መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / ለኢንተርፕይዞች ማገገሚያና መቋቋሚያ ብድር

ለኢንተርፕይዞች ማገገሚያና መቋቋሚያ ብድር

ማስተርካርድ ፋውንዴሽን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕይዞችን ማገገሚያና መቋቋሚያ ፕሮጀክት

ይህ ፕሮጀክት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከማስተርካርድ ፋውንዴሽንና ከፈርስት ኮንሰልት ጋር በመተባበር የሚተገበር ነው። የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ በኮሮና ወረርሽኝ የተነሳ የደረሰውን የንግድ መቀዛቀዝ ለመገዳደር ጥረት እያደረጉ ያሉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ማገዝ ነው።

ፕሮጀክቱ ዝቅተኛ ወለድ እና የእፎይታ ጊዜ ያለው ብድር በተመረጡ የፋይናንስ ተቋማት አማካኝነት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በማቅረብ የንግድ ሥራቸውን አንዲያስቀጥሉ እና ሠራተኞቻቸውን በሥራቸው ላይ እንዲያቆዩ ያግዛል።

በዚህ የማገገሚያ ብድር ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የማመልከቻ ድረገጽ (www.ethiomsefund.com) ማመልከት ይችላሉ።

በድረገጽ ማመልከት የማይችሉ በአዲስ አበባ የአዋሽ ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች እገዛ ማግኘት ይችላሉ።

የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መገለጫ እና መሰረታዊ የመለያ መስፈርቶች

መደበኛ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች

  • በህግ የተመዘገቡ፣ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የግብር ክፍያ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ
  • አዲስ አበባ ውስጥ ቋሚ የሥራ ቦታ ያላቸው።

ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች (ደረጃ ሐ)

  • 2-5 ሠራተኞች ያላቸው
  • አጠቃላይ ንብረት :- ለአገልግሎት ዘርፍ እስከ ብር 50,000፤ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ እስከ ብር 100,000

አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች (ደረጃ ሐ እና ለ)

  • 6-30 ሠራተኞችን ያላቸው
  • አጠቃላይ ንብረት:- ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ከብር 100,000 እስከ ብር 1,500,000፤ ለአገልግሎት ዘርፍ ከብር 50,000 እስከ ብር 500,000

ኢመደበኛ ኢንተርፕራይዞች

  • በህግ ያልተመዘገቡ/የንግድ ፈቃድ የሌላቸው ነገር ግን ቋሚ የሥራ ቦታ ያላቸው
  • 2-5 ሠራተኞች ያላቸው
  • ጠንካራ የዕሴት ሰንሰለት እና የማደግ ዓቅም ያላቸው።
  • በንግድ ሥራ ላይ እንዳሉ የሚያረጋግጥና ከኮሮና ጋር ተያያዥነት ያላቸው እገዛዎች ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የሚያሳይ ደጋፊ ደብዳቤ ከወረዳ/አካባቢ መስተዳደር ማቅረብ የሚችሉ።
  • የንግድ ሥራ ቦታ/አካባቢ:- ለዚህ ብድር አቅርቦት ማመልከት የሚችሉት አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ብቻ ናቸው።
  • ለዚህ ማስረጃ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የግብር መለያ ቁጥር ሊያሳዩ ይገባል።

የኢንተርፕራይዝ እድሜ:- አመልካች ኢንተርፕራይዞች ከሰኔ 2012 ዓ.ም በፊት ባለው ቢያንስ አንድ ዓመት በሥራ ላይ የቆዩ እና አሁንም በሥራ ላይ ያሉ መሆን አለባቸው።

የሴቶች እና የወጣቶች ቅድሚያ ተጠቃሚነት :- የብድር አቅርቦቱ በሴቶች እና በወጣቶች ለሚተዳደሩ ኢንተርፕራይዞች ከፍ ያለ ድርሻ (ከ50 እስከ 70%) ይሰጣል።

በአመልካቾች መሟላት ያለባቸው ሰነዶች

አመልካቾች የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ለብድር አቅርቦት ድጋፍ ከተመረጡ ብቻ ነው። ሆኖም ሰነዶቹ ቀድመው ዝግጁ አንዲያደድርጉ ይመከራል።

ለመደበኛ ኢንተርፕራይዞች

  • የቀበሌ መታወቂያ
  • የንግድ ፍቃድ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
  • የመሥሪያ ቦታ የኪራይ ስምምነት ወይንም በመንግስት የቀረቡ ሼድ የሚያረጋግጥ ሰነድ
  • ከሠራተኞች ጋር ያለ የቅጥር ውል
  • የሠራተኞች የጡረታ መዋጮ ሰነድ
  • ዓመታዊ የሽያጭ መረጃ/ የፋይናንስ መግለጫዎች
  • የጋብቻ ወይም ስድስት ወር ያላለፈው ያላገባ/ች የምስክር ወረቀት

ለኢመደበኛ ኢንተርፕራዞች

  • የቀበሌ መታወቂያ
  • ከወረዳ/አካባቢ መስተዳደር ለተሰጠ የመሥሪያ ቦታ የፍቃድ ደብዳቤ
  • በኪራይ ለተያዘ የመሥሪያ ቦታ የኪራይ ስምምነት
  • በመሥሪያ ቦታ ላይ ያለው የንግድ መኖር ማስረጃ

ኢንተርፕራይዞች በሚከተሉት ምክንያቶች በፕሮጀክቱ ላይካተቱ ይችላሉ

  • ተመላሽ ያልሆነ የገንዘብ እገዛ፣ የመክፈያ ጊዜ እፎይታ እና አነስተኛ ወለድ የሚከፈልባቸው ብድሮች ተጠቃሚ ከሆኑ፣
  • ከመጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. በፊት የፋይናንስ ዕዳ/ችግሮች ከነበሩባቸው፣
  • የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ እና አስተዳደራዊ ተስማሚነት መስፈርቶችን የማያሟሉ (የአልኮል፣ ሲጋራ እና አደንዛዥ-ዕፅ ንግድ፣ የጦር መሳሪያ ምርት እና ከጦርነት ጋር የተገኛኙ እንቅስቃሴዎችን፣ ቁማር፣ ከወሲብ ጋር የተገኛኙ ኢንዱስትሪዎች ከሆኑ)፣
  • ከመንግስት ባለቤትነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው፣
  • አግባብነት ለሌለው የግል ጥቅም የሚያውሉ፣
  • የወደኋላ ተከፋይ ብድር ለመክፈል የሚያውሉ፣
  • ለህገ ወጥ ወይም ለፓለቲካ አላማዎች የሚያውሉ

ምንጭ፦ አዋሽ ባንክ የማስታወቂያ ሰሌዳ

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …