መነሻ / ልምድ እና ተሞክሮ / ብሩክ እና የኔነሽ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

ብሩክ እና የኔነሽ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ብሩክ ነጋሽ እና ጓደኛቸው በ2006 ዓ.ም. ሲሆን አጠቃላይ የግንባታ ሥራዎችን በጠቅላላ ተቋራጭነት እንዲሁም የሕንጻ ማጠናቀቅ (ፊኒሺንግ) ሥራዎችን ይሠራል።

ድርጅቱ የሚሠራቸው ሥራዎች

  • የሕንጻ ሥራ – ከፋውንዴሽን ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ
  • የአልሙኒየም ሥራዎች
  • የሕንጻ ጥገና ሥራዎች
  • የብረት ሥራዎች
  • የመጋዘን ሥራዎች
  • የትምህርት ቤት ሕንጻ ግንባታዎች
  • የመንገድ ሥራዎች (በፋብሪካ ውስጥ የመንገድ ሥራ ሠርተዋል)

ማስተዋወቅ እና ማስፋፋት

አቶ ብሩክ ወደ ኮንስትራክሽን ሥራ የገቡት አጋጣሚ የተማሩት ትምህርትም ኮንስትራሽን በመሆኑ እንዲሁም ደግሞ በቅጥርም በዚሁ ሥራ ረዘም ላለ ጊዜ በመሥራታቸው እንደሆነ ገልጸዋል። በኮንስትራክሽን (ከድርጅቱ ምሥረታ በፊት እና በኋላ ያለው ተደምሮ) ከዐሥራ ስድስት ዓመት በላይ የሥራ ልምድ አላቸው። ድርጅቱ ሲመሠረት የነበሩት መሥራች አባላት ሁለት የነበሩ ሲሆን በሂደት ሦስት አባላት ተጨምረው ነበር፤ ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች መሥራት ባለመቻላቸው በአሁን ሰዓት ሲመሠረት የነበሩት ሁለቱ አባላት ናቸው ድርጅቱን እያስተዳደሩት የሚገኙት።

እንደ አቶ ብሩክ አገላለጽ በግል ሥራ የመሥራት ሀሳብ የመጣው ከነሱ ቀድመው የግል ሥራ የጀመሩትን በማየት፣ ከነበረው ተሞክሮ በማየት፣ እንዲሁም ከመንግሥት እና ከግል ድርጅቶች ያለውን ሁኔታ በመመልከት ነው። በፊት ከሠሩባቸው ድርጅቶች  ለምሳሌ ፍሊንትስቶን ሆምስ፣ አዲስ አበባ ተገጣጣሚ ሕንጻ መገጣጠሚያ ማምረቻ አና ከሌሎችም ሥራዎችን እንዴት መሥራት እችላለሁ የሚለውን በማየት ልምድ ቀስመዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሥራው ውስጥ ያሉ ሰዎች እንዴት እንደሚሠሩ ይህም ማለት ዕውቀት ኖሯቸው ልምድ ሳይኖራቸው፣ አንዳንዶች ደግሞ ልምድ ኖሯቸው ያለ ዕውቀት ሲሠሩ ተመልክተዋል። እነሱ ደግሞ ዕውቀቱም ልምዱም ስላላቸው በዚህ ሥራ ብንሠራ የተሻለ ነው ብለው በማጥናት እና በጊዜው የነበረው ሰፊ የገበያ አማራጭ እና ሌሎች ነገሮችን በማየት ነው ድርጅቱን የመሠረቱት።

ድርጅቱ ሲመሠረት የነበረው ካፒታል ብር 50,000 (ሃምሳ ሺሕ ብር) የነበረ ሲሆን አሁን ወደ ብር 1,800,000 (1.8 ሚሊዮን ብር) ማደግ ችሏል። ከዚህም በተጨማሪ ድርጅቱ ሥራ ሲኖር ከዐርባ እስከ ሰማንያ ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ እድል የሚፈጥር ሲሆን በቋሚነት ደግሞ ዐምስት ለሚጠጉ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።

ድርጅቱ እስከ አሁን ባለው የሥራ አፈጻጸም ሁሉንም በተባለው ጊዜ ነው የሚያስረክበው። ለምሳሌ የኢትዮ ቴሌኮምን ሥራ በአንድ ወር ከዐሥራ ዐምስት ቀን፣ የትምህርት ቤት ማስፋፊያ በሦስት ወር አጠናቀዋል። ብሩክ እና የኔነሽ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ሥራዎችን የሚሥራው ከመንግሥት በሚፈጠርለት የሥራ ትሥሥር እና አሁን ደግሞ በቅርቡ 2merkato.com ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ያዘጋጀውን የከፍታ አገልግሎት በመጠቀም ጨረታዎች ላይ ለመሳተፍ እና ብዙ ሥራዎችን ለመሥራት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በጨረታ በመሳተፍ አጠቃላይ አራት ጨረታዎችን አሸንፎ ሥራውን አጠናቅቆ አስረክቧል።

በከፍታ ፓኬጅ ላይ የነበራቸውን አስተያየት ከኮንስትራክሽን ውጪ ሌላ ጨረታ ያመጣብን ነበር፤ አሁን ግን አጠቃቀሙን በመገንዘባችን የኮንስትራክሽን ጨረታ ብቻ እየተከታተልን እንገኛለን ብለዋል።

ድርጅቱ አገልግሎቱን  ሰጥቶ ሥራውን ሠርቶ ካስረከበባቸው ተቋማት ወይም መሥሪያ ቤቶች መካከል

  • ንግድ ባንክ
  • ፊደራል ምግብ ዋስትና
  • ኢትዮ ቴሌኮም  – የታወር ማስፋፋያ እና የአጥር ሥራ
  • ማዘጋጃ ቤት የግቢ አጥር ሥራ እና የጥበቃ ቤት ማማ ሥራ  ሠርተዋል።

ያላቸው አፈጻጸም ታይቶ ደግሞ በዚህ ዓመት ከመንግሥት ዐሥራ አንድ ፕሮጀክቶች ተሰጥቷቸው አጠናቀዋል።

ምክር

አዲስ የሚገቡ ሰዎች የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸው ጥሩ ነው፤ በመቀጠል ደግሞ ቢያንስ የዓንድ ዓመት ወይም የሁለት ዓመት የሥራ ልምድ ይዘው ወደ ሥራ ቢገቡ ጥሩ ነው ብለው ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

የድርጅቱን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የድርጅቱን ስልክ በዚህ ሊንክ በመግባት ዓይተው መደወል ይችላሉ

ይህንንም ይመልከቱ

ገዛኸኝ፣ ቃለአብ እና ጓደኞቻቸው እንጨት እና ብረታ ብረት ሥራ

ድርጅቱ የተመሠረተው በአቶ ገዛኸኝ ተድላ በ2011 ዓ.ም. ነው። ድርጅቱ አጠቃላይ የፈርኒቸር ሥራዎችን ይሠራል፤ ድርጅቱ በአሁኑ …