መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / “እንሥራ” የሸክላ ስራ ማእከል ተመረቀ
pottery

“እንሥራ” የሸክላ ስራ ማእከል ተመረቀ

“እንሥራ” የሸክላ ስራ ማእከል ተመረቀ። የሸክላ ስራ ማእከሉ ግንባታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ነው።

የሸክላ ስራ ማእከሉን ኢ/ር ታከለ ኡማና ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች መርቀው ስራ አስጀምረውታል። በማእከሉ 1000 በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር የሚያገኙ ይሆናል።

የሸክላ ስራ የሙያውን ያህል ያልተከበረ የድካሙን ያህልም ጥቅም ያልተገኘበት ሆኖ ቆይቷል ያሉት ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ይሄን ዘርፍ ባለሙያዎችን በሚያሳድግ ሀገርን በሚጠቅም መልኩ ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል።

የሸክላ ምርቶቹ ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ገበያ እንዲያገኝ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ንግግር እየተደረገ ነው ያሉት ኢ/ር ታከለ ዘርፉን የሚደግፉ የህግ ማሻሻያዎችም እየተዘጋጁ ነው ብለዋል።

በከተማዋ ከሸክላ ስራ ማእከሉ በተጨማሪ የሸማ ጥበብ ማምረቻና መሸጫ ማእከል ሽሮ ሜዳ አካባቢ እየተገነባ ይገኛል።

የዜና እና የምስል ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ከንቲባ የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

BoJCED-Tamiru-Debela

የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር ለማሳደግ ኤግዚብሽንና ባዛር ጠቃሚ መሆኑ ተገለጸ

በኮቪድ ተፅዕኖ ተቀዛቅዞ የነበረውን የኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስር ለማሳደግ ኤግዚብሽንና ባዛር ጠቃሚ መሆኑን የአዲስ አበባ የሥራ …