መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር

አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር

ኅብረት ሥራ ማህበር ማለት ሰዎች የጋራ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ያላቸውን እውቀት፣ ጉልበት፣ ጊዜ እና ሀብት በማሰባሰብ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዚህ መሠረት አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ መሥራች አባላት በሕጋዊ መንገድ የተመሠረተ ኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።

አጋፔ:- ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማ

ራዕይ

አካባቢያችን እና ማኅበራዊ ዕሴቶቻችን በአግባቡ በመጠበቅ በ2025 የአባላትን የገቢ ደረጃ በማሳደግ ሞዴል የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር ሆኖ ማየት

ተልዕኮ

ለአባላት አስተማማኝ፣ ቀልጣፋ እና ተደራሽ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ፣ እንዲሁም ብቁ ግብአቶችን በማሟላት የኅብረት ሥራ ማኅበር መዋቅራዊና ኢኮኖሚያዊ ቅንጅት በመፍጠር አካባቢያዊ፣ ማኅበራዊ እና የአየር ንብረትን በአግባቡ በመንከባከብ እና አረንጓዴ ልማትን በማስፋፋት እና ታዳሽ ኅይልን በመጠቀም የአባላትን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

ዓላማ

  1. ከአባላቱ ለብድር አገልግሎት የሚውል ገንዘብ በቁጠባ በማሰባሰብ አባላቱን ሥራ ፈጣሪ ማድረግ እና የኑሮ ደረጃቸውን ከፍ ማድረግ
  2. አባል የሆኑ ግለሰቦች ስለ ኅብረት ሥራ ማኅበር ጠቀሜታና አገልግሎት ትምህርትና ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማድረግ
  3. አባላትን በማቀራረብ እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ልምድ እንዲያዳብሩ ማስቻል።

አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

የመደበኛ ቁጠባ

የማህበሩ መነሻ (ዝቅተኛ) መደበኛ ቁጠባ መጠን ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) ወይም የገቢውን 15% ያህል ነው። እያንዳንዱ አባል በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ቁጠባውን መቆጠብ ይኖርበታል። የቁጠባ ወለዱም 7% ነው።

የጊዜ ገደብ ቁጠባ

የማኅበሩ አባል በሆኑ ወይም ባልሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶች ከ6 ወር በላይ እና ከብር 5000 (ዐምስት ሺህ ብር) ጀምሮ የሚቀመጥ ሂሳብ ሲሆን እንደተቀማጭ የገንዘብ መጠን እና ከሚቀመጥበት ጊዜ መነሻ ተደርጎ ከ9-12.5 ወለድ ይከፍላል።

የሕጻናት ቁጠባ

በማኅበራችን የሥራ ክልል ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት የማኅበሩ አባላትም ሆነ አባል ያልሆኑ ልጆች በወላጆቻቸው አማካኝነት 8% ወለድ የሚታሰብለት ከብር 25 (ሃያ ዐምስት ብር) ጀምሮ መቆጠብ የሚያስችል የቁጠባ ሂሳብ ነው። ዕድሜያቸው 18 ዓመት ሲሆናቸው ያለመመዝገቢያ ክፍያ የማህበሩ አባል መሆን ይችላሉ።

ወለድ አልባ ቁጠባ

እንደ ግለሰቡ ፍላጎት የወለድ አልባ ቁጠባ እንዲሁም የብድር አገልግሎት ማግኘት ይችላል።
  • የማኅበሩ አባል የሆነ ሰው የብድር አገልግሎት ለማግኘት በትንሹ ሁለት ወራት መቶጠብ ይኖርበታል።
  • የቁጠባ ቆይታየብድር መጠንቅድሚያ ቁጠባመመለሻ ጊዜ
    2 ወር100,000አንድ አራተኛ የቆጠበ12 ወራት
    3 ወር 150,000አንድ አራተኛ የቆጠበ24 ወራት
    4 ወር200,000አንድ አራተኛ የቆጠበ30 ወራት
    5 ወር300,000አንድ አራተኛ የቆጠበ36 ወራት
    6 ወር400,000አንድ አራተኛ የቆጠበ36 ወራት
    9 ወር500,000አንድ አራተኛ የቆጠበ48 ወራት
    12 ወር600,000አንድ አራተኛ የቆጠበ60 ወራት
    18 ወር በላይ1,000,000አንድ አራተኛ የቆጠበ84 ወራት
  • አባሉ ለብድር የሚሆነውን ቅድሚያ ቁጠባ በሚቆይበት ወራት ከፍሎ መቆጠብ ይኖርበታል።
  • ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
  • ከአባላት ጋር ተመሳሳይ ፍላጎትና ዓላማ ያለው
  • የኅብረት ሥራ ማኅበሩን የመተዳደሪያ ደንብ እና ልዩ ልዩ መመሪያ እና ደንቦችን የሚቀበል
  • የመመዝገቢያ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) መክፈል የሚችል
  • ዝቅተኛው የዕጣ መጠን ሁለት ዕጣ ሆኖ የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በድምሩ ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር) መክፈል የሚችል
  • በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችል በሦስት ወር ከፍሎ ማጠናቀቅ ይችላል
  • በማኅበሩ ውስጥ በተለያዩ ኮሚቴዎች ሲመረጥ ያለ ክፍያ ወይም በውሎ አበል ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ
  • የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) ሲሆን ዝቅተኛ አንድ አባል መግዛት የሚችለው 2 ዕጣዎችን ነው።
  • ማንኛውም የኅብረት ሥራ ማኅበሩ አባል በማኅበሩ የቁጠባና ዕጣ ንፅፅር 3.5፡1 መሠረት በየጊዜው ተጨማሪ ዕጣ መግዛት ይጠበቅበታል።
  • አንድ አባል ለሽያጭ ከቀረቡት 1000 (አንድ ሺህ) ዕጣዎች ከ10% በላይ ድርሻ ሊኖረው አይችልም።

አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር አድራሻ እና ስልክ

አድራሻ

አያት ባቡር ተርሚናል ፊት ለፊት፣ አያት ሞል ሁለተኛ ፎቅ

ስልክ

  • 0920 56 13 74
  • 0967 29 39 33
  • 0913 05 61 92

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው አጋፔ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማኀበር  በአካል ሄዶ በመጠየቅ እና በስልክ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …