መነሻ / የጥቃቅን እና አነስተኛ መረጃ / ወቅታዊ መረጃ / የሲሚንቶን እጥረት ለመቅረፍ እየተሠራ ነው – ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
cement-bag

የሲሚንቶን እጥረት ለመቅረፍ እየተሠራ ነው – ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የሲሚንቶ ችግር ለመቅረፍ የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ገለጹ፡፡

ለሲሚንቶ እጥረት መከሰት በዋናነት የመለዋወጫ ችግር፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ፣ የግብዓት እጥረት ፣ የአመራርና የባለሙያ የክህሎት ክፍተት መኖር፣ የፀጥታ ችግር፣ የጥሬ እቃ አቅርቦት እና ሌሎች ችግሮች መኖራቸው ነው ያሉት አቶ መላኩ ችግሩን ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት በመሠራቱ መሻሻል መታየቱን ተናግረዋል፡፡

በፋብሪካዎች ላይ እየተፈጠረ ያለውን የመለዋወጫ ችግር ለመቀረፍ 85 ሚሊዮን ዶላር ተመድቦ እየተሠራ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትሩ ይህም የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ወደ 63 በመቶ ከፍ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም ወቅታዊውን ችግር ለመቅረፍ 3 ሚሊዮን ቶን ሲሚንቶ ከውጪ ለማስገባት መወሰኑን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በዘላቂነት የሲሚንቶን የገበያ ችግር ለመፍታት መመሪያ መዘጋጀቱንና ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

የዜና ምንጭ፦ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር የፌስቡክ ገጽ

ይህንንም ይመልከቱ

kefta-care-training-2

ከፍታ ለ20 ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ

ከፍታ ከኬር ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለ20 በሴቶች ለሚተዳደሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና ሰጠ። ሥልጠናው ያተኮረው …