጎትና ዓላማ ያለው
  3. የኅብረት ሥራ ማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ እና ልዩ ልዩ መመሪያ የሚቀበል
  4. የመመዝገቢያ ብር 1,000 (አንድ ሺሕ ብር) እና ዝቅተኛውን የዕጣ ክፍያ ብር 2,000 (ሁለት ሺሕ ብር) መክፈል የሚችል
  5. በማኅበሩ ውስጥ በተለያዩ ኮሚቴዎች ሲመረጥ ያለ ክፍያ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆነ

መደበኛ ቁጠባ

  • የማኅበሩ ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ነው

የፍላጎት ቁጠባ

  • እያንዳንዱ አባል ከመደበኛው ቁጠባ በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ መቆጠብ ይችላል። መደበኛ ያልሆነ ወይም የጊዜ ገደብ ቁጠባ ሲሆን ይህ ቁጠባ አስገዳጅ በሆነ ጊዜ መጠቀም ይችላል።

የጊዜ ገደብ ቁጠባ

  • የጊዜ ገደብ ቁጠባ የማኅበሩ አባል የሆኑ ወይም ያልሆኑ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ከ6 ወር በላይ እና ከብር 3,000 (ሦስት ሺህ ብር) ብር ጀምሮ የሚቆጠብ ሲሆን እንደተቀማጩ የገንዘብ መጠን እና ከሚቀመጥበት ጊዜ መነሻ ተድርጎ ከ9 -12.5% ወለድ ይከፍላል።

የመኪና ቁጠባ

የቤት ቁጠባ

የህጻናት (ልጆች) ቁጠባ

  • የህጻናት ቁጠባ በማኅበራችን የሥራ ክልል እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት የማኅበሩ አባላትም ሆነ አባል ያልሆኑ ሰዎች ልጆች በወላጆቻቸው አማካኝነት 8% ወለድ የሚታስብለት ከብር 25 (ሃያ ዐምስት ብር) ጀምሮ መቆጠብ የሚያስችል የቁጠባ ሒሳብ ነው። እድሜያቸው 18 ዓመት ሲሆናቸው ያለመመዝገቢያ ክፍያ የማኅበሩ አባል መሆን ይችላሉ።
  • የዕለት ደራሽ ብድር
  • የደመወዝ ብድር
  • ለንግድ ሥራ የሚሰጥ ብድር
  • ለመኪና መግዣ
  • ለቤት መግዣ
  • በማህበር ተደራጅተው ለሚሠሩ አባላት የሚሰጥ ብድር
ተ.ቁ የብድር አይነቶችየብድር መጠን በብር እስከብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠን በፕርሰንትብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠን በብርብድር ለመውሰድ የቅድመ የቁጠባ ጊዜ በተከታታይየብድር ወለድ መጠንየብድር መመለሻ ጊዜ
1የእለት ደራሽ ብድር20,000.0020%4,000.002 ወር13.5% ለአካል ጉዳተኛ
14% ለሴቶች
14.5% ለመደበኛ
6 ወር
2የደመወዝ ብድር100,000.0025%25,000.005 ወር13.5% ለአካል ጉዳተኛ
14% ለሴቶች
14.5% ለመደበኛ
24 ወር
3ለአነስተኛ የንግድ ብድር500,000.0025%125,000.006 ወር13.5% ለአካል ጉዳተኛ
14% ለሴቶች
14.5% ለመደበኛ
48 ወር
4የቤት መኪና ብድር800,000.0040%320,000.009 ወር14.5%60 ወር
5የንግድ መኪና ብድር1,000,000.0030%300,000.009 ወር14.5%72 ወር
6የቤት ብድር1,000,000.0040%400,000.0012 ወር እና ከዚያ በላይ15%84 ወር
  1. የቁጠባ ዋስትና
  2. በደመወዝ ዋስትና እስከ ብር 100,000 (መቶ ሺሕ ብር)
  3. በንብረት ዋስትና
  4. ለመኪና እና ለቤት ብድር ደግሞ የሚገዛው ንብረት ራሱ ዋስትና መሆን ይችላል
  • የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1,000 (አንድ ሺሕ ብር) ሲሆን አንድ አባል መግዛት የሚችለው ዝቅተኛ መጠን 2 ዕጣዎችን ነው።
  • አንድ አባል በጠቅላላ ጉባኤ እንዲሸጥ ከተወሰነው የዕጣ መጠን ከ10 በመቶ በላይ ድርሻ ሊኖረው አይችልም።
  • የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል በማህበሩ የቁጠባ እና ዕጣ ንጽጽር 1፡3.5 መሠረት በየጊዜው ተጨማሪ ዕጣ መግዛት ይጠበቅበታል።

አማራጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

አያት የክብር ደመና ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት፣ ያህዌ ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 304

ስልክ

  • +251 960 620059
  • +251 960 620060

ኢሜይል

Amarach@gmail.com

ፌስቡክ

Amarach Saving and Credit Cooperative Society

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው አማራጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …