ቤተሰብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት የተቋቋመ ሕጋዊ ድርጅት ነው። ማኅበሩ ዝቅተኛውን የማኅበረሰብ ክፍልን እና የሥራ ፈጣሪዎችን በተለይ ሴቶችን ማዕከል በማድረግ የጋራ በሆኑት ዕሴቶች ላይ ማለትም ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንዲችሉ የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው።
ቤተሰብ የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና ዕሴቶች
ራዕይ
እስከ 2018 ዓ.ም. ግልጽ፣ ፈጣን እና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት፤ በሀገሪቱ ከሚገኙ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ማኅበራት ልቆ መገኘትተልዕኮ
ዝቅተኛውንና ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የማኅበረ ሰብ ክፍል በማሰባሰብ፣ የቁጠባ ባሕሉን በማዳበር፣ ብሎም ዘላቂና አስተማማኝ የሆነ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በመስጠት የአባላትን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አቅምን ማሳደግዕሴቶች
- ግልጽነት
- ፍጹም ታማኝነት
- ፍትሃዊነት እና ተጠያቂነት
- ደንበኞችን መሠረት ያደረገ የሕዝብ አገልጋይነት
- ለአባላት ዕድገት በዕውቀት ላይ የተመሠረተና ቀጣይነት ያለው የምክርና የሥልጠና አገልግሎት ማግኘት የሚችሉበት ሁኔታዎችን ማመቻቸት
- በአዳዲስ የሥራ ፈጠራ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት አባላት ሥራቸው የሚሻሻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት
ቤተሰብ የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም የሚሰጣቸው አገልግሎቶች
- መደበኛ ቁጠባ
- የፍላጎት ቁጠባ
- የጊዜ ገደብ ቁጠባ
- ወለድ የማይታሰብለት ቁጠባ
- የልጆች ቁጠባ
- የትምህርት ቁጠባ
- አዲስ ንግድ ለመጀመር የሚሰጥ የብድር አገልግሎት
- የነበረ ንግድ ለማስፋፋት የሚሰጥ የብድር አገልግሎት
- የአስቸኳይ ጊዜ ብድር ለጨረታ
- የአስቸኳይ ጊዜ ብድር ለሠርግ
- ለቤት መሥርያ፣ ማደሻ እና ግንባታ ብድር መስጠት
- ለቤት፣ ለንግድ መኪና፣ ለኮንዶሚኒየም ቤት ቅድመ ክፍያና ሙሉ ክፍያ ብድር መስጠት
- እድሜው 16 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ ወይም ዕድሜው ከ16 ዓመት በታች ከሆነ በህጻናት ቁጠባ አባል መሆን ይችላል
- የማህበሩን ዓላማ፣ ደንብ እና መመሪያ የተቀበለ
- በኅብረት ሥራ ማኅበሩ የሥራ ክልል ውስጥ የሚኖርና ገቢ ያለው
- የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እና ሁለት 3*4 ጉርድ ፎቶ
- የመመዝገቢያ ብር 1000
- መደበኛ ወርሃዊ ቁጠባ ብር 500
- የአንድ ዕጣ ዋጋ ብር 1000 ሲሆን ዝቅተኛው የዕጣ መጠን 1 ዕጣ (ሼር) ሲሆን ይህንም መግዛት የሚችል
- የደሞዙን 10% መቆጠብ የሚችል እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአራጣ አበዳሪ ያልሆነ
- የፍላጎት ቁጠባ ማለት አንድ አባል ከመደበኛ ቁጠባ በተጨማሪ የፈለገውን/ችውን የገንዘብ መጠን በፍላጎት መቆጠብ ይችላል
- የፍላጎት ቁጠባው አባሉ በፈልገው ጊዜ ወጪ ሊያደርገው ችይላል
- አባል ተኮር የሥልጠና እና የማማከር አገልግሎት መስጠት
- አነስተኛ የብድር እና የሕይወት መድህን የልምድ ልውውጥ መድረኮች ማመቻቸት
- ለአባላት በተለያየ አርዕስት የተሻለ ወለድ ብድር መስጠት
- ከተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች የአደራ ገንዘብ ተቀብሎ ማስተዳደር
- ለአባላት የቢዝነስ ልማት (BUSINESS DEVELOPMENT) ሥልጠና እና የማማከር አገልግሎት መስጠት
- በተጠኑና አዋጭነት ባላቸው የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሳተፍ አባላትን ተጠቃሚ ማድረግ
ቤተሰብ የገንዘብ ብድርና ቁጠባ ተቋም አድራሻ እና ስልክ
አድራሻ
- ጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 01፣ ሽሮ ሜዳ
ስልክ
- +251 911 646710
- +251 911 627001
- +251 911 215899
- +251 943 048302
- +251 911 133064
ኢሜይል
- tiret.endale@gmail.com
ድረ ገጽ
- https://betsebe.wordpress.com/
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ቤተሰብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል በመሄድ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።