ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማ እና ሴቶች
ራዕይ
ጠንካራ የቁጠባ ባህልን በማሳደግ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት፣ እንዲሁም በኢኮኖሚ የበለጸገ ኅብረተ ሰብን በመፍጠር በ2024 በኢትዮጵያ ተቀዳሚ እና ተመራጭ የኅብረት ሥራ ማኅበር መሆንተልዕኮ
ከአባላት የሚገኘውን ገንዘብ በቁጠባ መልክ በማሰባሰብ የአገሪቱ ማዕከላዊ የገንዘብ ክምችት እንዲዳብር በማድረግ የኢኮኖሚ ችግሮችን በተባበረ ጥረት መፍታት፣ እንዲሁም ሃገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጎዳና ማፋጠንዓላማ
- በአባላት እና በማኅበረ ሰቡ ውስጥ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት እንዲዳብር እና እንዲስፋፋ ማድረግ
- ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ክምችት በተቋሙ በማፍራት የተጠቃሚውን ኅብረተ ሰብ ፍላጎት ማሟላት
- መጠነ ሰፊ የሆነ አባል በማሰባሰብ ከፍተኛ የፋይናንስ አማራጭ አቅራቢ ተቋም መገንባት
- የመንግስትን የልማት ሥራዎችን አማራጭ የፋይናንስ አቅርቦቶችን በማመቻቸት ማገዝ
- ከሌሎችም ተመሳሳይ ኀብረት ሥራ ማኀበራት ጋር ትብብርና ኀብረት በመፍጠር በአገሪቱ የልማት ዕድገት ውስጥ ተሳታፊ ሊሆን የሚቻልበትን ሁኔታ በጋራ ማመቻቸት እና በአከባቢ ልማት ላይ ተሳታፊ መሆን
- አባላትን በማቀራረብ እርስ በእርስ የመረዳዳትና የመተጋገዝ ልምድ እንዲያዳብሩ ማስቻል
ዕሴቶች
የኅብረት ሥራ ዕሴቶች- ራስን በራስ መርዳት
- የግል ኃላፊነትን መወጣት
- የዲሞክራሲ ባሕል ማስፋፋት
- እኩልነት
- ፍትሃዊነት
- ወንድማማችነት
- ታማኝነት
- ግልጽነት
- ተጠያቂነት
- አሳታፊነት
- ማኅበራዊ ኃላፊነት
- ለሌሎች ማሰብ
ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የሚሠጣቸው አገልግሎቶች
- በሕግ መብቱ ያልተገፈፈ
- ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው እና ከዚያ በላይ የሆነ፣ ዕድሜው ከ18 ዓመት በታች ከሆነ በሕጻናት ቁጠባ
- የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 1000፣ የዕጣ (ሼር) ዐሥር (10) እጣ ብር 5,000 እና መደበኛ ቁጠባውን ብር 500 መቆጠብ የሚችል
- የማኅበሩን አላማና ደንብ የተቀበለና ግዴታውን ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ
- በማኅበሩ የሥራ ክልል ውስጥ የሚኖር
- የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ
- ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
ቁጠባ
ቁጠባን ባሕል በማድረግ በራስ ገንዘብ ህይወትን መቀየር፣ ለውጥ ለማምጣት የኅብረት ሥራ ማኅበሩ መደበኛና የፈቃድ ቁጠባ ለአባላቶቹ ያዘጋጀ ሲሆን አባላቶቹ ሼር በመግዛት አባል ከሆኑ በኋላ ቁጠባን ይጀምራሉ። ለስድስት ወር በተከታታይ በመቆጠብ የቁጠባ ባሕላቸውን ካዳበሩ በኋላ ወደ ብድር እንዲሄዱ በማድረግ የራሳቸውን ፣የቤተሰባቸውን ብሎም የአገራቸውን እድገትና ለውጥ እንዲያፋጥኑ ድጋፍ ያደርጋል።መደበኛ ቁጠባ
የኅብረት ሥራ ማኅበሩ መነሻ ወይም ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን በ30 ቀናት (በአንድ ወር) ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ነው። እያንዳንዱ አባል ከመነሻ የቁጠባ መጠን በተጨማሪ የፍላጎት ቁጠባ፣ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ እና የተለያዩ ቁጠባዎችን መቆጠብ ይችላል።የፍላጎት ቁጠባ
መደበኛ መቆጠብ ካለበት 500 ብር እና ከዚያም በላይ የሚቆጠብ ቁጠባ ነው።የጊዜ ገደብ ቁጠባ
-
- ኅብረት ሥራ ማኅበሩ እንደ አስፈላጊነቱ ከአባላቱ ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሠረት ለተወሰነ ጊዜ ለአስቀማጩ ተከፋይ የማይሆን የጊዜ ገደብ ቁጠባ ሊሰበስብ ይችላል።
- ማንኛውም አመልካች አባል እንዲሆን ከተፈቀደለት ዕለት ጀምሮ ያለማቋረጥ በተከታታይ በየወሩ መደበኛ ቁጠባ መቆጠብ ይኖርበታል።
- የትኛውም ቁጠባ አባልነት በሚቋረጥበት ወቅት ተመላሽ ይሆናል።
- አባሉ የፍላጎት ቁጠባ ማውጣት ከፈለገ በጽሑፍ ወይም ኅብረት ሥራ ማኅበሩ ያዘጋጀውን ፎርም ተጠቅሞ በመጠየቅ ማውጣት ይችላል። ሆኖም ተበዳሪ ወይም ዋስ ከሆነ ብድሩ ተከፍሎ ካላለቀ ወይም ዋስትናው ካልተነሳ ማውጣት አይቻልም።
- አባሉ በፍላጎት ያስቀመጠውን የፍላጎት ቁጠባ፤ የተበደረው ብድር ቀሪ ዕዳው የፍላጎት ቁጠባውን ያህል ከሆነና ቁጠባው ለሌላ ተበዳሪ በዋስትና ካልተያዘ የፍላጎት ቁጠባውን ማጣጣት ይችላል።
- አባሉ ያለውን መደበኛ ቁጠባ ማውጣት የሚችለው ከአባልነት ሲለቅ ብቻ ነው።
የልጆች ቁጠባ
የልጆች ቁጠባ ዓላማው ልጆች በለጋ ዕድሜያቸው የቁጠባ ባሕልን እንዲያዳብሩ ለማበረታታት ነው። የልጆች ቁጠባ ደብተርን ለመክፈት ወላጅ/አሳዳጊ የራሱንና የልጁን ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመያዝ ወደ ብርሃን ለኢትዮጵያ ቢሮ በመምጣት መመዝገብ የሚቻል ሲሆን መቆጠብ የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን መቆጠብ ይችላሉ። ይህም ልጆችን ከማበረታታቱም በተጨማሪ ለወጣትነት ዕድሜያቸው የዩኒቨርሲቲ ወጪያቸውን መሸፈኛ ወይም ጥሩ የሥራ መነሻ ሊሆናቸው ይችላል። በተጨማሪም ከኅብረት ሥራ ማህበሩ 8% የተቀማጭ ገንዘብ ወለድ ያገኛሉ።የቁጠባ ዓይነቶች ከሙሉ ዝርዝራቸው ጋር
ተ.ቁ | የቁጠባ ዓይነት | ዝቅተኛው የቁጠባ መጠን | የመቆጠቢያ ጊዜ | የቁጠባ መጠን | ወለድ |
---|---|---|---|---|---|
1 | መደበኛ ቁጠባ | 500 | በየወሩ | 500 | 7% |
2 | መደበኛ ያልሆነ ቁጠባ | 500 | በየወሩ | 500 እና ከዚያ በላይ | 7.5% |
3 | የድርጅቶች (የተቋማት) ቁጠባ | በስምምነት | በስምምነት | በስምምነት | በስምምነት |
4 | የክብረ በዓላት ቁጠባ | 200 | ዝግ | 200 | 7% |
5 | የትምህርት ቁጠባ | 400 | ዝግ | 400 | 7% |
6 | የልጆች ቁጠባ | 100 | በየወሩ | 100 | 8% |
7 | የመኖሪያ ቤት ግንባታ | 1000 | በየወሩ | 1000 | 7% |
8 | የቡድን ቁጠባ | በስምምነት | በስምምነት | በስምምነት | በስምምነት |
9 | የጊዜ ገደብ ቁጠባ | የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ቁጠባ (በብር) | የሚቀመጥበት ጊዜ | የሚከፈል ወለድ መጠን በፐርሰንት | |
9.1 | 50,000-500,000 | 6 ወር | 8.5% | ||
9.2 | 50,000-500,000 | 12 ወር | 9% | ||
9.3 | ከ500,000 በላይ | 6 ወር | 9% | ||
9.4 | 50,000-500,000 | ከ18 ወር አስከ 24 ወር | 10% | ||
9.5 | ከ500,000 በላይ | 12 ወር | 10% |
ማኅበሩ ለአባላት ብድር በመስጠት አባላት በፍላጎታቸው በሚመርጡዋቸው የተለያዩ ሥራ መስኮች በመሰማራት የገቢ ምንጫቸውን እንዲያሰፉና ኑሮአቸው እንዲሻሻል ለማድረግ በትጋት ይሰራል።
በመሆኑም ለአባላቱ የመደበኛ ብድር፣ የቤት (ግዢ፣ እድሳትና ግንባታ) ብድር፣ ለመኪና ግዢ ብድር ይሰጣል።
የብድር ዓይነቶች ከሙሉ ዝርዝራቸው ጋር
የብድር ዓይነት | ብድሩ የሚውለው | የብድር መጠን በብር | ቅድመ ብድር የቁጠባ መጠንና ጊዜ | የብድር ወለድ መጠን በ% | የብድር ውል ጣራ | ||
---|---|---|---|---|---|---|---|
% | በብር | ጊዜ | |||||
መደበኛ ብድር | ለማኅበራዊ ግልጋሎት | 100,000 | 20 | 20,000 | 6 ወርና ከዚያ በላይ | 12.5 | 2 ዓመት |
ለትምህርትና ለጤና | 100,000 | 20 | 20,000 | 6 ወርና ከዚያ በላይ | 12.5 | 2 ዓመት | |
ለንግድ ብድር | 400,000 | 20 | 80,000 | 6 ወርና ከዚያ በላይ | 13.5 | 3 ዓመት | |
የመኪና ብድር | ለመኪና ብድር | 800,000 | 30 | 240,000 | 6 ወርና ከዚያ በላይ | 14.5 | 5 ዓመት |
የቤት ብድር | (ለቤት ግዢ፣ ለቤት ማደሻ፣ ለቤት ግንባታ) | 1,000,000 | 25 | 250,000 | 1 ዓመትና ከዚያ በላይ | 15 | 5 ዓመት |
- ተቀጣሪ ሠራተኛ ከሆነ ገቢውን የሚገልጽ ከሚሠራበት መሥርያ ቤት ወይም ድርጅት ደብዳቤ ማቅረብ
- ነጋዴ ከሆነ የንግድ ፈቃድና የገቢና ወጪ መግለጫ ማቅረብ
- ለብድሩ ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ማቅረብ
- 1.5% የህይወት መድን ዋስትና የሚከፍል
- 3.5% የአገልግሎት የሚከፍል
- ያገባ ወይም ያላገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ፤ ባለትዳር ከሆኑ ሁለቱም በአካል የሚገኙ መሆን አለባቸው
- የብድር ማመልከቻ በአካል ተገኝቶ በተዘጋጀው የማኅበሩ ብድር ማመልከቻ መሙላት
- በቁጠባ ዋስትና የሚሰጥ ብድር
- የአባሉ ቁጠባና የዋሱ ቁጠባ ተደምሮ ያለውን ቁጠባ ያህል ያለ ተጨማሪ ዋስ የሚሰጥ ብድር
- በንብረት ዋስትና የሚሰጥ ብድር፦ የቤት ካርታ እና የመኪና ሊብሬ የተገዛ ወይም የሚገዛ፣ ሊብሬ ከሆነ መኪናው ከተመረተ 15 ዓመት ያልሆነው መሆን አለበት
- ማንኛውም ብድር የሚሰጠው የተበዳሪውን የመክፈል አቅም ያገናዘበና ባቀረበው ዋስትና መጠን ብቻ ነው።
- የብድር ጣሪያው አስከ 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን) ብር ድረስ
- ወለድ ለመደበኛ ብድር ለወንድ 12.5% እንዲሁም ለሴት 12%
- ለመኪና 14.5 %
- ለቤት 15 %
- ለመደበኛ ብድር 2 ዓመት
- ለመኪና ብድር 5 ዓመት
- ለቤት ብድር 5 ዓመት
ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር አድራሻ እና ስልክ
አድራሻ
ጦር ኃይሎች አደባባይ ፊት ለፊት፣ ማክዳ ህንጻ፣ ሦስተኛ ፎቅስልክ
- 0921 752320
- 0988 749301
- 0911 605124
- 0911 874605
ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ብርሃን ለኢትዮጵያ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ እና በዌብሳይት በመመልከት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።