መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / የከፍታ ፓኬጅን ተጠቀመን ጨረታዎች እያሸነፍን ነው – አንዋር ሱሌማን እና ጓደኞቻቸው የስፖንጅ እና ፎም ውጤቶች አምራች

የከፍታ ፓኬጅን ተጠቀመን ጨረታዎች እያሸነፍን ነው – አንዋር ሱሌማን እና ጓደኞቻቸው የስፖንጅ እና ፎም ውጤቶች አምራች

አንዋር ሱሌማን እና ጓደኞቻቸው የስፖንጅ እና ፎም ውጤቶች የተመሠረተው በ 2010 ዓ.ም በአቶ አንዋር እና አራት መሥራች አባላት ነው። ድርጅቱ የተለያዩ ለአልጋ እና ለትራስ የሚሆኑ ስፖንጆችን የሚያመርት ድርጅት ሲሆን፣ በቀን ሁለት መቶ ሀምሳ ትራሶችን የማምረት አቅም አለው።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች

  • የስፖንጅ ፍራሾች
  • የስፖንጅ ትራሶች
  • እንዲሁም ለትምሕርት ቤቶች እና ለሆስፒታሎች አገልግሎት የሚውሉ የመኝታ ስፖንጆችን ያመርታል።

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ አንዋር ወደ ስፖንጅ ምርት ከመግባታቸው በፊት በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ቆይተው ነበር። ለምሳሌም በአትክልት ተራ አካባቢ በንግድ ሥራ ተሠማርተው ሠርተዋል፣ እንዲሁም በኮንስትራክሽን ጥሬ እቃ አቅራቢነት ላይ ሲሠሩ ነበር። ይሁን እንጂ በነበረው የኮንስትራክሽን ሥራ መቀዛቀዝ እሳቸውም ዘርፍ ቀይረዋል። አቶ አንዋር ጎጃም በረንዳ አካባቢ ምን ብንሠራ ያዋጣናል ብለው ከጓደኞቻቸው ጋር ጥናት ካጠኑ በኋላ ነው ወደ ስፖንጅ ሥራ የተሠማሩት።  ሥራውም ከአካባቢ ጋር የሚሄድ ሥራ ነበር ይህም ማለት በአካባቢው በቂ ጥሬ አቃ አቅርቦት አለ፤ ይህም ለድርጅቱ እድገት ትልቅ አስተፅዖ አበርክቷል ። ድርጅቱ ሲመሠረት አምስቱ መሥራች አባላት አስፈላጊውን ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ ቀጥታ ወደ ሥራ ገብተዋል። ድርጅቱ አሁን ለሦስት ቋሚ ሠራተኞች የሥራ ዕድል ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። እንዲሁም ድርጅቱ ሲመሠረት በሃያ አምስት ሺህ ብር ካፒታል ሲሆን አሁን የሶስት መቶ ሺህ ብር ካፒታል አቅም አካብቷል።

ደርጅቱ ሁለት አይነት ትራሶች ያመርታል፦ የከለር እና የአቡጀዲ ትራሶች።  እነዚህን ትራሶች በተለያየ መጠን በማምረት ለገበያ ያቀርባል።

ከድርጅቱ ምርቶች ውስጥ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው።

  • ዘጠና በአርባ ትራሶች
  • አርባ በሰባ ትራሶች
  • ስልሳ በአርባ ትራሶች
  • ሰማያ በሰማንያ ትራሶች
  • ዘጠና በሰባ ትራሶች
  • አርባ በአርባ ትራሶች እንዲሁም ሜትር ከሰባ የሆኑ ፍራሾች ያመርታል።
  • የትራሶቹን ዋጋ ከመቶ እስከ መቶ ሀምሳ ብር እንደ መጠናቸው ያቀርባል።

ድርጅቱ ሲመሠረት አሁን ላይ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ብዙ ችግሮችን አልፎ ነው የመጣው። ከነበሩ ችግሮች መካከል የገበያ ትስስር አጥረት፣ ምርት በጊዜው ላይወሰድ ይችላል እና ደንበኛን ማግኘት በጣም አስቸጋሪ የሚባሉት ችግሮች ሲሆኑ እነዚህን ችግሮች አልፎ ጠንካራ ሊሆን የቻለው የሚመረተውን ምርት ጥራት መጨመር እና በጣም ጥሩ ባለሙያዎችን በውስጡ በመያዝ ነው። ይህም ማለት ሠራተኞች ስለ ሥራው በቂ ዕውቀት ስለነበራቸው ሥራውን እነሱ ሲሠሩ የተቀሩት ደግሞ ችግሮቹን በመከፋፈል ሊፈቱ ችለዋል። ድርጅቱ አሁን ምርቱን ወደ ክልሎች ድረስ በመላክ ላይ ይገኛል። እንዲሁ አምስት ቋሚ ደንበኞች በክልሎች ሲኖሩት፣ በአዲስ አበባ ደግሞ መርካቶ አካባቢ በብዛት ያከፋፍላል።

ድርጅቱ ሥራ የሚያገኘው በሰው በሰው እና በከፍታ ፓኬጅ 2merkato.com ላይ በማስተዋወቅ ነው። በዚህም ብዙ ደንበኞች ሊያገኝ ችሏል። ድርጅቱ በከፍታ kefta.2merkato.com አማካኝነት በቀረበው ፓኬጅ በመጠቀም ጨረታዎች ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። በዚሁም መሠረት ሁለት ጨረታዎችንም ከክልል ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እና በአዲስ አበባ ላይ በማሸነፍ ሙሉ ሥራውን በጥራት አጠናቆ አስረክቧል።

የኮቪድ ተፅዕኖ

ድርጅቱ በኮቪድ ወረርሽኝ ተዘግቶ ነበር። እንዲሁም ብድር ከአዲስ ብድር እና ቁጠባ ተቋም በመበደር ለሥራ ማስኬጃ በመጠቀም ሊቋቋም ችሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለደንበኞች በዱቤ ከተሸጡ ምርቶች በተሰበሰበ ገቢ የኮቪድ ወረርሽኝ ከተረጋጋ በኋላ ሊቀጥል ችሏል።

ምክር እና እቅድ

ወደ ፊት የተሻለ የማሳያ ሱቅ መክፈት እና ቅርንጫፎችን የመክፈት እቅድ አለው።

አዲስ የሚገቡ ሰዎች ሥራውን ማወቅ አለባቸው፤ የጥሬ እቃ ግብዓት ከየት እንደሚገኝ ማወቅ አለባቸው። ሰው ስለሠራው ብቻ እሠራዋለሁ ማለት ትክክል አይደለም። ስነ-ምግባር ሊኖር ይገባል፤ ደንበኛን ማክበር እና መተማመን ለማደግ አስፈላጊ ነው።

“ምንም አይነት ሥራ መጀመርያ ሲጀመር ይጨንቃል፤ ልከስር እችላለሁ ብሎ ማሰብ አለ ይህንን ሃሳብ በመተው ሰው በድፍረት የሚያውቀውን ሥር ቢሠራ ውጤታማ ይሆናል። እንዲሁም ሰው መቶ እቃ ሲጠይቅ የለም ማለት በፍፁም አይገባም እቃም ተውሶ መሥራት አስፈላጊ ነው ለደንበኛው ፍላጎት ቅድሚያ መሰጠት አለበት።” ሲሉ የድርጅቱ መሥራች መክረዋል። በሠራተኛም ብዙ ሰው ዝም ብሎ ከመያዝ፣ ጥቂት ጥሩ ሠራተኞች መያዝ በጣም በቂ ነው ለሥራ መሻሻል እና እድገት።

አቶ አንዋር 2merkato.com ጠቅሞናል በእጅ በስልካችን ጨረታ ይመጣልናል በጣም ተጠቅመናል ለሌሎችም እንዲጠቀሙ እየመከርን ነው ብለዋል።

አቶ አንዋር kefta.2merkato.com ይህንን እድል ስላመቻቸላቸው በድርጅታቸው ስም አመስግነዋል።
ለበለጠ መረጃ አንዋር ሱለይማን እና ጓደኞቻቸው የስፓንጅና ፎም ውጤቶች ማምረቻ ህ/ሽ/ማ ይመልከቱ ።

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …