የካቲት 23 የገንዘብ ቁጠባና ብድር

የካቲት 23 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ቁጠባን ባሕል አድርጎ በራስ ገንዘብ ሕይወትን መቀየር ይቻላል ብሎ ያምናል። ይህም ይሳካ ዘንድ መደበኛ እና የፈቃድ ቁጠባ ለአባላቱ ያዘጋጀ ሲሆን ለስድስት ወር በተከታታይ በመቆጠብ ብድር መበደር እንዲችሉ ያደርጋል። በዚህም አባላት የራሳቸውን፣ የቤተሰባቸውን ብሎም የአገራቸውን የእድገት ለውጥ እንዲያፋጥኑ የሚያደርግ ተቋም ነው።

የካቲት 23 የገንዘብ ቁጠባና ብድር የሚሠጣቸው አገልግሎቶች

አባል ለመሆን መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

  • የአባልነት መመዝገቢያ ክፍያ በአንድ ጊዜ የሚከፈል ብር 500 መክፈል
  • ዕጣ (ሼር) መግዛት፦ የአንድ ዕጣ ዋጋ አንድ መቶ ብር ሲሆን አንድ አባል ቢያንስ ስድስት ዕጣዎች (የስድስት መቶ ብር) መግዛት
  • አዲስ አባል ሲመዘገብ የምዝገባ ብር 500፣ የዕጣ ብር 600 እና ወርሃዊ ዕጣና ቁጠባ ብር 450 በድምሩ ብር 1550.00 መክፈል
  • ሁለት ጎርድ ፎቶ ግራፍ (ከ6 ወር ወዲህ የተነሳው) ማቅረብ
  • የታደሰ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት መታወቅያ ይዞ በማበሩ ቢሮ በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የአባልነት ቅጽ መሙላትና አባል መሆን ይቻላል።
የካቲት 23 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ቁጠባን ባሕል አድርጎ በራስ ገንዘብ ሕይወትን መቀየር ይቻላል ብሎ ያምናል። ይህም ይሳካ ዘንድ መደበኛ እና የፈቃድ ቁጠባ ለአባላቱ ያዘጋጀ ሲሆን ለስድስት ወር በተከታታይ በመቆጠብ ብድር መበደር እንዲችሉ ያደርጋል። በዚህም አባላት የራሳቸውን፣ የቤተሰባቸውን ብሎም የአገራቸውን የእድገት ለውጥ እንዲያፋጥኑ የሚያደርግ ተቋም ነው።

መደበኛ ቁጠባ

  • ማንኛውም አባል በወር የዕጣ ግዥና መደበኛ ቁጠባ ጨምሮ ቢያንስ ብር 450.00 (አራት መቶ ሃምሳ ብር) መቆጠብ አለበት

የፍላጎት ቁጠባ

  • አንድ አባል ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ የፈለገውን/ችውን የገንዘብ መጠን በፍላጎት መቆጠብ ይችላል። የፍላጎት ቁጠባውን በየትኛውም ጊዜ ወጪ ማድረግ ይችላል።

የዐጭር ጊዜ ብድር

  • ለበዓል መዋያ በ3 ወር የሚመለስ እስከ ብር 20,000.00
  • ለሠርግ፣ ለቋሚ እቃ መግዣና ለትምህርት በ1 ዓመት የሚመመለስ እስከ ብር 60,000.00
  • ለማኅበራዊ ጉዳይ በ1 ዓመት ከ6 ወር የሚመለስ እስከ 100,000.00

የመካከለኛ ጊዜ ብድር

  • ለግንባታ ግብዓት ግዥ፣ ለገቢ ማስገኛ ሥራ በ4 ዓመት የሚመለስ እስከ ብር 400,000.00
  • የረጅም ጊዜ ብድር
  • ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል ባለ አራት እግር ተሽከርካሪ መግዣ የሚውል በ 5 ዓመት የሚመለስ እስከ ብር 600,000.00
ተ.ቁየብድር ዓይነትየብድር መጠንመመለሻ ጊዜቅድሚያ ቁጠባወለድ
1የበዓል ብድር20,0003 ወርየለም9%
2ለቤት እቃ እና ትምህርት ክፍያ60,0001 ዓመት20%10%
3ለማኅበራዊ ጉዳይ100,0001 ዓመት ከ6 ወር25%11%
4ለንግድ ሥራ400,0004 ዓመት30%12.50%
5ለተሽከርካሪ መግዣ600,0005 ዓመት35%13.50%
የሚሰጠው የተበዳሪውን አቅም በማገናዘብና ባቀረበው ዋስትና መጠን ሲሆን የዋስትና ዓይነቶቹም እንደሚከተሉት ናቸው፦
  • የቁጠባና ዕጣ ዋስትና
  • የደመወዝ ዋስትና
  • የንብረት (የቤት ካርታ ወይም የመኪና ሊብሬ) ዋስትና
  • የማኅበሩ አባል መሆንና ለተከታታይ 6 ወራት መቆጠብ
  • ተገቢውን የብድር ቅድሚያ ቁጠባ መቆጠብ
  • ለሚፈልጉት ብድር መጠን ተመጣጣኝ ዋስትና ማቅረብ
  • 1% የአገልግሎት ክፍያ መክፈል
  • 0.25% (ባለትዳር ካልሆነ) እና 0.5 % (ባለትዳር ከሆነ) የሕይወት መድን ዋስትና ክፍያ መክፈል
  • ባለትዳር ከሆኑ የትዳር አጋር በአካል ማቅረብ
  • የብድር ማመልከቻ በማኅበሩ ቢሮ በአካል ተገኝቶ ማቅረብ

ወለድ አልባ ብድርና ቁጠባ

  • ማኅበሩ ወለድ አልባ የቁጠባና ብድር አገልግሎት ለሚፈልጉ አባላት አገልግሎት ይሰጣል።

የካቲት 23 የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ
  • ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ አበባ
ስልክ
  • +251 916 032137
  • +251 912 772566

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው የካቲት 23 የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኀላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …