መነሻ / ፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት / የግል ብድር እና ቁጠባ ተቋማት / በጋራ እንችላለን – ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር
sheger-logo

በጋራ እንችላለን – ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር የቁጠባ ባሕልን ለማሳደግ፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ አሁን ከደረሰበት ደረጃ ጋር በተያያዘ በኢኮኖሚው ዘርፍ ጠንካራ ተዋናይ ሆኖ ለመገኘት የሚያስፈልገውን የፋይናንስ ፍላጎት በጋራ ሆኖ ለማሟላት፣ እንዲሁም የገንዘብ አጠቃቀምና አስተዳደር ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ዓላማ ባደረጉ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ማኅበር ነው። ማኅበሩ በ2009 ዓ.ም. የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ለማቋቋም በተደነገገው አዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት መጋቢት 4 ቀን፣ 2013 ዓ.ም. የተመሠረተ እና በአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ጀንሲ ሕጋዊ እውቅና ያገኘ ማኅበር ነው።

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር፦ ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዓላማ እና ዕሴቶች

ራዕይ

በ2027 ዓ.ም. በአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን የገንዘብ ብድር እና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ማኅበር ሆኖ ማየት

ተልዕኮ

በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ የቁጠባ እና ብድር የኅብረት ሥራ ማኅበር የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት፣ በጋራ ለማደግ ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት እና ባንክ ነክ አገልግሎት በመስጠት እና የአባላትን ኑሮ ደረጃ በማሻሻል በሀገራችን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽዖ ማድረግ

ዓላማ

የኅብረት ሥራ ማኅበሩ ዋና ዓላማ ከባንክ ሥርዓት የፋይናስ ፍላጎታቸውን ሊያሟሉ ለማይችሉ የኅብረተ ሰብ ክፍሎች የገንዘብ አስተዳደርና አጠቃቀም ግንዛቤ በማስጨበጥ የቁጠባ ባሕልን ማሳደግ እና ለአባላት ምቹና አስተማማኝ የፋይናንስ አገልግሎቶችን መስጠት ነው። የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች አሉት
  • የአባላት ፍላጎትን መሠረት ያደረገ መደበኛ እና የፍላጎት ቁጠባና የተለያዩ የብድር አገልግሎቶች በመስጠት፣ የኢንቨስትመንት አቅም ማጎልበት
  • የአነስተኛ ብድር መሠረት ያደረገ መድን ዋስትና አገልግሎቶች በመስጠት ማኅበራዊ ቀውስን ማስወገድ
  • የተለያዩ የፋይናስ አገልግሎቶችን በመስጠት የኅብረት ሥራ ማኅበሩን ካፒታል ማጠናከር
  • ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሥርዓት በመዘርጋት የኅብረት ሥራ ማኅበሩንና አባላቱን ዘመናዊ የኮር ባንኪንግ ሥርዓት እና ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎት ማዳረስ
  • ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር ለማኅበረ ሰቡ የተደራጀ የፋይናንስ አቅርቦት መሰረት መጣል
  • ከኅብረት ሥራ ማኅበሩ አደራጅ ተቋም እና ከተለያዩ አስተዳደር ኣካላትና ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የአባልነት ሽፋንን ማሳደግ፣ በተለያዩ ምክንያቶች አባል ሊሆኑ ለማይችሉ የኀብረተሰብ ክፍሎች ተስማሚ አገልግሎቶችን በማቅረብ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ማሳደግና የመቆጠብና ኢንቨስትመንት ባሕልን በማዳበር በብሔራዊ የገንዘብ ዝውውርና ክምችት ላይ የራሱን አስተዋጽዖ ለማበርከት ጠንክሮ መሥራት
  • የፋይናንስ አገልግሎት አካታችነት በማሳደግ፣ የኅብረተ ሰቡን የፋይናንስ ክህሎትና የቁጠባ ባሕልን በማዳበር የአባላትን በራስ የመተማመን አቅም ማጎልበት
  • የፋይናንስ ተቋማት እና ኀብረት ሥራ ማኀበሩ የፋይናንስ ትስስር በመፍጠር የሚከሰተውን የፋይናንስ እጥረትና ክምችት ችግርን መፍታት

ዕሴቶች

  • ቅንነት
  • ግልጽነት
  • ተጠያቂነት
  • አሳታፊነት
  • ማኅበራዊ ኃላፊነት
  • ሌሎችን መንከባከብ

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

መደበኛ የተቀማጭ ሂሳብ

  • ሁሉም አባላት በኅብረት ሥራ ማኅበሩ ወስጥ አባል ሁነው እስከቀጠሉ ድረስ መደበኛ ቁጠባቸውን ማቋረጥ አይችሉም።
  • የመደበኛ ቁጠባ መጠን በጠቅላላ ጉባኤ የተወሰነ ለሁሉም እኩል የሆነ 500 ብር ነው።
  • ለመደበኛ ቁጠባ 7% ወለድ ይታሰብለታል።
  • በተከታታይ ሦስት ወር ያልቆጠበ በፈቃደኝነት እንደተሰናበተ ይቆጠራል።
  • ይህ ቁጠባ ለብድር እንደ ቅድመ ቁጠባ ያገለግላል።
  • ወጭ የሚሆነውም በጠቅላ ጉባኤ አባላቱ በሚወስኑት ውሳኔ ይሆናል።

የህጻናት የተቀማጭ ሂሳብ

ለህጻናት የሚቆጠብ የተሻለ ወለድ የሚታሰብለት የቁጠባ ዓይነት ነው።

ለመኪና ግዢ የሚቆጠብ

መኪና መግዛት የሚፈልጉ አባላት የሚቆጥቡት የቁጠባ አይነት ነው። በዚህ ቁጠባ አንድ አባል እስከ 1.5 ሚሊዮን (1,500,000) ብር ድረስ መበደር ይችላል። ብድሩንም ለማግኘት አባሉ የሚወስደውን የብድር መጠን 20% ሳይቆራረጥ መቆጠብና 15% ሼር መግዛት ይኖርበታል፤ ወይም በአንድ ጊዜ መጀመሪያ ቆጥቦ ጊዜ ገደቡን ጠብቆ መበደር ይቻላል። ለብድሩ ዋስትና የሚሆነው የሚገዛው መኪና ይሆናል። ኅብረት ሥራ ማኅበሩ በቂ ሀብት ካለው ከጊዜ ገደቡ ቀድሞ ሊያበድር ይችላል።

ለቤት የሚቆጠብ

ቤት መግዛት የሚፈልጉ አባላት የሚቆጥቡት የቁጠባ አይነት ነው። በዚህ ቁጠባ አንድ አባል እስከ 2.5 ሚሊዮን (2,500,000) ብር ድረስ መበደር ይችላል። ብድሩንም ለማግኘት አባሉ የሚወስደውን የብድር መጠን 20% ሳይቆራረጥ መቆጠብና 10% ሼር መግዛት ይኖርበታል፤ ወይም በአንድ ጊዜ መጀመሪያ ቆጥቦ ጊዜ ገደቡን ጠብቆ መበደር ይቻላል። ለብድሩ ዋስትና የሚሆነው የሚገዛው ቤት ይሆናል። ኅብረት ሥራ ማኅበሩ በቂ ሀብት ካለው ከጊዜ ገደቡ ቀድሞ ሊያበድር ይችላል።

የውስን ጊዜ ቁጠባ (Fixed Time Deposit)

ለተወሰነ የጊዜ ገደብ ከ9 በመቶ እሰከ 11.5 በመቶ የተሻለ ወለድ በድርድር እና በስምምነት የሚቆጠብ የቁጠባ ዓይነት ነው።

መደበኛ ብድር

መደበኛ ብድር የሚባለው ጣራው 1 ሚሊየን (1,000,000) ብር ሲሆን አባሉ ለተለያዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች የሚወስደው ብድር ሲሆን የአባሉ መዋጮ 15% ይሆናል።
  • ሦስት (3) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 10% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን፣ የብድር ጣራው ብር አንድ መቶ ሃያ ሺህ (120‚000.00) ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 48 ወር ድረስ ይሆናል።
  • አራት (4) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 10% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን፣ የብድር ጣራው ብር ሁለት መቶ ሺህ (200‚000.00) ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 48 ወር ድረስ ይሆናል።
  • አምስት (5) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 10% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን፣ የብድር ጣራው ብር ሦስት መቶ ሺህ (300‚000.00) ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 48 ወር ድረስ ይሆናል።
  • ስድስት (6) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 10% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን፣ የብድር ጣራው ብር አምስት መቶ ሺህ (500‚000.00) ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 48 ወር ድረስ ይሆናል።
  • ሰባት (7) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 10% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን፣ የብድር ጣራው ብር ሦስት መቶ ሺህ (600‚000.00) ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 48 ወር ድረስ ይሆናል።
  • ስምንት (8) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 10% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን፣ የብድር ጣራው ብር ሰባት መቶ ሺህ (700‚000.00) ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወር ድረስ ይሆናል።
  • ዘጠኝ (9) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 10% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን፣ የብድር ጣራው ብር ስምንት መቶ ሺህ (800‚000.00) ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወር ድረስ ይሆናል።፡
  • ዐሥራ ሁለት (12) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 10% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 5% እጣ የገዛ አባል መደበኛ ብድር የሚያገኝ ሲሆን፣ የብድር ጣራው ብር አንድ ሚሊየን (1,000‚000.00) ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 60 ወር ድረስ ይሆናል።

የመኪና ብድር

የመኪና ብድር ዐሥራ ሁለት (12) ወር በተከታታይ የሚበደረውን 20% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 15% እጣ የገዛ አባል የመኪና ብድር የሚያገኝ ሲሆን የብድር ጣራው ብር 1.5 ሚሊዮን (1‚500‚000.00) ሲሆን፣ የመመለሻ ጊዜው እስከ 72 ወር ድረስ ይሆናል፡፡

የቤት ብድር

የቤት ብድር ዐሥራ ሁለት (12) በተከታታይ የሚበደረውን 20% መደበኛ ቁጠባ የቆጠበ እና 10% እጣ የገዛ አባል የቤት ብድር የሚያገኝ ሲሆን፣ የብድር ጣራው ብር 2.5 ሚሊዮን (2‚500‚000.00) ሲሆን የመመለሻ ጊዜው እስከ 180 ወራት ድረስ ይሆናል፡፡
  • ብድር ጠያቂው የማኅበሩ አባል መሆን አለበት
  • አባል ሆኖ ሁለት ወር መቆየት ይኖርበታል
  • እንደሚበደረው የገንዘብ መጠን በማኅበሩ የተቀመጠውን የቆይታ ጊዜ ማሟላት አለበት
  • በሚጠይቀው የገንዘብ መጠን ልክ በማኅበሩ የተቀመጠውን ሼር የገዛ እና ቁጠባውን ቀድሞ ወይም ሳይቆራረጥ ብድሩን እስኪጠይቅ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የቆጠበ መሆን አለበት
  • የገቢ ማስረጃ እና ዋስትና ማቅረብ የሚችል
  • የታደሰ መታወቂያ ካርድ ማቅረብ የሚችል
  • የተበዳሪውንም ሆነ የዋሱን ያገባ ያላገባ ጊዜው ያላለፈበት ሰርተፊኬት ማምጣት የሚችል
  • ብድሩ ለንግድ ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርትፊኬት እና የ1 ዓመት የቤት ኪራይ ውል
  • ብድር ባነሰ ወለድ በሚመጥን መስፈርት ይወስዳሉ
  • የድርጅት ባለቤት ይሆናሉ
  • በዓመቱ መጨረሻ የትርፍ ተካፋይ ይሆናሉ
  • የተለያዩ የሥልጠና ዕድሎች ያገኛሉ
  • በሕግ መብቱ ያልተገደበ
  • ዕድሜው 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ
  • ከአባላት ጋር ተመሳሳይ ፍላጐትና ዓላማ ያለው
  • ጥሩ ባሕሪ ኖሮት በኀብረት ሥራ ማኀበሩ መርህ እና ዕሴት የሚያምን
  • የመመዝገቢያ እና ዝቅተኛውን የዕጣ ክፍያ መክፈል የሚችል
  • የኅብረት ሥራ ማኅበሩን የመተዳደሪያ ደንብ እና ልዩ ልዩ መመሪያ እና ደንቦችን የተቀበለ እና በሚሻሻልበት ወቅት በ15 ተከታታይ ቀናት በውስጥ ማስታወቂያ ከተለጠፈ ተፈፃሚነቱን የሚቀበል
  • በማኅበሩ ውስጥ በተለያዩ ኮሚቴዎች ሲመረጥ ያለ ክፍያ ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ
  • መመዝገቢያ እና ወርሀዊ መደበኛ የቁጠባ መጠን ለሁሉም አንድ ሲሆን፣ አባል መሆን የሚፈልግ የመመዝገቢያ ብር አንድ ሺህ (1000) እና መደበኛ ወርሀዊ ቁጠባ  ብር አምስት መቶ (500) መክፈል አለበት
  • የአንድ እጣ ዋጋ 200 ብር ነው ሲሆን ዝቅተኛ የእጣ ግዥ መጠን ዐሥር (10) ይህም ብር ሁለት ሺህ (2000) መፈጸም አለበት
  • ከፍተኛ የእጣ ግዥ መጠን አንድ ሺህ ሁለት መቶ (1200) ዕጣዎች ወይም የኅብረት ሥራ ማኅበሩን ካፒታል 10% ድረስ ነው

ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር፦ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር

ዋና መሥሪያ ቤት

ሜክሲኮ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ሕንጻ 4ኛ ፎቅ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ኢሜይል

shegersmart@gmail.ccom

ስልክ

    • +251948051115
    • +2510118550035

ዌብ ሳይት

https://shegersacco.com/

ማስታወሻ፦ ይሄ መረጃ የተዘጋጀው ሸገር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በአካል ሄዶ በመጠየቅና እና የማኅበሩን ድረ ገጽ በመመልከት በተገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶች በሚጠቅም መልኩ ተቀናብሮ ነው።

ይህንንም ይመልከቱ

liyu-logo

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም

ልዩ የገንዘብ የእገዛ ተቋም መንግሥት ባወጣው የአንስተኛ ፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 40/88 መሠረት …