መነሻ / የቢዝነስ ዜና / መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ ጀመረ

መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቱን ለገበያ ማቅረብ ጀመረ

በህግ ማስከበር ዘመቻው ምክንያት ባለፉት አራት ወራት ሥራ አቁሞ የነበረው በትግራይ ክልል የሚገኘው መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የማምረት ሥራውን በመጀመር ምርቱን ለገበያ እያቀረበ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ። ፋብሪካው ምርቱን ለገበያ ማቅረብ መጀመሩ ወደላይ ወጥቶ የነበረውን ዋጋ  ለማሻሻል የራሱ የሆነ አዎንታዊ ሚና  እንደሚኖረው ጨምረው ተናግረዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች የምርት መጠናቸውን በመጨመር በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሲሚንቶን የመሸጫ ዋጋ ተመጣጣኝ እንዲሆን ለማድረግ እየተሠራ ያለው ሥራ አበረታች ውጤት ማምጣቱን የገለጹት አቶ መላኩ በፍላጎትና አቅርቦት መካከል ያለውን ክፍተት ለማስተካከል በከፍተኛ ትኩረት የድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የአንድ ኩንታል የሲሚንቶ ዋጋ አስከ ስድስት መቶ  (600) ብር  (አንዳንድ ቦታዎች በችርቻሮ እስከ ሰባት መቶ ሃያ (720) ብር) ደርሶ ነበር። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ  ዋጋው የጨመረው በሕገ ወጥ ደላሎች እና በገበያ ሻጥር መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። ሚኒስቴሩ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በሠራው ጥብቅ የቁጥጥርና ክትትል ሥራ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ የመሸጫ ዋጋ ወደ 420 ብር ቀንሷል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ያለውን የግንባታ ግብዓቶች (ዕቃዎች፣ ኪራይ፣ የሰው ኃይል) ዋጋ con.2merkato.com ላይ በመግባት ማየት ይቻላል።


የዜና ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፌስቡክ ገጽ
የምስል ምንጭ፦ የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ድረ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …