መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / በቀን 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርተው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ
sheger-bread

በቀን 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርተው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ተመረቀ

ሸገር ዳቦ ፋብሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና ኢ/ር ታከለ ኡማ በተገኙበት ተመርቆ በይፋ ስራውን ጀምሯል።

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ በሰዓት 80ሺህ በቀን ደግሞ 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርት ሲሆን ለማከፋፈያ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችም ተዘጋጅተዋል።

sheger-bread-3

የፋብሪካው ግንባታ 900 ሚሊየን ብር ወጪ በ9 ወራት ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን ዳቦዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚያቀርብ ይሆናል።

400 የሚሆኑ የአንበሳ አውቶብሶችም እድሳት ተደርጎላቸው ለመሸጫነት እንዲውሉ በየአካባቢው ተዘጋጅተዋል።

ዳቦዎችን ለተጠቃሚዎች እንዲያደርሱ በየአካባቢው ያሉ ወጣቶች ተደራጅተዋል።

የዜና እና የምስል ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …