ይህ ጽሑፍ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በየደረጃው የሚሰጡ ድጋፎችን ያካተተ ሲሆን ዓላማውም ኢንተርፕራይዞች ማግኘት የሚችሉትን የድጋፍ ዓይነቶች በቀላሉ ተረድተው ተጠቃሚ ኢንዲሆኑ ለማድረግ ነው። ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽሕፈት ቤት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።
ተጨማሪድጋፍ
ለኢንተርፕይዞች ማገገሚያና መቋቋሚያ ብድር
ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕይዞችን ማገገሚያና መቋቋሚያ ፕሮጀክት ይህ ፕሮጀክት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከማስተርካርድ ፋውንዴሽንና ከፈርስት ኮንሰልት ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ የደረሰውን የንግድ መቀዛቀዝ ለመገዳደር ጥረት እያደረጉ ያሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማገዝ ነው። ፕሮጀክቱ ዝቅተኛ ወለድ እና የእፎይታ ጊዜ ያለው ብድር በተመረጡ የፋይናንስ …
ተጨማሪየመስሪያ ቦታዎች ድጋፍ
መንግስት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከሚሰጣቸው ድጋፎች አንዱ፣ በራሱ (በመንግስት) በጀት ህንጻ፣ ወርክ ሾፕ እና ሼዶችን በመገንባት ለዕድገት ተኮር ዘርፎች በዝቅተኛ የኪራይ ዋጋ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ነው። የመስሪያ ቦታዎቹ የሚከተሉት መልኮች ሊኖራቸው ይችላል፡- ማምረቻ ህንጻ ወርክ ሾፖች ሼዶች (ማምረቻ) መሸጫ ሕንፃዎች፣ ተለጣፊ ሱቆች፣ መደብሮች፣ ኮንደሚኒየም ሱቆች እና ሼዶች የመስሪያ ቦታዎች ዓይነትና የሚሰጡት …
ተጨማሪበጀማሪ ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ
በምሥረታ ወይም ጀማሪ ደረጃ ላይ የሚገኙ (ገና በመቋቋም ላይ የሚገኙ ወይም ለመቋቋም የሚያስቡ) ኢንተርፕራይዞች፣ የሚያገኙት ድጋፍ ደግሞ እንደሚከተለው ነው። በምሥረታ ወይም ጀማሪ (Start-up) ደረጃ የሚሰጥ ድጋፍ እንዲህ ዓይነቱ ድጋፍ የሚያካትተው ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለመመስረት በመፈለግ በማኅበር እና በግለሰብ በህግ አግባብ ተደራጅተው የራሳቸውን ቁጠባና ከተለያዩ ፋይናንስ ተቋማት ብድር በመውሰድ ወደ ሥራ …
ተጨማሪ