ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች በከተማና በገጠር የሚኖሩ ለሥራ ተነሻሽነት ያላቸው ዜጎች በተለይም የባንክ አገልግሎት ዕድል ለተነፈጉ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ነጋዴዎችና አርሶ አደሮች የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በማግኘት የተቋቋመ ተቋም ነው።

ራዕይ

የተሻለ የፋይናንስ አቅርቦት ለተጠቃሚዎች በማቅረብ፤ እንዲሁም ደንበኞችን፣ ባለአክስዮኖችን፣ ሠራተኞችንና አጠቃላይ ኅብረተ ሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎችን በመሥራት በሀገሪቱ ካሉት የፋይናንስ ተቋማት ቀዳሚ ሆኖ መገኘት ነው።

ተልዕኮ

የደንበኞችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የተለያዩ የብድርና የቁጠባ ዓይነቶችን በማዘጋጀት ቀጣይነት ባለው መልኩ የገንዘብ ምንጭ አጥተው በድህነት ውስጥ የሚገኙ ምርታማ ዜጎችን በተለይም በከተማና በገጠር የሚኖሩ ወጣቶች፤ ሴቶችና በንግድ ላይ የተሰማሩ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች ኑሮዋቸው ተቀይሮ ለማየት የሚሠራ ተቋም ነው።

ማኅበራዊ ግቦች

ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ዓላማ ያደረገው አቅምና ጉልበት ያላቸውን ምርታማ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች በተለይም በከተማና በገጠር የሚኖሩ ወጣቶች፤ ሴቶችንና በንግድ ላይ የተሰማሩ ማኅበረ ሰቦችን ጥራቱን በጠበቀና የደንበኞችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ቀጣይ የሆነ የገንዘብ ምንጭ በማቅረብ አዎንታዊ ለውጦች በማምጣት ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ደህንነታቸውን ማሻሻል ነው።

ግራንድ ማይኮሮፋይናንስ፡- የተቋሙ አገልግሎቶች

 1. የብድር አቅርቦት
 2. የቁጠባ አገልግሎት
 3. የአነስተኛ ብድር የህይወት መድን
 4. የሞባይል ባንኪንግ እና የኤጀንት ባንኪንግ አገልግሎት
  ተቋሙ የደንበኞችን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ በርካታ የብድር አገልግሎቶችን ለደንበኞች እንዲደርሱ በማድረግ ላይ ይገኛል፤ በዚሁ መሠረት የሚሠጣቸው የብድር አገልግሎቶች
 1. የግል ንግር ብድር
 2. የቡድን ንግድ ብድር
 3. የሠራተኞች ብድር (የፍጆታ ብድር)
 4. የታዳሽ ኃይል አቅርቦት (ሶላር፤ባዮጋዝ...) ብድር
 5. የእርሻ ብድር
 6. የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች ብድር
 7. የማኅበራት ብድር እና ሌሎችም
 8. የቋሚ ንብረት ግዢ ብድር
 1. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነና ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው፣ የራሱ የገቢ ምንጭ ያለውና በራሱ ወይም በድርጅቱ ሠርቶ ብድሩን መክፈል የሚችል
 2. በተለያዩ የንግድ ሥራ፤ በግብርና እና በቋሚ ደመወዝ የሚተዳደሩት የኅብረተሰብ ክፍሎች
የቡድን ብድር
 1. የደንበኛው የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
 2. የደንበኛው ቲን ሰርተፍኬት ኮፒ
 3. የጋብቻ ሰርተፍኬት ኮፒ፣ ያላገባ ከሆነ ማስረጃ ኮፒ
 4. የባለቤት መታወቂያ ኮፒ
 5. የቀበሌ/ወረዳ ድጋፍ ደብዳቤ
 6. የተበዳሪው 2፣ የባለቤት 1 እና የዋሱ 1 ፎቶግራፎች
የግል ንግድ ብድር
 1. የደንበኛው የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
 2. የደንበኛው ቲን ሰርተፍኬት ኮፒ
 3. የደንበኛው የታደሰ ንግድ ፈቃድ
 4. የደንበኛው የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት
 5. የጋብቻ ሰርተፍኬት ኮፒ፣ ያላገባ ከሆነ ማስረጃ ኮፒ
 6. የባለቤት መታወቂያ ኮፒ
 7. የተበዳሪው 2፣ የባለቤት 1 እና የዋሱ 1 ፎቶግራፎች
የሠራተኞች (የፍጆታ) ብድር
 1. የደንበኛው የታደሰ የመስሪያ ቤትና የቀበሌ መታወቂያ ኮፒ
 2. የደንበኛው ቲን ሰርተፍኬት ኮፒ
 3. የጋብቻ ሰርተፍኬት ኮፒ፣ ያላገባ ከሆነ ማስረጃ ኮፒ
 4. የባለቤት መታወቂያ ኮፒ
 5. የመሥሪያ ቤቱ የዋስትና ደብዳቤ
 6. ከዋሱ መሥሪያ ቤት የዋስትና ደብዳቤ
 7. የዋሱ የቀበሌና የመሥሪያ ቤቱ መታወቂያ ኮፒ
 8. የተበዳሪው 2፣ የባለቤት 1 እና የዋሱ 1 ፎቶግራፎች
 1. የመደበኛ የውዴታ ቁጠባ
 2. የጊዜ ገደብ ቁጠባ
 3. የተቋማት ቁጠባ
 4. የህጻናት፤ የታዳጊዎችና የወጣቶች ቁጠባ
 5. የእናቶች ቁጠባ እና
 6. የሳጥን ቁጠባ የሚጠቀሱ ናቸው።
 1. ማንኛውም ግለሰብ የሚያስፈልገውን የቁጠባ መጠን መቆጠብ
 2. ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፎች
 3. የታደሰ መታወቂያ
ቅርንጫፍአድራሻ ስልክ
ዋና መሥሪያ ቤትደብረ ዘይት መንገድ፣ ጋራድ ሕንጻ፣ 7ኛ ፎቅ0114 70 51 02
ቄራ ቅርንጫፍሶፊያ ሞል ፊት ለፊት (አያሌው ሕንጻ 2ኛ ፎቅ)0114 70 13 15
ኮልፌ ቅርንጫፍ እፎይታ የገበያ ማዕከል ሕንጻ፣ 3ኛ ፎቅ0112 73 99 01
አዳማ ቅርንጫፍ ደራርቱ ቱሉ አደባባይ ፊት ለፊት ጀርመን ሲቲ ሞል፣ 2ተኛ ፎቅ0222 11 92 93
ሀዋሳ ቅርንጫፍ አቶቴ በሹ ኢንተናሽናል ሆቴል ጎን ዳሽን ባንክ ያለበት ሕንጻ፣ 1ኛ ፎቅ0462 12 74 77

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ግራንድ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በአካል ሄዶ በመጠየቅ በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ.

ኒኦ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሠረት በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ …