አዋጭ ለአነስተኛ የንግድ ሥራ እስከ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ድረስ የሚያበድር ሲሆን ለንግድ መኪና ደግሞ እስከ ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ድረስ ያበድራል።
ለመበደር ምን ማድረግ አለብኝ?
ለአነስተኛ ንግድ ሥራ ብድር አባል ሆኖ ቢያንስ ለ6 (ስድስት) ወራት በተከታታይ መቆጠብ ይኖርበታል። የሚበደረውን ገንዘብ መጠን 25% (አንድ አራተኛ) መቆጠብ አለበት።
የንግድ መኪና ለመግዛት ለሚሰጥ ብድር አባል ሆኖ ቢያንስ ለ 12 (ዐሥራ ሁለት) ወራት በተከታታይ መቆጠብ ይኖርበታል ። የሚበደረውን ገንዘብ መጠን 40% (አርባ በመቶ) መቆጠብ አለበት።
አዋጭ በነኝህ ዋስትናዎች ለአነስተኛ ንግድ እንዲሁም ለንግድ መኪና ያበድራል:- በቁጠባ ዋስትና፣ በደመወዝ ዋስትና እና በአባል ዋስትና፣ በንብረት ዋስትና (ለየመኪና እና የቤት ብድር የሚገዛው ንብረት ራሱ ዋስትና ይሆናል)
የአዋጭ የዋና መሥሪያ ቤት፣ የቅርንጫፎች አድራሻ እና ስልክ ቁጥሮች
ቅርንጫፍ | አድራሻ | ስልክ ቁጥር |
---|---|---|
ዋና መሥሪያ ቤት | አዲስ አበባ፣ አዋሬ አጋር ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 11 557 97 98 |
ዋና መሥሪያ ቤት | አዲስ አበባ፣ አዋሬ አጋር ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 11 557 88 89 |
ዋና መሥሪያ ቤት | አዲስ አበባ፣ አዋሬ አጋር ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 11 557 98 99 |
ዋና መሥሪያ ቤት | አዲስ አበባ፣ አዋሬ አጋር ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 944 69 69 69 |
ቅርንጫፍ | አድራሻ | ስልክ ቁጥር |
---|---|---|
ሥላሴ ቅርንጫፍ | ቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ | +251 111 26 01 92 |
ስታዲዮም ቅርንጫፍ | የሓ ሲቲ ሴንተር 1ኛ ፎቅ | +251 118 12 44 13 |
ስድስትኪሎ ቅርንጫፍ | ሊደርሺፕ ሕንፃ ምድር ላይ | +251 118 68 55 98 |
ልደታ ቅርንጫፍ | ኤ አይ ኤ የገበያ ማዕከል ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 115 30 30 98 |
ሰዓሊተ ምህረት ቅርንጫፍ | ድራር ሞል 1ኛ ፎቅ | +251 116 73 2011 |
ጀሞ ቅርንጫፍ | ኤክስፕረስ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ | +251 113 69 86 83 |
አዲሱ ገበያ ቅርንጫፍ | ጃምቦ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ | +251 111 54 74 40 |
ቦሌ ቅርንጫፍ | ቦሌ መድኃኒዓለም ሽግር ህንፃ ፊት ለፊት ከንብ ባንክ አጠገብ ባለው ህንፃ 1ኛ ፎቅ | +251116671443 |
ቃሊቲ ቅርንጫፍ | ቃሊቲ ቶታል ካፍደም ህንፃ 2ኛ ፎቅ | +251114715955 |
ቅርንጫፍ | አድራሻ | ስልክ ቁጥር |
---|---|---|
ቢሾፍቱ ቅርንጫፍ | ጠንክርና ቤተሰቡ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ | +251 118 12 42 42 |
ጫንጮ ቅርንጫፍ | አዳም ሕንፃ ምድር ላይ | +251 118 12 43 44 |
ሰበታ ቅርንጫፍ | ሳምቡሳ ቤት አካባቢ ኦፍታና ህንፃ ፊትለፊት | +251 113 38 45 23 |
ሆለታ ቅርንጫፍ | ቀልቤሳ ሆቴል አጠገብ ሃና ፋርማሲ ያለበት ህንፃ 1ኛ ፎቅ | +251 112 61 07 77 |
ጠቃሚ መረጃዎች ስለ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የሕብረት ሥራ ማኅበር
ተ.ቁ. | የብድር ዓይነት | የብድር መጠን በብር እስከ | ብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠን በመቶኛ (%) | ብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠን በብር | ብድር ለመውሰድ የቅድመ ቁጠባ መጠንና ጊዜ በተከታታይ | የብድር ወለድ መጠን በመቶኛ (%) | የብድር መመለሻ ጊዜ እና ገደብ |
---|---|---|---|---|---|---|---|
1 | መደበኛ ብድር - ለማኅበራዊ ጉዳይ | 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) | 25% | 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ) | 6 ወር እና ከዚያ በላይ | 13.5% | 3 ዓመት |
2 | መደበኛ ብድር - ለትምህርትና ለጤና | 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) | 25% | 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ) | 6 ወር እና ከዚያ በላይ | 13.5% | 3 ዓመት |
3 | መደበኛ ብድር - ለአነስተኛ ንግድ | 400,000 (አራት መቶ ሺህ) | 25% | 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) | 6 ወር እና ከዚያ በላይ | 13.5% | 3 ዓመት |
4 | ለቤት መኪና ብድር | 600,000 (ስድስት መቶ ሺህ) | 40% | 240,000 (ሁለት መቶ አርባ ሺህ) | 1 ዓመት እና ከዚያ በላይ | 14.5% | 5 ዓመት |
5 | ለንግድ መኪና ብድር | 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) | 40% | 320,000 (ሦስት መቶ ሃያ ሺህ) | 1 ዓመት እና ከዚያ በላይ | 14.5% | 5 ዓመት |
6 | ለቤት ብድር መያዣ መሥሪያ ማደሻ | 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) | 30% | 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ) | 1 ዓመት እና ከዚያ በላይ | 15.5% | 10 ዓመት |
አንድ አዲስ አባል የብድር አገልግሎት ለማግኘት ቢያንስ ለተከታታይ 6ወራት መቆጠብ ሲኖርበት ለመኪና እና ለቤት ብድር ደግሞ ቢያንስ አንድ ዓመት መቆጠብ አለበት በተጨማሪም የገቢ መግለጫ፣ተመጣጣኝ ዋስትና እና የጋብቻን ሁኔታ የሚገልፅ ሰርተፍኬት የራሱም የዋሱንም፣ ባል ወይም ሚስት በአካል ማቅረብ እንዲሁም ዋስም በአካል መቅረብ ይኖርበታል። ተበዳሪው ከጠቅላላ ብድሩ 1% የብድር መድህን እና 1% ደግሞ የአገልግሎት ክፍያ መክፈል አለበት።
- በቁጠባ ዋስትና
- በደመወዝ ዋስትና እና በአባል ዋስትና
- በንብረት ዋስትና የሚሰጥ ብድር
- የመኪና ብድር እና የቤት ብድር የሚገዛው ንብረት ራሱ ዋስትና ይሆናል።
- ማንኛውም ብድር የሚሰጠው የተበዳሪው የመክፈል አቅም ያገናዘበና ባቀረበው ዋስትና መጠን ብቻ ነው።
- የማኅበሩ መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን ብር 350.00 (ሦስት መቶ ሃምሳ) ወይም ከ30 ቀናት ገቢ ውስጥ 10% ሲሆን ይህን ቁጠባ ሳያቋርጥ በየወሩ መቆጠብ ይኖርበታል፣
- እያንዳንዱ አባል ከመነሻ የቁጠባ መጠን በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ መቆጠብ ይችላል።
- አንድ አባል የቆጠበውን መደበኛ ቁጠባ ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ይወስዳል። ነገር ግን ተጨማሪ/የፍላጎት ቁጠባውን አስገዳጅ በሆነ ጊዜ ወጪ አድርጎ መጠቀም ይችላል።
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የህብረት ሥራ ማኅበር ህብረተሰቡ ከሚያገኘው ገቢ ላይ የተወሰነ ገንዘብ በመቆጠብ እራሱን በራሱ እንዲረዳና የቁጠባን ባህል በማዳበር ፈጣን የሆነ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ በአቶ ዘሪሁን ሸለመ ዋና መስራችነት 41አባላትን በማሰባሰብ መጋቢት 13/1999 ዓ.ም. በመጀመሪያ በአራዳ ክፍለ ከተማ በአዋጅ 147/91 ተመሠረተ።
ኅብረት ሥራ ማኅበሩ ባሳየው ከፍተኛ እድገት የሥራ ክልሉን በማስፋት በፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ምዝገባ ቁጥር አገ/ቁ/ብ/005/09 ተመዝግቦ ፈቃድ ያለው፤ በፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ብቃት ማረጋገጫ መመሪያ ቁጥር 018/2007 መሠረት ተመዝኖ 81.65 ከመቶ በማግኘት በከፍተኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ እና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ታህሳስ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. የተሰጠው ኅ/ሥ/ማኅበር ነው።
በተጨማሪም አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓለም አቀፍ ኅብረት ሥራ ኅብረት (CA) አባል እንዲሁም የአፍሪካ የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ኮንፌደሬሽን (ACCOSCA) ተባባሪ አባል የሆነ ማህበረሰብ አቀፍ ህብረት ሥራ ማኅበር ነው።
- መደበኛ ቁጠባ
- የፍላጎት ቁጠባ
- የልጆች ቁጠባ
- የቤት ቁጠባ
- የመኪና ቁጠባ
- የጊዜ ገደብ ቁጠባ
- በተመጣጣኝ ወለድ የብድር አገልግሎት መስጠት
- አነስተኛ የብድር መድህን አገልግሎት
- የትምህርት፣ ሥልጠና እና ማማከር አገልግሎት
- የአዋጭ በሕብረት ሥራ ማኅበሩ የሥራ ክልል ነዋሪ የሆነና የነዋሪነት ማረጋገጫ ያለው
- ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
- የሕብረት ሥራ ማኅበሩ አባል በመሆን በኅብረት ሠርቶ በኅብረት ለማደግ ዓላማ ያለው
- በሕብረት ሥራ ማኅበሩ ደንብና መመሪያ ተገዢ ለመሆን ፈቃደኛ የሆነ/ነች
- በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
- አንድ አመልካች አባል እንዲሆን ሲፈቀድለት የመመዝገቢያ ለአንድ ጊዜ ብቻ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የተወሰነውን የገንዘብ መጠን ይከፍላል።
- ለመመዝገቢያ የተከፈለ ገንዘብ በስንብት ወቅት ለአባላት ተመላሽ አይሆንም።
- የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1,000.00 ሲሆን አንድ አባል መግዛት ያለበት ዝቅተኛው የዕጣ መጠን ሁለት ነው።
- አንድ አባል በጠቅላላ ጉባዔ ተወካይ አባላት እንዲሸጥ ከተወሰነው የዕጣ መጠን ከ10 በመቶ በላይ ድርሻ ሊኖረው አይችልም።
- በሕ/ሥ/ማኅበሩ የዕጣ እና ቁጠባ ምጥጥን መሰረት አንድ አባል በየጊዜው 1፡3.5 መሰረት ዕጣ መግዛት ይጠበቅበታል።
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው አዋጭ በሚያዘጋጀው ብሮሹር እና በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።